ፈልግ

ማህታማ ጋንዲ፣ ማህታማ ጋንዲ፣  

የማህታማ ጋንዲ ሕይወት ዛሬም መልካም ምሳሌ ሆኖ መገኘቱ ተነገረ።

እ.አ.አ. ጥቅምት 2 ቀን 2019 አ/ም/ የማሃትማ ጋንዲ የ150 ኛ አመት የልደት በአል በሚከበርበት ቀን ዋዜማ በቅድስት መንበር የህንዱ አምባሳደር አቶ ሲቢ ጆርጅ ለአንድ ቀን የፈጀ በእምነት ነክ ጉዳዮች ላይ በቫቲካን በተደረገ ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መቅድም ገረመው - ቫቲካን

የማሃትማ ጋንዲ 150ኛው አመት የልደት በዓል እ.አ.አ. ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 2 ቀን በህንድ ሃገር ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ዙሪያ ባሉ መንግስታት ፣ ድርጅቶችና ሰዎችም ጭምር በተለያዩ ፕሮግራሞች ታጅቦ ተከብሯል፡፡ የዚህ ሰው ታላቅነት፣የህንዳውያን አባት ተብሎ ያስጠራቸው ሲሆን ዛሬም ድረስ ከሞቱ ከብዙ ዓመታት በኋላም እንኳን በጣም የተወደዱ እና የተከበሩ መሆናቸው ማስረጃ ነው፡፡

እ.አ.አ. ጥቅምት 2 ቀን በ1869 በጉጃራት ውስጥ በሚገኘው ፖርባንደር የተወለዱት ማሃትማ ጋንዲ የሕግ ተሟጋች ሲሆኑ የብሪታንያን አገዛዝ በመቃወም የህንድ የነፃነት ንቅናቄን በተሳካ ሁኔታ መምራት ችሏል ፡፡ በሕንድ መኳንንት ሎሬት ራቢንድራናት ታጎሬ “ማሃትማ” ወይም (“ታላቅ ነፍስ”) የሚል ማዕረግ የተሰጣቸው ጋንዲ እ.አ.አ. ጥር 30 ቀን 1948 አ-ም በ 78 ዓመታቸው በዴልሂ ተገድለዋል፡፡

ጋንዲ በዓለም ዙሪያ ለሲቪል መብቶች እና ለማህበራዊ ለውጦች ተነሳሽነት የፈጠረ ሲሆን የሳቸውን ፍልስፍና ከተቀበሉ የዘመናችን ታላላቅ ሰዎች መካከል የዩኤስ የሲቪል መብቶች መሪ የነበሩት ማርቲን ሉተር ኪንግ ጂ አር እና የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ ይገኙባቸዋል፡፡

የጋንዲ ገድል በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ የተባበሩት መንግስታት በሰኔ 15ቱ በ2007 አ-ም ጠቅላላ ጉባኤው  የአለም የጸረ- አመጽ ቀን በማለት የጋንዲን የልደት ቀን እ.አ.አ. ጥቅምት 2ትን ሰይመዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የተባበሩት መንግስታት  የሰላም ፣ የመቻቻል ፣ የመረዳዳትን ባህል አለማቀፋዊ ፋይዳን ለማረጋገጥ ይሆናልም ብለዋል።

እ.አ.አ.ማክሰኞ እለት የጋንዲ 150ኛው የልደት በዓል ዋዜማ ፣ በቅድስት መንበር የአብያተ ክርስቲያናት ውይይት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ማሃትማ ጋንዲን አስመልክቶ የወንድማማችነት ፍቅር፣ጸረ-አመጽ እንዲሁም ለአለም ሰላም በሚል ርእስ የአንድ ቀን ስብሰባ ተደርጓል።

በእለቱ ንግግር ካደረጉት ሰዎች መሃከል በቅድስት መንበር የህንድ አምባሳደር አቶ ሲቢ ጆርጅ አንደኛው ሲሆኑ፡እሳቸውም የጋንዲ መልእክት እና እሴቶች እስከዛሬም ድረስ በጣም ጠቃሚ መሆናቸውን ለቫቲካን ዜና ገልጸዋል፡፡አያይዘውም እ.ኤ.አ. በ2007 በብዙ ድምጽ ብልጫ ጋንዲ የተወለደበት እ.አ.አ.ጥቅምት 2 ቀንን የዓለም አቀፍ የጸረ-አመጽ ቀን በማለት የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ መሰየሙ የዚህ ታላቅ ሰው አስተምህሮና መርህ በዚህ ዘመንም አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል በማለት ተናግሯል።

በቅድስት መንበር የህንድ አምባሳደር እንዳሉት የጋንዲን መርህና እና የቆሙለት አላማ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስተምህሮ ጋር የተዛመደ ሲሆን በተለይም ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ጸረ-አመጽ እና ለአለም ሰላም ከሚለው አስተምህሮአቸው ጋር የተጣጣመ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ረገድ እሳቸው እና ሌሎች ብዙዎች በትምህርት ቤት መፃህፍት ላይ ከልጅነት ጀምሮ ያነበብዋቸውን የመሐትማ ጋንዲን መልእክት አንስቷል። ይህም የጋንዲ “ታሊስማ” ለዓለም ይባላል። ትርጉሙም ማንኛውም ሰው ውሳኔ ለመወሰን ጥርጣሬ ውስጥ ሲገባ፣ የሚወስነው ውሳኔ ደካሞችንና ድሆችን የሚያግዝ መሆኑን ያረጋገጠ ከሆነ ያሰው በዛ ውሳኔው መጽናት አለበት የሚል ነው።

በቅድስት መንበር የህንድ አምባሳደር እንዳሉት ቫሱዳይቫ ኩቱምባካም የተባለ “የጥንታዊው ሳንስክሪት የሂንዱ ሐረግ ”ማለትም“ ዓለም አንድ ቤተሰብ ናት ”የሚል መልእክት ያለው ሲሆን አምባሳደር ጆርጅ እንዳሉት ፣ እያንዳንዱ ግለሰብ ፣ በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው ቦታ ምንም ይሁን ምን ፣እያንዳንዱ ሰው አስፈላጊ ነው የሚል ነው፡፡ እኛ የምንወስነው ማንኛውም ውሳኔ በሕዝቡ ላይ በጎ ተጽዕኖ ሊኖረው ይገባልም በማለትም አስገንዝበዋል፡፡

02 October 2019, 17:45