ፈልግ

በአማዞን ሕገ ወጥ የደን ጭፍጨፋ፣ በአማዞን ሕገ ወጥ የደን ጭፍጨፋ፣ 

ካርዲናል ፓሮሊን፥ የደን መጥፋት የአካባቢያዊ፣ ማሕበራዊ እና የሥነ ምግባር ቀውስ መሆኑን አስታወቁ።

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን እ-አ-አ መስከረም 23 ቀን በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የደን ጥበቃን በተመለከተ ከፍተኛ ስብሰባ አካሂደዋል ፡፡

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መቅድም ገረመው - ቫቲካን

ቅድስት መንበር የደን መጥፋት አካባቢያዊ ችግር ብቻ ሳይሆን ማህበራዊና ከሁሉም በላይ ደግሞ ሥነምግባርን የሚመለከት ስለሆነ ዓለምአቀፋዊ  የደን ጥበቃ ለማድረግ ፈጣን ፣ አስቸኳይ እና ዘላቂ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርባለች፡፡

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን በሰኞ ዕለት እንዳስታወቁት “ደኖች ለመላው ዓለም እና በእርግጥም ለሰው ልጅ የወደፊት ዕጣ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ በጥብቅ እንገነዘባለን፡፡

በኒው ዮርክ በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባ ላይ “የደን ጥበቃን በተመለከተ ንግግር ሲያደረጉ ደኖችን መንከባከብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት የሚሰጠው እነጂ ችላ የሚባል አይደለም ካሉ በኋላም የደን ልማትን በተመለከተ ማህበረሰብን ማስተማር ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል።ከተሜነት በበዛበት በዚህ ዘመን ልንተካው የማንችለው ከደን የምናገኘው ጥቅም ማጣት ስለሚጎዳን በተባበረ ክንድ  ደኖችን መጠበቅ አለብን በማለት አሳስበዋል።

የተቀናጀ ሥነ-ምህዳር እና ልማት።

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን እንዳሉት “በአሁን ዘመን ትልቁ የሰው ልጆች ሥቃይ ደኖችን ከመጨፍጨፍና ከማጥፋት የሚነሳ ሲሆን ፣” ይህ ተፅእኖ በዋነኝነት የሚያጠቃው ኑሮአቸው ፣ ባህላዊ እና ማህበራዊ መዋቅሮቻቸውን  ደኖቻቸው ላይ ጥገኛ ያደረጉት ላይ ነው፡፡“የጋራ መኖርያችንን የሆነውን ደንን በመንከባከብ ፣ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን መንከባከብ አለብን” በማለት አጥብቀው ተናግሯል ፡፡

አያይዘውም በዋናነት የሚፈለገው ሥነ ምህዳራዊ እና ማህበራዊ ልማት ሲሆን ደኖችን ተፈጥሮአዊ ገጽታቸውን ጠብቀን ተንከባክበን ሀላፊነት በተሞላበት መልኩ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ማዋል ችለን በዋናነት በደኖች መጥፋት ምክንያተ ህይወታቸው ለተናጋባቸው ህይወታቸው ከመታደግ ባሻገር ለሰው ልጅ ሁሉ ጤናማ አኗኗር ዋስትና ይሆናል፡ለወደፊት ትውልድም ጤናማ አየር ማውረስ እንችላለን።

ደኖቻችንን በተመለከተ የሚደረግ ማንኛውንም ማሻሻያ በዋናነት ህይወታቸው ፣ባህላቸው እና ማህበራዊ አኗኗራቸው በቀትታ ከሚመለከታቸው በደኖቹ አካባቢ ከሚኖሩ ሰዎች ጋር በመወያየት መሆን አለበት።አያያዝ ለማሻሻል የሚደረገው ማንኛውም ውሳኔ መብቶቹ ፣ እሴቶቻቸው እና ህይወታቸው በጣም የሚጎዱትን ሙሉ እና ትርጉም ያለው ተሳትፎ ማካተት እንዳለበት አስረድተዋል ፡፡

ካርዲናል ፓሮሊን በቫቲካን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ስላሳወቁት የአማዞን መጪው ሲኖዶስ ጉባኤም ተናግሯል ፡፡ ይህ በዋናነት በአካባቢው እና በቤተክርስቲያኒቱ ሃዋርያዊ ጉዳዮችና በአርብቶ አደሩ ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልፀው በዚያ ለሚኖሩት የአገሬው ተወላጆች እና በተለይም በክልሉ እና በሰው ልጆች ላይ ተጽዕኖ ለሚፈጥሩ ሰብአዊ ፣ ስነ-ምህዳራዊ ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ብለዋል ፡፡

ድህነትን መዋጋት ደኖችን ለመከላከል ይረዳል ፡፡

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በማዳጋስካር የነበራቸው ጉብኝት በማስታወስ ማዳጋስካር ከ 2001 ዓ.ም. ጀምሮ 21 በመቶ የሚሆነውን ደኖችዋን ያጣች ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ  በዚሁ ጉብኝታቸው ደኖችን መንከባከብ እና የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን መንከባከብ አለብን በማለት ለባለስልጣናቱ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እነዚህ በደኖቹ አካባብ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከድህነት እንዲወጡና ለደን ጥበቃው አንዱ አካል እንዲሆኑ ለማድረግ ሥራ በመፍጠር ማገዝ እንደሚገባም ጭምር አበክረው ተናግረዋል።

በመጨረሻም የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን እንዳሉት ደኖችን ያለምንም መዘግየት በተባበረ ክንድ የተለያዩ ዘዴዎችን በመቀየስ በተቀናጀ መልኩ ድህነትን መዋጋትና  ለትጨቆኑት ወገኖቻችን ክብር መስጠት ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡

25 September 2019, 17:11