ፈልግ

በቫቲካን እና በራሻ ሥር የሚተዳደሩ የሕጻናት ሆስፒታሎች ተባብረው ለመሥራት ተስማሙ በቫቲካን እና በራሻ ሥር የሚተዳደሩ የሕጻናት ሆስፒታሎች ተባብረው ለመሥራት ተስማሙ 

በቫቲካን እና በራሻ ሥር የሚተዳደሩ የሕጻናት ሆስፒታሎች ተባብረው ለመሥራት ተስማሙ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 27/2011 ዓ.ም የራሻ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ከሆኑት ከቪላዲምር ፑቲን ጋር በቫቲካን ተገናኝተው በተለያዩ ወቅታዊ የዓለማችን ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸውን ቀድም ሲል መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን ከተደረጉት ውይይቶች መካከል አንዱ በቫቲካን ሥር የሚተዳደረው የሕጻናት የሕክማና መስጫ ጣቢያ የሆነው ባንቢኖ ጀዙ (ሕጻኑ ኢየሱስ) በመባል በሚታወቀው የሕጻንት ሆስፒታል መካከል እና በራሻ በሚገኙ ተመሳሳይ አገልግሎት ከሚሰጡ የሕጻናት የሕክምና መስጫ ጣቢያዎች ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት መፈረሙ ተገለጸ።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በስምምነቱ ወቅት እንደ ተገለጸው በቅድስት መንበር ሥር በሚተዳደረው ባንቢኖ ጀዙ በመባል በሚታወቀው የሕጻንት የሕክምና መስጫ ታቢያ እና በራሻ ተመሳሳይ አገልግሎት በሚሰጡ የሕጻናት ሆስፒታሎች መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ቀጣይነት ባለው መልኩ በሕክምናው ዘርፍ ላይ አዳዲስ ሳይንሳዊ የሆኑ ምርምሮችን በማደረግ ለሕጻናት የሚሰጠውን የጤና ክብካቤ አገልግሎት ማጠናከር የሚችል ስምምነት እንደ ሆነ ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት ተግልጹዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 27/2011 ዓ.ም የራሻ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ከሆኑት ከቪላዲምር ፑቲን ጋር በቫቲካን ተገናኝተው በተለያዩ ወቅታዊ የዓለማችን ሁኔታዎች ላይ ያደረጉትን ውይይት በተመለከተ የቫቲካን ፕሬስ ቢሮ ባወጣው መግለጫ አክሎ እንደ ገለጸው በቫቲካን ሥር በሚተዳደረው ባንቢኖ ጄዙ በመባል በሚታወቀው የሕጻንት ሆስፒታል እና በራሻ ተመሳሳይ አገልግሎት በሚሰጡ የሕጻናት የሕክምና መስጫ ጣቢያዎች መካከል ተባብረው ለመሥራት የሚያስችል “የጋራ የመግባቢያ ሰነድ” መፈረሙን ጨምሮ ገልጹዋል።

04 July 2019, 11:26