ፈልግ

የስደተኞ አስተዋጾ እና አሁን እየገጠማቸው ያለው ተግዳሮት የስደተኞ አስተዋጾ እና አሁን እየገጠማቸው ያለው ተግዳሮት 

የስደተኞ አስተዋጾ እና አሁን እየገጠማቸው ያለው ተግዳሮት

ዛሬ ሰኔ 13/2011 ዓ.ም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ የስደተኞች ቀን እያከበረ እንደ ሚገኝ ይታወቃል። ይህንን የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያከብረውን የሰደተኞ ቀን በተመለከተ በሰኔ 12/2011 ዓ.ም በሬዲያ ቫቲካን አዘጋጅነት ውይይት መደረጉ የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች እያጋጠማቸው ያለውን ከፍተኛ ተግዳሮት በተመለከተ እና የስደተኞች ጉዳይ የሚመለከታቸው ተቋማት እስካሁን በስደተኞች ዙሪያ ላይ ያከናወኑትን ተግባራት የገመገመ ውይይት ነበር።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“ስደተኞች እኛ ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ ያበረከቱት አስተዋጾ እና አሁን እየገጠማቸው ያለው ተግዳሮት” በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ውይይት ሲሆን ይህንን ስብሰባ ያዘጋጀው ደግሞ በቅድስት መንበር የአርጄንቲና ኤንባሲ ሲሆን በእዚህ ስብሰባ ላይ ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ዲፕሎማቶች፣ የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች እና የግብረ ሰናይ ተቋማት ተወካዮች ተሳታፊ እንደ ነበሩም ተገልጹዋል።

በእዚህ ስብሰባ ላይ ቅድስት መነበር ከሌሎች አገራት ጋር የምታደርገውን ኦፊሴላዊ ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠሩት ሊቀ ጳጳሳ ፖል ጋላገር ተሳታፊ እንደ ነበሩ የተገለጸ ሲሆን በእዚህ ስብሰባ ላይ ካሪታስ በመባል ለሚታወቀው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የእርዳታ መስጫ ድርጅት ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ የሚታወቁት ዶክተር ማርቲና ሌባስኪ ተካፋይ እንደ ነበሩም ተገልጹዋል።

Sher the Journey” (ጉዞውን ያጋሩ) በሚል አርእስት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን ከፍተኛ እንቅስቃሴ በበላይነት የሚመሩት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የእርዳታ መስጫ ድርጅት ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ የሚታወቁት ማርቲና ሌባስኪ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት ይህ “Sher the Journey” (ጉዞውን ያጋሩ) በሚል መሪ ቃል እርሳቸው የሚመሩት ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በአሜሪካ ከፍተኛ የሆነ ድጋፍ እያገኘ መምጣቱን ገልጸው እርሳቸው ይህንን እንቅስቃሴ በአሜሪካ በማድረግ ላይ በነበሩበት ወቅት በአንድ ስደተኛ ሶሪያዊ ሴት እና በአንድ አሜሪካዊ ሴት መካከል ተድርጎ የነበረውን ውይይት በዋቢነት የጠቀሱ ሲሆን አሜሪካዊ የሆነችው ሴት ስደተኞችን በተመለከተ በተለያዩ መንገዶች ይፋ የሚሆኑ አሐዛዊ መረጃዎች ያስፈራቸው እንደ ነበረ፣ ነገር ግን ከአንድ ሶሪያዊ ስደተኛ ሴት ጋር በነበራቸው ቆይታ ይህ ፍርሃታቸው መወገዱን እና በአሁኑ ወቅት ስደተኞችን በተመለከተ ያላቸው አስተሳሰብ አዎንታዊ እንደ ሆነ እኝህ አሜሪካዊ ሴት ገልጸውላቸው እንደ ነበረ አስታውሰዋል።

ፍራሃት እና ውይይት

“የአንዳንድ አገራት ሕዝቦች ስደተኞን በፍርሃት እና በጥርጣሬ ይመለከታሉ ይህንን ፍርሃት እና ጥርጣሬ እንዴት ማስወገድ ይቻላል?” ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ የሰጡት Sher the Journey” (ጉዞውን ያጋሩ) በሚል አርእስት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን ከፍተኛ እንቅስቃሴ በበላይነት የሚመሩት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የእርዳታ መስጫ ድርጅት ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ የሚታወቁት ዶክተር ማርቲና ሌባስኪ “እኔ እንደ ማስበው ፍራሃትን እና ጥርጣሬን ለማስወገድ ይቻል ዘንድ ዋነኛው እና አስፈላጊው ነገር ውይይት ማደረግ ነው፣ ይህ ደግሞ ብቸኛው ምንገድ ነው ለማለት ያስቸግረኛል፣ ሌላ መንገድ ሊኖር ይችላል። እኔ እንደማስበው የስደተኞችን መብት ማክበር እና አስፈላጊውን አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል ይህም ስደተኞች ክብር ያለው ህይወት እንዲኖራቸው ይረዳል” ብለዋል።

20 June 2019, 12:18