ፈልግ

በኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድረጅት የቅድስት መንበር (ቫቲካን) ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ቤርናርዲቶ አውዛ በኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድረጅት የቅድስት መንበር (ቫቲካን) ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ቤርናርዲቶ አውዛ  

ሊቀ ጳጳስ ቤርናርዲቶ « አውዛ ተቻችሎ የሚኖር እና አቃፊ የሆነ ባሕል መገንባት ይገባል » አሉ።

በኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድረጅት የቅድስት መንበር (ቫቲካን) ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ቤርናርዲቶ አውዛ በሰኔ 17/2011 ዓ.ም አሸባሪዎች በተለያዩ ሐይማኖት ተከታይ ማኅበርሰቦች ላይ በአሁኑ ወቅት እያደርሱት የሚገኘውን ጥቃት ለመከላከል ይቻል ዘንድ ተቻችሎ የመኖር እና አቃፊ የሆነ ባሕል ይፈጠር ዘንድ ለማድረግ ታስቦ በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ መካፈላቸው የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ የእመንት ተቋማት አማኞች ላይ እየደርሰ የሚገኘው ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ በመምጣቱ የተነሳ ተቻችሎ የሚኖር እና አቃፊ የሆነ የማኅበረሰብ ባሕል መገንባት ይገባል ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድረጅት የቅድስት መንበር (ቫቲካን) ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ቤርናርዲቶ አውዛ እንደ ገለጹት በእመንታቸው ብቻ የተነሳ ጥቃት እየደረሰባቸው የሚገኙ የማሕበረሰብ ክፍሎችን ከእዚህ ጥቃት መከላከል ይቻል ዘንድ ትዕግስት፣ ጽናት፣ ጥበብ፣ ድፍረትንና የተቀናጀ አመራር በመስተት በአሁኑ ወቅት በአሸባሪዎች አማካይነት በክርስቲያኖች ላይ እየተቃጣ የሚገኘውን ጥቃት ማስቀረት እንደ ሚቻል ቅድስት መንበር እንደ ምታምን የገለጹ ሲሆን በተለይም ደግሞ በሁሉም ሃይማኖቶች መካከል የመቻቻል መንፈስ እንዲኖር በማደረግ እና አቃፊ የሆነ ማኅበርሰብ በመፍጠር ችግሩን መቅረፍ እንደ ሚቻል ገልጸዋል።

"እኛ ሁላችንም የአጭርና የረጅም ጊዜ መፍትሄ አካሎች እንሆናለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት በኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድረጅት የቅድስት መንበር (ቫቲካን) ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ቤርናርዲቶ አውዛ በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ በአይሁድ፣ በእስልምና፣ በክርስትና እና በአጠቃላይ በሁሉ የእመንት ተቋማት ምዕመናን ላይ እየደረሰ የሚገኘው ጥቃት ይቆም ዘንድ ጥሪ ማቀረባቸው የተገለጸ ሲሆን በተለይም ደግሞ በቅርቡ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተል የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ላይ በባግላዲሽ የደርሰውን የአሸባሪዎች ጥቃት በዋቢነት የጠቀሱ ሲሆን ሥርዓተ አምልኮ የሚፈጸምባቸው ቦታዎች « ግዲያ የሚፈጸምባቸው ሥፋርዎች እየሆኑ መምጣታቸው » የጉዳዩን አሳሳቢነት እንደ ሚያሳይ ገልጹዋል።

እነደነዚህ ዓይነት ጥቃቶችን ማውገዝ በራሱ በቂ አለመሆኑን በመግለጽ ንግግራቸውን የቀጠሉት በኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድረጅት የቅድስት መንበር (ቫቲካን) ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ቤርናርዲቶ አውዛ « ምንግሥታት በአገራቸው ውስጥ የሚገኙትን ዜጎቻቸውን በእኩልነት የመጠበቅ ኃላፊነት እንደ ተጣለባቸው » የገለጹ ሲሆን የመቻችል በሕል ይጎልበት ዘንድ የበኩላቸውን ጥረት ማድረግ እንደ ሚገባቸው ጨምረው ገለጸዋል።

የህሊና እና ሃይማኖት ነጻነት

መቻቻችል የሰፈነበት እና አቃፊ የሆነ ማኅበርሰብ ለመገንባት ይችላ ዘንድ የህሊና እና የሐይማኖት ነጻነት በቅድሚያ መረጋገጥ እንደ ሚኖርበት የገለጹት በኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድረጅት የቅድስት መንበር (ቫቲካን) ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ቤርናርዲቶ አውዛ ያለመታደል ሆኖ በጣም ብዙ አገራት በብሔራዊ ደረጃ በሕገ-መንግሥታቸው ውስጥ ብሔራዊ ሐይማኖት እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎች የሐይማኖት ተቋማት ክልከላ እንደ ሚደረግባቸው የገለጹ ሲሆን በአንዳንድ አጋጣሚዎች በአገራቸው ውስጥ የሚገኙ በቁጥር አነስተኛ የሆነ የምነት ተከታዮች ላይ ጥቃት እንደ ሚቃጣ ጨምረው ገልጸዋል።

የፖለቲካ ማህበራዊና የሃይማኖት መሪዎች ኃላፊነት

የፖለቲካ ማህበራዊና የሃይማኖት መሪዎች እና ኃላፊዎች በማነኛውም የሐይማኖት ተቋማት ላይ የሚቃጣውን አደጋ ማውገዝ እንደ ሚጠበቅባቸው በኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድረጅት የቅድስት መንበር (ቫቲካን) ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ቤርናርዲቶ አውዛ በእዚህ ረገድ ጥቃት ፈጻሚ የሆነ የሐይማኖት ተቋማትን ብቻ ማወገዙ በራሱ በቂ እንዳልሆነ ገልጸው የሐይማኖት አስተምህሮዎችን ተገቢ ባለሆነ መልኩ በመተርጎም የራሳቸውን ፖሌቲካዊ፣ ማሕበራዊ እና ሐይማኖታዊ የሆኑ ርዕዮተ ዓለሞችን ለማራመድ በማሰብ ሕዝቡን ለጥላቻ እና ለግጭት የሚዳርጉ ግለሰቦች ሳይቀር ተጠያቂ ሊሆኑ እንደ ሚገባ ጨምረው ገልጸዋል።

አእምሮን እና ልብን ማስተማር

አእምሮን እና ልብን በእውቀት ብርሃን መሙላት እንደ ሚገባ የገለጹት በኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድረጅት የቅድስት መንበር (ቫቲካን) ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ቤርናርዲቶ አውዛ በተለያዩ ባሕሎች መካከል ውይይቶች እንዲደረጉ በማደርግ በተለይም ደግሞ ለወጣቶች አግባብ ያለው የሕነጻ ትምህርት በመስጠት፣ የትምህርት መስጫ ተቋምት፣ ተማሪዎች እና ኢንተርነቴን የመሳሰሉ የማሕበራዊ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት አካራሪነትን የሚያበረታቱ አስተምህሮዎችን እንዳያስተላልፉ ጥንቃቄ በማደረግ የመግሥት ተቋማት ኃላፊነታቸውን ይወጡ ዘንድ ጥሪ ካቀረቡ በኋላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

24 June 2019, 15:24