ፈልግ

ቅድስት መንበርን በመወከል የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ተወካይ የሆኑት የእኔታ አባ ፌርናንዶ ኪኪ አሬላኖ ቅድስት መንበርን በመወከል የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ተወካይ የሆኑት የእኔታ አባ ፌርናንዶ ኪኪ አሬላኖ  

ቅድስት መንበር ዘላቂ የግብርና ልማት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳሰበች።

በተባበሩት መንግሥታት ሥር የሚተዳደረው የአለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት በሰኔ 19/2011 ዓ.ም “ስደት፣ ግብርና እና የገጠር ልማት” በሚል መሪ ቃል ባካሄደው ጉባሄ ላይ ቅድስት መንበርን በመወከል የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ተወካይ የሆኑት የእኔታ አባ ፌርናንዶ ኪኪ አሬላኖ ተገኝተው በጉባሄው ላይ ንግግር ማደረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ዘላቂ የሆነ የግብርና ልማት እንዲኖር እና በገጠራማ አከባቢዎች የሚኖሩ ቤተሰቦች እንክብካቤ ይደረግላቸው ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ የሚስተዋለውን የስደተኞችን ፍለሰት፣ ረሃብ እና ድህነት ለመግታት ይቻል ዘንድ ዘላቂ የሆነ የግብርና ልማት ይኖር ዘንድ መሥራት እንደ ሚገባ የገለጹ ሲሆን ዘላቂ የሆነ ግብርና ልማት በቂ የሆነ የመሠረተ ልማት እንዲኖር ያደረጋል፣ አካባቢያዊ ሀብቶችን የሚያጠናክሩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ያበረታታል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለማቀፍ ደረጃ እየታየ የሚገኘውን ከፍተኛ እና መራራ የሆነ የስደተኞች ፍልሰት ዋናው መንስሄ ድህነት፣ ግጭት፣ ጦርነት እና የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው መዘዝ እና በተፈጥሮ አደጋዎች በመሆኑ የተነሳ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ይቻል ዘንድ የአለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የበኩሉን አዎንታዊ አስተዋጾ ያደርግ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጹዋል።

የአለም የምግብ እና የእርሻ ድረጅት የተመሰረተበት ዋነኛው ዓላማ ዘላቂ የሆነ የግብርና ልማት ለማምጣት እንደ ሆነ የገለጹት ቅድስት መንበርን በመወከል የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ተወካይ የሆኑት የእኔታ አባ ፌርናንዶ ኪኪ አሬላኖ ነገር ግን ከበርካታ አመታት በኋላ እንኳን ሳይቀር በተወሰነ መልኩ ለውጥ ብያስመዘግብም በአጠቃላይ ሲታይ ግን የታቀደለት ግብ ላይ አለመድረሱን ገልጸው አሁንም ቢሆን በርካታ የአለማችን ሕዝቦች በረሃብ እየተሰቃዩ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

ቅድስት መንበርን በመወከል የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ተወካይ የሆኑት የእኔታ አባ ፌርናንዶ ኪኪ አሬላኖ ጨምረው እንደ ገለጹት በግብርና ዘርፉ ውስጥ ወጣት ሥራ ፈጣሪነትን ለማጎልበት የሚረዱ ፖሊሲዎችን ማራመድ አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ መሬት የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው፣ የመሬት ባለቤትነት እንዲረጋገጥላቸው እና የብድር አገልግሎት ለአካባቢ ገበያዎች ተደራሽ ማድረግ እንደ ሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

27 June 2019, 14:08