ፈልግ

የምዕራብ አፍሪካ የቤተክርስቲያን መሪዎች የአሸባሪዎችን ጥቃት ለመከላከል በጋር መሥራት ይገባል አሉ የምዕራብ አፍሪካ የቤተክርስቲያን መሪዎች የአሸባሪዎችን ጥቃት ለመከላከል በጋር መሥራት ይገባል አሉ 

የምዕራብ አፍሪካ የቤተክርስቲያን መሪዎች የአሸባሪዎችን ጥቃት ለመከላከል በጋር መሥራት ይገባል አሉ

የምዕራብ አፍሪካ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባሄ ተወካዮች በአሁኑ ወቅት በቀጠናው በአሸባሪዎች በቤተክርስትያን ላይ እየተቃጣ የሚገኘውን የሽብር ጥቃት ለመከላከል እና ሰላም እና አንድነት በክልሉ ይሰፍን ዘንድ ተቀናጅተው እንደ ሚሰሩ ገለጹ።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የምዕራብ አፍሪካ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪዎች በክልሉ በሚገኙ የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት እና ማህበረሰቦች ላይ የሚፈጸመውን ግፍ ለማስቆም እና ሰላማዊ ማህበረሰብ ለመገንባት ይቻል ዘንድ ሁሉም የማኅበርሰቡ አባላት በሂደቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጹዋል። በቀጠናው ከሚገኙ አገራት ውስጥ በተለይም በቡርኪና ፋሶ እና በኒጀር በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ በቅርቡ በአሸባሪዎች ጥቃት መፈጸሙ የሚታወስ ሲሆን በዚህ በአሸባሪዎች በተቃጣው ጥቃት የተነሳ በርካታ ሰዎች መገደላቸው፣ አብያተ ክርስቲያናት እና እንዲሁም የክርስትና እምነት መገለጫ የሆኑ ምልክቶች ያሉባቸው ስፍራዎች ላይ ሳይቀር ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል።

ባለፈው ሳምንት ብቻ አንድ ካህንን ጨምሮ ቢያንስ 10 ሰዎች በቡርኪና ፋሶ ባልታወቁ ታጣቂ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን ቡርኪና ፋሶን ከኒጀር ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው በኒያሜይ አገረ ስብከት ውስጥ በሚገኘው አንድ ቁምስና ላይ በተከፈተው ጥቃት አንድ ካህን የመቁሰል አደጋ እንደ ደረሰባቸው መዘገባችን ይታወሳል።

የምዕራብ አፍሪካ የካቶሊክ ቤተክርስትያን ጳጳሳት ጉባሄ ሕብረት አባላት የቀጠናቸውን ሁኔታ በተመለከተ “በአንድነት እና በጋር የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ማሸነፍ እና ሕዝቡ ድል አድራጊ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል” በሚል መሪ ቃል መወያየታቸው የገለጸ ሲሆን ይህ ስብሰባ በቡሪክና ፋሶ ዋና ከተማ ከባለፈው ግንቦት 04-10/2011 ዓ.ም ተካሂዶ እንደ ነበረም ከፍስራው ለቫቲካን ከደረሰው ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ጌታ እዚህ ከእኛ ጋር ስላለ እናሸንፋለን” የሚል መግለጫ ካወጡ በኋላ ጉባሄው መጠናቀቁ ተገልጹዋል።

17 May 2019, 18:23