ፈልግ

ቤተሰብ  ፍቅር የምንማርበት የመጀመሪያው ትምህርት ቤት ነው ቤተሰብ ፍቅር የምንማርበት የመጀመሪያው ትምህርት ቤት ነው 

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚወጡ ፖሊሲዎች ቤተሰብን ማዕከል ያደርጉ ሊሆኑ ይገባል

ቅድስት መንበርን በመወከል በጄኔቫ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጆቶች ቋሚ ተወካይ ይሆኑት ሊቀ ጳጳስ ኢቫን ጁርኮቪቺ በጄኔቫ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅ አዘጋጅነት በግንቦት 06/2011 ዓ.ም በጄኔቫ በተካሄደው 15ኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ቀን ላይ በተደረገው ጉባሄ ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት የቤተሰብን እሴት ማስተዋወቅ እና ለቤተሰብ ጥበቃ ማድረግ የገባል ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መበራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን።

ቅድስት መንበር ቤተሰብን በተመለከተ ቤተሰብ “መሰረታዊ እና የማኅበርሰብ ዋና አካል” መሆኑን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይህ አቋም እውቅና እንዲሰጠው” ጥሪ ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን ለቤተሰብ የሚደርገው ማነኛውም ዓይነት ጥበቃ እና እንክብካቤ ለዓለም አቀፉ ማኅበርሰቡ የጋራ ተጠቃሚነት መሰረታዊ የሆነ ነገር ነው ብለዋል።

“ቤተሰብ ከሁሉም በላይ ሰው መሆን እንዴት እንደ ሚቻል እና በተጨማሪም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ጳውሎስ 6ኛ አዘውትረው እንደ ሚናገሩት ፍቅር የምንማርበት የመጀመሪያው ትምህርት ቤት ነው” በማለት በጉባሄው ላይ የተናገሩት በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ተወካይ ሊቀ ጳጳስ ኢቫን ጁርኮቪቺ በጄኔቫ በዚህ ምክንያት ለቤተሰብ እንክብካቤ ማድረግ እና በቤተሰብ ውስጥ የሚገኙትን መልካም እሴቶች ለዓለም ማስተዋወቅ ይገባል ብለዋል። በጄኔቫ የተባበሩ ተመንግሥታት ድርጅ የቅድስት መንበር ቋሚ ተወካይ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ኢቫን ጁርኮቪቺ በጄኔቫ ይህንን ከዚህ በላይ ያለውን ንግግር ያደርጉት በግንቦት 6/2011 ዓ.ም በጄኔቫ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት 15ኛውን ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ቀን አስመልክቶ ባዘጋጀው ጉባሄ ላይ ተጋብዥ ለነበሩ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች ባደረጉት ንግግር እንደ ነበረም ታያይዞ የደርሰን ዜና ያስረዳል።

ሰላማዊ ለሆነ ቀጣይነት ላለው ሥልጣኔ ቤተሰብ አስፈላጊ ነው!

ሊቀ ጳጳስ ኢቫን ጁርኮቪቺ በጄኔቫ ንግግራቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት "ዛሬ በትውልዶች መካከል ለሚደረገው ፍሬያማ የሆነ ሽግግር እና ለቤተሰብ እሴቶች እምብዛም ትኩረት አልተሰጠም” በማለት መናገራቸው የተገለጸ ሲሆን ግለሰባዊነት ባመጣው የተዛባ አስተሳሰብ የተነሳ ‘ቤተሰብ ማለት የግለሰቦች ስብስብ ነው፣ ይህም የማኅበርሰቡ የመጀመሪያው ማህበራዊ አሃድ ነው’” የሚል የተዛባ አስተሳሰብ እያራመዱ መሆኑን ገልጸዋል።

"ቤተሰብ ሁልጊዜ የህብረተሰብ መሰረታዊ ክፍል እና ዋና መሰረታዊ የትምህርት መስጫ ቦታ እንደ ሆነ” የገለጹት ሊቀ ጳጳስ ኢቫን ጁርኮቪቺ በጄኔቫ ቤተሰብ “አሁን ሰላማዊ የሆነ ስልጣኔ ለመገንባት በሚደርገው ጥረት ውስጥ ያጋጠመውን ከፍተኛ ተግዳሮት ለመፍታት ቤተሰብ ወሳኝ ሚና ሊጫወት እንደ ሚችል” ጨምረው ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ቤተሰቦች ለቤተሰብ ምስረታ መሰረት የሆኑት እሴቶችን ተግባራዊ በሆነ መልኩ በመመስከር ዛሬ ባለው ዓለማችን ውስጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነውን የእውነተኛ የወንድማማችነት መንፈስ ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቤተሰብ ከፍተኛ የሆነ ሚና እንደ ሚጫወት ጨምረው ገልጸዋል።

በትውልድ መካከል ያለውን ትስስር ማሳሳት

በጄኔቫ የተባበሩ ተመንግሥታት ድርጅ የቅድስት መንበር ቋሚ ተወካይ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ኢቫን ጁርኮቪቺ  ንግግራቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት “እንደ ኢኮኖሚ ውድቀት እና ድህነት ያሉ ከባድ ችግሮች ባለፉት ዘመናት ከነበረው ትውልድ ጋር የነበረውን ትስስር ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማስቀጠል አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እየፈጠሩ መሆኑን” ገልጸው “በቤተሰብ መካከል ትስስር አለመኖሩ እና ከራስ ወዳድነት መንፈስ ነጻ በሆነ መልኩ ኅብረት የመፍጠር እና ይቅርታ የማድረግ መንፈስ እየቀዘቀዘ በመምጣቱ የተነሳ የቤተሰብ ሁኔታ አስገራሚ ወደ ሆነ ሁኔታ ሊያመራ እንደ ሚችል ያላቸውን ስጋት ገለጸዋል።

“በቤተሰብ ውስጥ ያለው ትስስር እየተዳከመ እና እየላላ በሚመጣበት ወቅት በሚልዮን የሚቆጠሩ ህፃናት እና ወጣቶች ተገቢና አስፈላጊ የሆነ የሕይወት መመሪያ ሳያገኙ ይቀራሉ፣ በዚህም የተነሳ ትምህርት የማቋረጥ፣ ለአስገዳጅ የጉልበት ሥራ ብዝበዛ እና የወሲብ ጥቃት ተጋላጭ በመሆን ከእነዚህ ጋር ተያያዥነት ላላቸው እና ለተሳሰሩ አደጋዎች ይበልጥ ተጋላጭ ሆነዋል” ብለዋል።

እ.አ.አ. በ2014 እና በ2015 ዓ.ም ቤተሰብ ላይ መሰረቱን አድርጎ የነበረው ሲኖዶስ ቤተሰብ ዛሬ ባለው ዓለማችን ውስጥ ማዕከላዊ በሆነ መልኩ “ሰብዓዊነትን የምንማርበት ትምሕርት ቤት” በመሆኑ የተነሳ በጣም አስፈላጊ መሆኑን በአጽኖት መግለጹን አስረድተዋል። በእርግጥ ጥንካሬን ፣ በደስታ ተግባራችንን ማከናወን፣ የወንድማማችነት ፍቅርን፣ ደግነትን እና ይቅር ባይነትን ከሁሉም በላይ ደግሞ ሕይወታችንን ለሌልች አገልግሎት ማዋል የመሳሰሉ ነገሮችን በእርግጠኛነት የምንማረው ከቤተሰብ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። ስለሆነም ለማኅበረሰቡ መሠረታዊ የሆነ ሚና ቤተሰብ መጫወት እንዲችል ሰዎች ትዳር እንዲመሰርቱ እና ከዚያም ቤተሰብ መፍጠር ይችሉ ዘንድ ማበረታታት ያስፈልጋል ብለዋል።

በመጨረሻም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕፃናት መብቶች በተመለከተ ከሰላሳ አመት በፊት የተደረጉ ስምምነቶችን እና እንዲሁም ከ25 አመታት በፊት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲከበር የተደነገገው ዓለም አቀፍ የቤተስብ ቀን ኢዩበሊዩ በሚከበርበት በአሁኑ ወቅት ቤተሰብን ማዕከል ያደረጉ እና ቤተሰብን የሚያጠናክሩ ፖሊሲዎች እና እቅዶች ማውጣት ተገቢ መሆኑን  የገለጹት በጄኔቫ የተባበሩ ተመንግሥታት ድርጅ የቅድስት መንበር ቋሚ ተወካይ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ኢቫን ጁርኮቪቺ በማነኛውም ሁኔታ የሚወጡት ዓለም አቀፍ እቅዶች ቤተሰብን ማዕከል ያደረጉ መሆን ይኖርባቸዋል ካሉ በኋላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 

13 May 2019, 15:50