ፈልግ

ሊቀ ጳጳስ ቤርናርዲቶ አውዛ በተባበሩት መንግሥታት ድረጅት የቅድስት መንበር (ቫቲካን) ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ ቤርናርዲቶ አውዛ በተባበሩት መንግሥታት ድረጅት የቅድስት መንበር (ቫቲካን) ቋሚ ታዛቢ  

ቅድስት መንበር “የሥነ ፆታ ርዕዮተ ዓለም በሰብአዊነት ላይ ከፍተኛ አደጋ እያስከተለ ይገኛል!”

በተባበሩት መንግሥታት ድረጅት የቅድስት መንበር (ቫቲካን) ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ቤርናርዲቶ አውዛ በመጋቢት 12/2011 ዓ.ም በተባበሩት መንግሥታ ድርጅት ተገኝተው ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት “በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በከፍተኛ ደረጃ እየተካሄዱ የሚገኙት የሥነ ፆታ ርዕዮተ ዓለም ሰብአዊነት ወደ ኋላ የሚመልስ ጉዳይ በመሆኑ እንዳሳሰባቸው ገልጸው ይህም በሰብአዊነት ላይ አደጋን የሚደቅን አሳሳቢ ጉዳይ” መሆኑን ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በመጋቢት 12/2011 ዓ.ም በኒውዮርክ በተባበሩት መንግሥት ደርጅት በተካሄደው ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደርጉት በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መነበር (ቫቲካን) ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ቤርናርዲቶ አውዛ በወቅቱ ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ እየተካሄደ ያለው የሥነ ፆታ ርዕዮተ ዓለም ግራ መጋባትን እየፈጠረ ያለ ክስተት እየሆነ መምጣቱ እንደ ሚያሳስባቸው አጽኖት ሰጥተው ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት "የጾታ እኩልነት እና የጾታ ርዕዮተ ዓለም: ለሴቶችንና ለልጃገረዶችን ጥበቃ ማድረግ" በሚል ዓላማ እየተካሄደ በሚገኘው ስብሰባ ላይ በዓለም ላይ ሴቶች የሚጫወቱት አዎንታዊ ሚና እንዲጨምር እና ሴቶች በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ከፍ ይል ዘንድ በተጨማሪም ሴቶች ማህበራዊ የሆኑ መብቶቻቸው እና ለትምህርት ያላቸው ተደራሽነት ይጨምር ዘንድ የሚያስችል ስብሰባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በአንድ ወቅት "ሴት መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ በግልጽ እንዲታወቅ የሚያደርግ ክሮሞሶም የሚባል ንጥረ ነገር በሰውነታችው ውስጥ ይገኝ ነበር” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ሊቀ ጳጳስ በርናርዲቶ አውሳ ዛሬ ይህ ግልጽነት ከጾታ የተላቀቀው ግላዊ ማንነት መኖሩን በሰፊው በሚገልጽ የጾታ ርዕዮተ ዓለም ፍልስፍና የተነሳ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

በተፈጥሮ የተገኘውን የፆታ ማንነት በስነ-ጾታ ርዕዮተ ዓለም ምክንያት ጾታን መቀየር "በህግ፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በጤና፣ በፀጥታ፣ በስፖርት፣ በቋንቋና ባህል ላይ ብቻ ሳይሆን” ነገር ግን በተጨማሪም በሥነ-ሰብዕ (Anthropology) በሰብአዊ ክብር፣ በሰብአዊ መብት፣ በጋብቻ እና በቤተሰብ፣ በእናቶች እና በአባቶች ሚና ላይ፣ እንዲሁም በሴቶች እና በወንዶች ሁኔታ ላይ፣ በተጨማሪም በተለይም ደግሞ በልጆች የወደ ፊት እጣ ፈንታ ላይ ከፍተኛ የሆነ አደጋ የሚደቅን ነው” ብለዋል። በአንጻሩ ማነኛውም ሰው በራሱ ተፈጥሮአዊ ጾታ ሊወከል እንደ ሚገባው አጽኖት ሰጥተው የገለጹት ሊቀ ጳጳስ በርናርዲቶ አውዛ በሥነ-ፆታ ርዕዮተ ዓለም ምክንያት በአሁኑ ጊዜ በሰፊው እየተንሸራሸሩ የሚገኙት ሐሳቦች በግለሰቦች እና በማህበረሰቡ ላይ ሳይቀር ከፍተኛ አደጋ የሚደቅን በመሆኑ የተነሳ ሊታሰብበት ይገባል ብለዋል።

ሊቀ ጳጳስ በርናርዲቶ አውዛ በንግግራቸው ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በላቲን ቋንቋ “Laudato sì'” በአማርኛው “ውዳሴ ላንተ ይሁን!”  በሚል አርእስት ከዚህ ቀደም ለንባብ አብቅተው የነበረውን ሐዋርያዊ መልእክት በዋቢነት በመጠቀም በዚሁ ሐዋርያዊ መልእክት በቁጥር 155 ላይ የተጠቀሰውን በመግለጽ የሚከተለውን ብለዋል . . .

“የሰው ልጅ እንደ ፈለገ ሊለውጠው የማይችለው የተፈጥሮ ስጦታ አለው። ሰውነታችን ራሱ ከአከባቢና ከሌሎች ሕያዋን ፍጥረታት ጋር በቀጥታ የተቆራኘ እና ግንኙነት ያለው ነው። ሰውነታችንን እንደ የእግዚአብሔር ስጦታ አድርገን መቀበል መላው ዓለም የአብ ስጦታና የጋራ ቤታችን አድርገን በደስታ ለመቀበል ውሳኝ ነው። በገዛ ሰውነታችን ላይ ፍጹም የሆነ ሥልጣን አለን ብለን ማሰብ ግን በተፈጥሮም ላይ ስልጣን አለን ብለን ወደ ማሰብ ይመራናል። ሰውነታችንን እንዴት እንደ ምንቀበል፣ እንደምንከባከበው እና ሙሉ ትርጉሙን እንደምናክብር ማወቅ ለማነኛውም እውነተኛ ሰብአዊ ስነ-ምህዳር መሰረታዊ የሆነ ነገር ነው። እነደዚሁም ራሴን ከሌላው የተለየው አድርጌ ለማወቅ ከፈለኩኝ እንደ ተባዕት እና እንደ እንስት ለራስ ሰውነት ዋጋ መስጠት ያስፈልጋል። በዚህ ዓይነት የሌላውን ወንድ ወይም ሴት ልዩ ስጦታዎችና የፈጣሪውን የእግዚኣብሔርን ሥራ በደስታ ለመቀበልና የጋራ ብልጽጋናን ለመቀዳጀት እንችላለን።

22 March 2019, 14:37