ፈልግ

የቫቲካን ሬዲዮ አገልግሎቱን በይፋ የጀመረው የዛሬ 88 አመት ነበር።

በኢጣሊያ መንግሥት እና በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያ መካከል በወቅቱ የነበሩትን አለመግባባቶች ለመፍታት በርካታ ተከታታይ የሆኑ ውይይቶች ከተደርጉ በኋላ አለመግባባቶችን በማስወገድ ዘላቂ መፍትሄ ያስገኘው የላቴራን ስምምነት በመባል የሚታወቀው ስምምነት በጣሊያን እና በቫቲካን መካከል በየካቲት 4/1921 ዓ. ም. የዛሬ 90 ዓመት ገደማ ማለት ነው፣ መፈረሙ ይታወሳል።

በጊዜው በኢጣሊያ መንግሥት እና በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያ መካከል የተካሄዱትን ውይይቶች የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በመወከል ጉዳዩን በጥብቅና ይዘው የነበሩት አቶ ፍራንችስኮ ፓቸሊ የተባሉ፣ ምሁር፣ የሕግ አዋቂ፣ የዩኒቨርሲቲ መምሕር፣ ታዋቂ ተደራዳሪ የነበሩት እና በቀድሞ ስማቸው ኤውጀኒዮ ፓቸሊ በመባል በመባል የሚታወቁ እና በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት የፒዮስ 12ኛ ታላቅ ወንድም ነበሩ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ይህ ስምምነት በየካቲት 4/1921 ዓ. ም. የዛሬ 90 ዓመት ገደማ ማለት ነው፣ ከተፈረመ ከአንድ ዓመት ገደማ በኋላ በየካቲት 05/1923 ዓ.ም የዛሬ 88 ዓመት ገደማ ማለት ነው፣ በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን 259ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ፒዮስ 11ኛ ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን “የቫቲካን ሬዲዮ ጣቢያን” በይፋ መርቀው ማስጀመራቸው የሚታወስ ሲሆን ይህ የሬዲዮ ጣቢያ አገልግሎት ላይ እንዲውል በቴክኖሎጂው መስክ ከፍተኛ አስተዋጾ አድርገው የነበሩት ደግሞ የመጀመሪያዎቹ የሬዲዮ ሞገድ ፈልሳፊ ከሚባሉ ሰዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት አቶ ጉሌሊሞ ማርኮኒ የሚባሉ ሰው እንደ ነበሩ ከታሪክ መዝገብ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን፣ ይህንን በወቅቱ አዲስ የነበረውን የሬዲዮ ማሰራጫ ተክኖሎጂ ሞገድ ተጠቅመው በወቅቱ የነበሩት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 11ኛ በቀጥታ መስማር ላይ ድምጻቸውን እና አስምህሮዎቻቸውን እስከ ዓለም ዳርቻ በሬዲዮ እንዲደርስ ያደርጉ በታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሆኑ አስችሉዋቸዋል።

13 February 2019, 14:34