ፈልግ

የቅድስት መንበር ቀዳሚ ተልዕኮ ለሰው ልጅ ጥበቃን ማድረግ እንደሆነ ተገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በቅድስት መንበር እና በቫቲካን ከተማ መካከል ያለውን አዲስ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ለማገናዘብ በሚል ዓላማ ቫቲካን እና ከፍተኛ የሕገ ቀኖና ትምህርት ቤት በጋራ ሆነው ያዘጋጁትን ስብስባ የተካፈሉት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን፣ የቅድስት መንበር ቀዳሚ ተልዕኮ ለሰው ልጅ ጥበቃን ማድረግ እንደሆነ አስረድተዋል።  ጉባኤው የተዘጋጀው ከ90 ዓመት በመት በፊት ማለትም በየካቲት 4 ቀን 1921 ዓ. ም. የተፈረመውን የላቴራን ውል ስምምነት ምክንያት እንደሆነ ከቫቲካን የዜና አገልግሎት የደረሰን ዘገባ አመልክቷል።

የዘመናችን ዋና ፈተና በምድራችን ሰላምን ማስፈን ነው ያሉት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን፣ ቅድስት መንበር ከዚህ በፊትም ስታደርግ እንደቆየችው ሁሉ፣ ሰላም የነገሠበትን ማሕበረሰብ ለመገንባት የሚያግዝ በመሆኑ፣ ሰብዓዊ ክብር ለማስጠበቅ ብላ የምታበረክተውን ጥረት የምትቀጥልበት መሆኑን አረጋግጠዋል።

የቅድስት መንበር አዎንታዊ ገለልተኛነት፣

ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ለስብሰባው ተካፋዮች የላቴራን ውል ስምምነት ምንጭ በማስረዳት ባቀረቡት የማጠቃለያ ንግግራቸው እንደገለጹት፣ ቅድስት መንበር ሰብዓዊ ክብር መጠበቅ እንዳለበት የሚያሳስቡ መልዕክቶችን ስታስተላልፍ የቆየችው ጥረት ዘመናትን ያስቆጠረ እንደሆነ አስረድተው ዛሬም ቢሆን ወደ ፊት ቅድስት መንበር የምትጠቀምበትን የአዎንታዊ ገለልተኛነትን መንገድ በመከተል ሰባዓዊ ክብርን ለማስጠበቅ የምታበረክተውን እገዛ እንደምትቀጥልበት እና ይህንን ለማሳደግ ከተለያዩ መንግሥታት ጋር ውይይት በማድረግ ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል።

የጋራ ውይይትን እና መደማመጥ ያለበት የረጅም ጊዜ ታሪክ ነው፣

በሮም ከተማ ከሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች ተጋብዘው ስብሰባውን የተካፈሉት የሕግ ባለሞያዎች እና የታሪክ አጥኚዎች በጋራ ሆነው የቫቲካን መንግሥት የሚከተላቸውን አዳዲስ የአውሮጳ መንግሥታት እና የዓለም መንግሥታት ደንቦችን መመሪያዎችን በዝርዝር የተመልከቱ ሲሆን ከጳጳሳዊ ምክር ቤት እና ከላቴራን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ የተወጣጡ ባለሞያዎችም የበኩላቸውን አስተያየት እና የጥናት ውጤት አቅርበዋል።

የላቴራን ስምምነት እስካሁን ጠቃሚ ሆኖ ቆይቷል፣

የቫቲካን መንግሥት፣ ከፍተኛ የሕገ ቀኖና ትምህርት ቤት ዋና ዳይረክተር እና የቫቲካን መንግሥት ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት የሆኑት አቶ ጁሰፔ ዳላ ቶሬ እንደገለጹት በኢጣሊያ በቤተክርስቲያ እና በመንግሥት መካከል ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት ለማስወገድ በየካቲት 4 ቀን 1921 ዓ. ም. የተፈረመውን የላቴራን ስምምነት፣ በሁለቱ መንግሥታት መካከል የተፈጠረውን ተፈጣሮ የነበረውን ችግር በማስወገድ እስከ ዛሬ ዘላቂ መፍትሄ ሆኖ ዘልቋል ብለዋል። 

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
09 February 2019, 15:49