ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የአብያተ ክርስቲያናት ውህደት ምክር ቤት ጋር   ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የአብያተ ክርስቲያናት ውህደት ምክር ቤት ጋር  

በሐይማኖት ተቋማት መካከል የጋራ ውይይት መካሄዱ ተገለጸ።

ሁለቱ ጽሕፈት ቤቶች በመካከላቸው ያለው ትብብር እያደገ መምጣቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸው በጋራ ሆነው ለማከናወን የገቡትን ቃል በማደስ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አረጋግጠዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በቫቲካን ከተማ፣ በሐይማኖች መካከል የሚደረገውን ውይይት በሚከታተል ጳጳሳዊ ምክር ቤት አባላት እና የአብያተ ክርስቲያናትን ውህደት በሚከታተል ምክር ቤት አባላት መካከል የጋራ ውይይት መካሄዱ ታውቋል። ከጥር 3 ቀን ጀምሮ ሲካሄድ የሰነበተው የሁለቱም ምክር ቤቶች የጋራ ውይይት፣ ምክር ቤቶቹ በሕይማኖት ተቋማት መካከል የሚደረጉ ውይይቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተስማምተዋል። በውይይታቸው መካከል ባለፈው የጎርጎሮሳዊያኑ 2018 ዓ. ም. በጋራ አገልግሎቶች መካከል የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ መልዕክት መለዋወጣቸው ታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ ምክር ቤቶቹ በተጀመረው አዲሱ የጎርጎሮሳዊያኑ 2019 ዓ. ም. ሊተገበሩ የታቀዱትን የሥራ ድርሻዎቻቸውንም መከፋፈላቸው ታውቋል። ሁለቱ ምክር ቤቶች እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር በ1977 ዓ. ም. ያጸደቁትንና “ትምህርት ለሰላም” የሚለውን የጋራ ሰንድ በድጋሚ መመልከታቸው ታውቋል። ይህን የጋራ ሰነድን መሠረት በማድረግ ጽሕፈት ቤቶቹ ከጎርጎሮሳዊያኑ 1977 ዓ. ም. ወዲህ በርካታ የአብያተ ክርስቲያናት ፕሮጀክቶችን በጋራ ሲያከናውኑ መቆየታቸው ይታወቃል።

ሁለቱ ጽሕፈት ቤቶች በመካከላቸው ያለው ትብብር እያደገ መምጣቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸው በጋራ ሆነው ለማከናወን የገቡትን ቃል በማደስ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አረጋግጠዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!

 

14 January 2019, 14:20