ፈልግ

“የምህረት እናት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የሕክምና መስጫ ማዕከል “የምህረት እናት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የሕክምና መስጫ ማዕከል  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለድሆች አገልግሎት የሚሰጥ የሕክምና መስጫ ጣቢያ ያፋ እንዲሆን አደረጉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 12/2011 ዓ.ም በቫቲካን ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለድሆች እና ከተለያዩ ሀገራት ለሚመጡ መንፈሳዊ ነጋዲያን አገልግሎት የሚሰጥ የሕክምና መስጫ ጣቢያ ይፋ ማድረጋቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህ “የምህረት እናት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የሕክምና መስጫ ማዕከል የመጀመርያ ደረጃ እርዳታን ጨምሮ የተለያዩ የሕክምና አገልግሎቶችን ለድሆች፣ ለመንፈሳዊ ነጋዲያን እና መጠልያ ለሌላቸው ሰዎች አገልግሎት እንደ ሚሰጥ ለመረዳት ተችሉዋል።
የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን “የምሕረት እናት” የሚል መጠርያ የተሰጠውን የሕክምና መስጫ ጣቢያ ለሆች፣ ለመንፈሳዊ ነጋዲያን እና መጠልያ ለሌላቸው ሰዎች አገልግሎት ይውል ዘንድ ይፋ ያደርጉት የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ እንደ ሆነም ጨምሮ ተገልጹዋል። ይህ “የምህረት እናት” በመባል የሚጠረው እና በቅርቡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያፋ ያደርጉት የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋም፣ ከሚሰጠው የጤና ክብካቤ አገልግሎት በተጓዳኝ ድሃ ለሆኑ የማኅበርሰብ ክፍሎች የሰውነት መታጠቢያ እና የጸጉር እና የጺም መላጨት አገልግሎት እንደ ሚሰጥም ተገልጹዋል።
ይህ “የምሕረት እናት” በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የጤና መስጫ ተቋም ለህመምተኞች ሙሉ የሕክምና ምርመራዎችን ማድረግ ያስችለው ዘንድ በቂ የሚባሉ የሕክምና መስጫ ቁሳቁሶች የተሟሉለት እንደ ሆነም ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በሳምንት ሦስቴ ዘወትር ሰኞ፣ ሐሙስ እና ቅዳሜ እለት አገልግሎት እንደ ሚሰጥ ለመረዳት ተችሉዋል።
የጤና ክብካቤ አገልግሎቱ የሚሰጠው በጎ ፈቃደኞች በሆኑ የሕክማና ባለሙያዎች፣ እስፔሻሊስቶች እና የጤና ባለሙያዎች አማካይነት እንደ ሆነ ለማረዳት የተቻለ ሲሆን በተጨማሪም በሮም ከተማ ውስጥ የሚገኘው ቶር ቬርጋታ ዩኒቬርሲቲ፣ የጣሊያን የጤና ክብካቤ መስጫ ማኅበር እና የጣሊያን ፖዲያትሪስት ማኅበር በጋራ የሚያከናውኑት ሕክምና እንደ ሚሆንም ከደረሰን ዘገብ ለመረዳት ተችሉዋል።
 

Photogallery

“የምህረት እናት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የሕክምና መስጫ ማዕከል
24 December 2018, 16:37