ፈልግ

ካ. ፔትሮ ፓሮሊን ካ. ፔትሮ ፓሮሊን  

ካ. ፔትሮ ፓሮሊን “የአየር ንበረት ለውጥ ከሰብዓዊ መብት ተለይቶ መታየት የለበትም”

በአሁኑ ወቅት በፖላንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያዘጋጀወ የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ በመካሄድ ላይ የገኛል። በዚህ ካንፈረንስ ላይ ቅድስት መንበርን በመወከለ የተገኙት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በኮነፈረንሱ ማብቂያ ላይ አጽኖት ሰጥተው እንደ ተናገሩት ምድራችን እና ተግላጭ የሆኑ የዓለማችን ሕዝቦች እያሰሙ የሚገኙትን ጩኸት ማዳመጥ ይገባል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በንግግራቸው ወቅት ጨምረው እንደ ግለጹት እ.አ.አ በ2015 ዓ.ም በፈረንሳይ ዋና ከተማ የዓለም የአየር ነበረት ለውጥን አስመልክቶ የተደረጉ ስምምነቶችን በፊርማቸው ያጸደቁትን የዓለማችን ሀገራት አመስግነው ይህም ከ 2 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በታች አማካይ የሙቀት መጠን መቀነስን ግብ አድርጎ የተነሳ እና ያካተተ ስምምነት መሆኑን ጨምረው ገለጸዋል። ነገር ግን ይህ ስምምነት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ የሚያስፈልገውን አጣዳፊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች መደረግ አለባቸው፣ ይህንን ስምምነት በበቂ ሁኔታ ለማስፈጸም እና አሁን በዓለማችን ላይ በመታየት ላይ ያለውን ከፍተኛ አደጋ ለመቅረፍ የምያስችል ሁኔታ እንዳልሆነ በንግግራቸው ያሳሰቡት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ይህንን ሐሳባቸውን እና የቫቲካን የአቋም መግለጫ የሆነውን መልእክት በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ኮንፈረንስ ላይ (ኮፕ 24) ካስተላለፉት መልእክት ለመረዳት ተችሉዋል።
ምድራችንን ማዳመጥ የገባል
በዚህ በተባበሩት መንግስታት አዘጋጅነት የተካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ (ኮፕ 24) የተለላፉት ደንቦች በምድር ላይ እየደርሰ ያለውን ጥፋት እንጂ ይህ ደንብ - የሰብአዊ መብት ሁኔታን በተገቢው መንገድ ያላገናዘበ እና ያልተመለከተ ኮንፈረንስ መሆኑን የጠቆሙት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በዚህ የአየር ንበረት ለውጥ የተነሳ በጣም የተጠቁ እና ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የዓለማችን ሕዝቦች ጩኸት እጅግ እየላቀ መሄዱ አሳሳቢ በመሆኑ የተነሳ ከግንዛቤ ውስጥ ሊገብ ይገባ እንደ ነበረ ጨምረው ገልጸዋል።
ቅድስት መንበር በተገኘው አገጣሚ ሁሉ ጠንካራ የሆነ አቋሟን በመግለጽ ከሁሉም ነገር በላይ የሰው ልጆች ሰብዓዊ መብታቸው ይከበር ዘንድ አበክራ እየገለጸች መሆኑን ያስታወሱት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በማነኛው እኮኖሚያዊ እድገት ውስጥ መአከል መሆን የሚገባቸው የሰው ልጆች መሆን እንዳለባቸው ጨምረው ገልጸው በምንም ዓይነት ሁኔታ የሰው ልጆችን ስብዓዊ መብት አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግባሮችን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እንደ ማትቀበል ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጨምረው ገለጸዋል። በዚህም መስረት ማነኛው ኢኮኖሚያዊ እድገት በተቀናጀ መልኩ የሰው ልጅን ሰብዓዊ መብት ከግምት ያስገባ መሆን እንደ ሚገባው ገልጸው በዚህም ረገድ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በስፊው እየተጎዱ የሚገኙት ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ የዓለማችን ሕዝቦች በመሆናቸው የተነሳ የአየር ንበረት ለውጥ እና ሰብዓዊ መብት በዚህ አግባብ የተገናኙ በመሆናቸው የተነሳ የሰብዓዊ መብት መከበር ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተለይቶ መታየት የሌለበት ጉዳይ መሆኑን በአጽኖት ገለጸዋል።
ዘላቂ የሆነ ድንጋጌ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በላቲን ቋንቋ “Laudato Si” በአማርኛው ውዳሴ ለአንተ ይሁን በሚለው እና የጋራ መኖሪያ ቤታችንን ከጥፋት እንከላከል በሚል ጭብጥ ዙርያ ለንባብ ባበቁት ሐዋርያዊ መልእክታቸው ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ለዓለማችን የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ የሆነ ትኩረት በመስጠት በዚህ የዓለም የአየር ነበረት ለውጥ የተነሳ እየተከሰቱ የሚገኙትን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ፍትሀዊ የአብት ክፍፍል ላይ የደቀነውን ከፍተኛ አደጋ ማስወገድ እንደ ሚገባ በተደጋጋሚ ቅዱስነታቸው ማሳሰባቸውን ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በንግግራቸው ገልጸዋል። በዚህ ረገድ የቅድስት መንበር ወይም የቫቲካን አቋም መነኛው ኢኮኖሚ፣ ማነኛውም እድገት፣ መነኛው በዓለማችን ላይ የሚደረግ እንቅስቃሴ የጋራ መኖሪያ የሆነችውን ዓለማችንን በማይጎዳ መልኩ የካርበን ጋዝ ልቀት ውጪ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን እንደ ምትደግፍ ያወሱት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን አማራጭ እና ታጋሽ የኃይል ምንጭችን በመጠቀም ምድራችንን ከካርበን ጋዝ ልቀት ነጻ በሆነ መልኩ በማልማት ለመጪው ትውልድ ምቹ የሆነች ዓለም መፍጠር እንደ ሚገባ መግለጻቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

 

20 December 2018, 16:17