ፈልግ

ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን  በሞሮኮ    ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በሞሮኮ  

ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን “ለስደተኞች ሰብዓዊ ክብርን የጠበቀ ምላሽ መስጠት ይገባል”

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ለሁለት ቀናት ያህል በሞሮኮ ማሬኬሽ ስደተኞችን በተመለከተ ለስደተኞ ዓለማቀፍ በሆነ ደረጃ ደህንነታቸውን የተጠበቀ፣ ሥርዓታማ እና መደበኛ በሆነ መልኩ ስደተኞችን ለማስተናገድ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ይረዳ ዘንድ ከዓለም ዙርያ የተሰበሰቡ የተለያዩ ሀገራት መንግሥታት በማካሄድ ላይ ባሉት የሁለት ቀን ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር እንደ ገለጹት “ለስደተኞች ጥያቄ  ሰብዓዊ ክብርን የጠበቀ ምላሽ መስጠት ይገባል” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ከ160 በላይ ሀገራት የተወጣጡ ተሳታፊዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ የተዘረጋውን ለሰብአዊ ደህንነት ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ ለመስጠት እና ሰብዓዊ እንቅስቃሴን ለማረጋጋት የሚያስችለውን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀረበውን አስገዳጅ ያልሆነ ደንብ ለመቀበል መስማማታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል። የቅድስት መንበር ከፍተኛ ተወካዮችን ጨምሮ በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የጀርመኗ መርሃ መንግሥት አንጌላ መርክልን ጨምሮ ይህንን አስገዳጅ ያለሆነ ስምምነት መፈረማቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በወቅቱ በኮነፈረንሱ ላይ የተገኙት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በንግግራቸው ወቅት እንደ ገለጹት “ለስደተኞች በዓለማቀፍ ደረጃ አግልግሎት መስጠት እና ስደተኞችን መቀበል በታሪክ ውስጥ ወሳኝ በሆነ ወቅት ላይ እንደ ሚገኝ” መግለጻቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ስደተኞችን በተመለከተ ቀውሶችን እና አደጋን ለመከላከል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማገዝ የሚደረገውን ሙከራ በማነኛውም መንገድ ማገዝ እንደ ሚገባ የገለጹ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩም የዓለምን ማህበረሰብ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ያለው ትስስር የተጠናከረ እንዲሆን  በተሰራ መጠን ስደተኞችን ለማስተናገድ እና የኑሮ ሁኔታዎቻቸውን ለማሻሻል የሚያስችል እንደ ሆነ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። እነዚህን ግቦች ለማሳካት" ዓለም አቀፉ ሰደተኞችን በተመለከተ የረቀቀው የስምምነት የአቋም መግለጫ ምንም እንኳን ሕጋዊ በሆነ መልኩ አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ የሚተገበር ስምምነት ባይሆንም ሁሉም የስነ-ፍልሰ- ተግባሮች ተጓዳኝነት ያላቸው በመሆኑ የተነሳ ዓለም አቀፍ ትብብርን እና ሃላፊነትን በመጋራት አጠቃላይ የህግ ማዕቀፎች እና ፖሊሲዎችን በማርቀቅ ማካተት እንደ ሚገባ ጨምረው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የስደተኞችን ጉዳይ በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው የሚከታተሉት ጉዳይ እንደ ሆነ በንግግራቸው የገለጹት የቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ስደተኞች ሁኔታ በመከታተል እና ስለሁኔታው ግንዛቤ በማስጨበጥ፣ ተገቢ የሆነ ሰብዓዊ እንክብካቤ እንዲደርግላቸው እና ለመፈናቀላቸው መንስሄ የሆኑ አብይት ተግባራን ንቅሶ በማውጣት እና መንስሄዎቻቸውንም በመረዳት ተገቢውን ምልስ ለመስጠት በአጠቃላይ ለስደተኞች ጉዳይ ስነ-ምግባራዊ የሆነ ምላሽ ለመስጠት ቅዱስነታቸው እየተጉ መሆናቸውን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጨምረው ገልጸዋል።

12 December 2018, 15:24