ፈልግ

አባ ካንታላሜሳ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለሆነ ሌላ ውጫዊ የሆነ ነገር መፈለግ አይገባንም”

የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት ለማክበር ያስችለን ዘንድ የመዘጋጃ ወቅት የሚሆነን የስብከተ ገና ሳምንት በኅዳር 23/2011 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል።

ይህንን የስብከተ ገና የዝግጅት ወቅት በማስመልከት በቫቲካን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፣ የእርሳቸው የቅርብ የሥራ ተባባሪ የሆኑት ብጹዕን ጳጳሳት እና ቀሳውስት፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤት ሰባኪ የሆኑት አባ ራኔሮ ካንታላሜሳ ይህንን የስብከተ ገና ወቅት በማስመልከት በቫቲካን በሚገኘው ሬደምቶሪስ ማተር በመባል በሚታወቀው የጸሎት ቤት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መሰረቱን ያደርገ አስተንትኖ በመስጠት ላይ መሆናቸው ይታወቃል። ለዘንድሮ የሰብከተ ገና ሳምንታት ዝግጅት ይሆን ዘንድ የተመረጠው የመጽሐፍ ቅዱስ የአስተንትኖ ሐሳብ የተወሰደው “ነፍሴ ሕያው አምላክን ተጠማች” (መዝ. 42፡2) ላይ የተወሰደው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንደ ሆንም ተገልጹዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“ለተለያዩ ችግሮቻችን መፍትሄ ለመስጠት፣ የተለያዩ ችግሮቻችንን ለመጋፈጥ፣ ለተለያዩ ተግዳሮቶቻችን ምላሽ ለመስጠት ሳንችል ቀርተን እያየን እንዳላየ ሆነን እናልፋለን ወይም ችግሮቹን እንዳሉ እዚያ በመተው ለመኖር እንመርጣለን። ከእግዚኣብሔር ጋር ያለን የግል ግንኙነት እንዴት ነው? በሰላም እና በትዕግስት ማጣት ምክንያት የሚከሰቱ ችግሮችን በቀዳሚነት የምንጋፈጠው በምን ዓይነት ሁኔታ ነው? የሚሉትን ቁልፍ የሆኑ በሕይወት ሂደት ውስጥ የሚገጥሙንን ቁልፍ የሆኑ ተግዳሮቶች በዚህ በስብከተ ገና ሳምንታት ውስጥ መገምገም እንደ ሚገባን” የሚያሳስብ አስተንትኖ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

“እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለሆነ ሌላ ውጫዊ የሆነ ነገር መፈለግ አይገባንም”

ጊዜያዊ የሆኑ ችግሮቻችንን በሙሉ ወደ ጎን በመተው ሕያው የሆነው እግዚኣብሔር የምያሳየንን ምልክቶች በመከተል ከእርሱ ጋር ቀጣይነት ያለው እና ሕይወት ሊዘራ የሚችል ግንኙነት በመመስረት መኖር እንደ ሚገባን የገለጹት የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤት ሰባኪ የሆኑት አባ ካንታላሜሳ በተቃራኒው በዓለማችን የሚገኙ የዘመናችን ሰዎች በዓለም ውስጥ ለመኖር የሚያስችላቸውን ምልክቶች በመከተል እና አዋቂ የሆኑ ሰዎች መሆናቸውን ለማሳየት በመፈለግ በዚህም አግባብ ምርምር በማድረግ በመትጋት በመኖር ላይ እንደ ሚገኙም ገልጸዋል። ምንም እንኳን ይህ ህጋዊነትን የተላበሰ ምርምር ቢሆንም ምንም እንኳን" እርግጠኛ ባይሆኑም፣ ሕዋ ውስጥ በመግባት አጽናፈ ዓለምን የፈጠረው ሕያው ፍጡር ማን እንደ ሆነ ይመራመራሉ፣ ያጠናሉ በሕዋ ውስጥ ማን እንደ ሚኖር ለማወቅ በታሪክ ውስጥ ያሉትን ምልክቶች ለማግኘት ይጣጣራሉ ብለዋል። “በመካከላችን እውነተኛ እና ሕያው የሆነ አምላክ አለ” በማለት ግልጽ በሆነ ሁኔታ በማስቀመጥ አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት አባ ካንታላሜሳ ብዙን ጊዜ በእኛ መካከል የሚገኘውን ሕያው የሆነ አምላክ መኖሩን በመዘንጋት በግብዝነት መንፈስ ከሞት ልያድኑን የማይችሉትን ነገሮች እንፈልጋለን ብለዋል።

ሁሉንም ነገር በትዕግስት ማግኘት ይቻላል

የእግዚአብሔር ልጅ ከየትኛውም ጊዜ እና መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ባሻገር በመሄድ እኛ ከምንጠይቀው ጥቃቅን የሆኑ ነገሮች ባሻገር በመሄድ ራሱን አሳልፎ ለመስጠት ቃል እንደ ገባ በአስተንትኖዋቸው የገለጹት አባ ካንታላሜሳ ይህም የእግዚኣብሔር ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገባልን የተስፋ ቃል ሁሌም ቢሆን ተጠብቆ እንደ ሚኖር ጨምረው ገልጸዋል። “እርሱን የሚፈልገው ሰው ሁሉ ያገኘዋል” ለምያንኳኳ ሰው ሁሉ እርሱ በሩን ይከፍትለታል፣ አንድ ጊዜ እርሱን ካገኘነው ሌላው ነገር ሁሉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል” ብለዋል። "ወደ እምነት መመለስ" ማለት በሐሳባችን ዐውድ የፈጠርነውን ግድግዳ ደርምሶ በማለፍ እጁን ከፍቶ የሚጠብቀንን ሰማያዊ አባታችንን ለመገናኘት ወደ እዚያው መጓዝ ማለት ነው በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉ አባ ካንታላሜሳ እርሱ አንድ ረቂቅ የሆነ ነገር ሳይሆን ነገር ግን አንድ እውነታ ነው ብለዋል። እኛ ከምናስበው በላይ እግዚኣብሔር ሕያው የሆነ አማላክ መሆኑን በአጽኖት በመግለጽ አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት አባ ካንታላሜሳ በወረቃት ላይ በተሳለው ሰማይ እና በእውነተኛው ሰማይ መካከል ከፍተኛ የሆነ ልዩነት እንዳለም ጨምረው ገልጸዋል።

የሕያው እግዚአብሔርን ፊት ፍለጋ

ከጥንት ጊዜ አንስቶ የሰው ልጆች የሕያው እግዚአብሔርን ፊት ፍለጋ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ተስማርተው ከፍተኛ የሆኑ ምርምሮችን እና ጥናቶችን ስያካሂዱ መቆየታቸውን የገለጹት አባ ካንታላሜሳ ይሁን እንጂ የሰው ልጅ ረቂቂ የሆነውን እግዚኣብሔር በተለያዩ ነገሮች እና ሁኔታዎች ውስጥ የሚፈልገው ቢሆንም፣ እግዚኣብሔር ግን ባልተጠበቀ ሁኔታ ወደ ሰዎች በመቅረብ በሰዎች ሕይወት ውስጥ በድንገት በመከሰት መንፈሳዊ ልውጥ እንዲያመጡ እያደረጋቸው እንደ ሆነ በታሪክ ውስጥ ከታዩ በራካታ ክስተቶች መማር ይቻላል ብለዋል።

07 December 2018, 16:34