ፈልግ

2018-06-13 Papa Francesco Udienza generale 2018-06-13 Papa Francesco Udienza generale 

ቅድስት መንበር እና የአይሁድ እምነት መምህራን የሕፃናትን ሕይወት እና ክብር ለማሳደግ ተስማሙ።

ለሕጻናት የሚሰጥ ሰብዓዊ ክብር፣ ለሕጻናት ሊደረጉ የሚያስፈልጉ በርካታ ማነቃቂያ መንገዶችን ያካተተ መሆን አለበት።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የታላቁ የአይሁድ እምነት መምሕራን ልኡካንና በቅድስት መንበር የሐይማኖቶች ግንኙነት ጳጳሳዊ ምክር ቤት በመካከላቸው ባደረጉት ውሳኔ የሕፃናትን ህይወት እና ክብር ለማሳደግ መስማማታቸው ታውቋል። ወደዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት በሮም ከተማ ከህዳር 9 እስከ ህዳር 11 ቀን 2011 ዓ. ም. ድረስ ባደረጉት 16ኛው የጋራ ጉባኤ ወቅት እንደሆነ ታውቋል።

በሁለቱ የሐይማኖት ወገኖች ማለትም የታላቁ የአይሁድ እምነት መምሕራን ልኡካንና በቅድስት መንበር የሐይማኖቶች ግንኙነት ጳጳሳዊ ምክር ቤት መካከል የተደረሰው ስምምነት፣ በማሕበረሰባችን ውስጥ አቅመ ደካማ ለሆኑት፣ በተለይም ለወደ ፊት ትውልድ ዋስትና ለሆኑትና ራሳቸውን ለመከላከል አቅም ለሚያንሳቸው ሕጻናት ህይወት ልዩ ክብር የመስጠት ግዴታ አለብን የሚል እንደሆነ ታውቋል።

ለሕጻናት እንክብካቤን ለመስጠት ወደሚያችል ሃሳብ ላይ መድረስ፣

ለሕጻናት የሚሰጥ ሰብዓዊ ክብር ለሕጻናት ሊደረጉ የሚያስፈልጉ በርካታ ማነቃቂያ መንገዶችን ያካተተ መሆን አለበት፣  እንክብካቤ የመስጠት ችሎታንም ለማሳደግ ወደሚያችል የሃሳብ እድገት ላይም መድረስ ይኖርበታል ያሉት የሁለቱ የእምነት ተቋማት ማለትም፣ የአይሁድ እምነት መምሕራን ልኡካንና በቅድስት መንበር የሐይማኖቶች ግንኙነት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ተወካዮች፣ በአይሁድ እምነት በኩል መምህር ራሶን አሩሲ ሲሆኑ በቅድስት መንበር በኩል የፍትህና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ፕሬዚደትን የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ፒተር ታርክሰን መሆናቸው ታውቋል።

ሃሳብ የማሳደግ ሂደት፣

ሁለቱም ወገኖች የተስማሙበት ርዕስ የሕጻናትን ጤንነትና የሚደረግላቸውን ጥበቃ ማሳደግ፣ በትምህርት ቤት የሚሰጡትን የሐይማኖት ትምህርቶችን አስፈላጊነት ማወቅ፣ ሕጻናትን ለሚመለከቱ ጉዳዮች ትኩረትን በመስጠት የመለጠ ማሳደግና የሕጻናትን የፈጠራ ችሎታ ማሳደግ የሚሉ እንደሚገኙበት ታውቋል። ስምምነቱ በማከልም ሕብርተሰቡ በራሱ በተለይም ወላጆች፣ መምህራን፣ መንፈሳዊ አቅጣጫዎችን ማሳየቱም በሕጻናት ስነ ምግባራዊና መንፈሳዊ አስተዳደግ ውስጥ ልዩ ሃላፊነትን ይጠይቃል ብሏል። የዚህ ሃስብ ዋና ዓላማም የሕጻናትን ሰብዓዊ ክብር ከማንኛውም ዓይነት ጥቃት መጠበቅና መከላለል እንደሆነ ሁለቱም ወገኖች መስማማታቸውን ገልጸዋል።

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር የተደረገ ግንኙነት፣

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር ያደረጉትን ግንኙነት ያስታወሱት የሁለቱም ምክር ቤቶች አባላት ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኩል የተደረገላቸው አቀባበል፣ ቅዱስነታቸው ጉባኤው ባስተላለፈው ስምምነቶች መደሰታቸውን የሚገልጽና በተለይም ውይይቶች በተደረጉባቸው ርዕሶች ማለትም በሕልፈተ ሕይወት፣ በሕክምና የሚሰጥ የሕይወት ማብቂያ መንገድ፣ የራስን ሕይወት ለማክተም የሚደረግ እገዛ የሚሉ በሰብዓዊ ፍጡር ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎችን የሚመለከቱ እንደሆኑ ቅዱስነታቸው መገንዘባቸው  ታውቋል።      

23 November 2018, 15:38