ፈልግ

ከዛሬ 75 ዓመት በፊት በቫቲካን ላይ በፋሽቶች የደርሰው ጥቃት ታስቦ ዋለ! ከዛሬ 75 ዓመት በፊት በቫቲካን ላይ በፋሽቶች የደርሰው ጥቃት ታስቦ ዋለ! 

ከዛሬ 75 ዓመት በፊት በቫቲካን ላይ በፋሽቶች የደርሰው ጥቃት ታስቦ ዋለ!

አጉስቶ ፌራራ የተባለ አንድ ጣልያናዊ “1943 Bombe sul Vaticano” በአማርኛው በ1943 ዓ.ም በቫቲካን ላይ የተጣሉ ቦንቦች” በሚል አርእስት በወቅቱ ለንባብ ባበቃው መጽሐፍ ላይ በጥቅምት 26/1943 ዓ.ም የዛሬ 75 አመት ገደማ ማለት ነው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት መንበር መቀመጫ በሆነቺው በቫቲካን ላይ በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ስለተጣሉ ቦንቦች በስፊው የሚያትት መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በወቅቱ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1943 ዓ.ም በመካሄድ ላይ በነበረው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ምክንያት በተከሰተው ከፍተኛ ጉዳቶች የተነሳ በጠፋው የሰው ሕይወት እና  የንብረት ውድመት የተነሳ በርካታ ቤተሰቦች ማዘናቸው እና ለስደት መዳረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ይህ ጉዳይ ቤተ ክርስቲያንን እጅግ በጣም ያሳዘነ ጉዳይ ነበር።

እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በጥቅምት 26/1943 ዓ.ም የዛሬ 75 ዓመት ገደማ ማለት ነው ምሽት ላይ አንድ የጦር አውሮፕላን ሳይታሰብ በጣም ዝቅ ብሎ በመብረር በቫቲካን ላይ 5 ትላልቅ ቦንቦችን ይጥላል። እነዚህ በቫቲካን በተለያዩ ስፍራዎች የተጣሉ ቦንቦች ምንም እንኳን በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት ያላደረሱ ቢሆንም ነገር ግን በቫቲካን ከተማ የሚገኙትን ሕንጻዎች፣ ታሪካዊ ስፍራዎች፣ ቤተ መዘክሮች እና በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ አጠገብ የወደቀው ቦንብ ደግሞ የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በቀጥታ ባይነካውም ነገር ግን በውስጡ የነበሩ መስታዎቶች እንዲሰባበሩ በማድረግ ከፍተኛ እና ታሪካዊ የሆነ ውድመት አስከትሉዋል።

እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር “በ1943 ዓ.ም በቫቲካን ላይ የተጣሉ ቦንቦች” በሚል አርእስት በአጉስቶ ፌራራ ለንባብ የበቃው መጽሐፍ ይህንን በሁለኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በቫቲካን ላይ የተጣሉት 5 ቦንቦች በተመለከተ በመጽሐፉ ውስጥ እንደ ገለጸው የእዚህ ቦንብ ድብደባ ዋነኛው ዓላማ እና ኢላማ የነበረው የቫቲካን ሬድዮ የማሰራጫ ጣቢያ እንደ ነበረ የገለጸ ሲሆን ምክንያቱም በወቅቱ የቫቲካን ሬዲዮ የሁለተኛ የዓለም  ጦርነትን በማውገዝ፣ እያደረሰው የሚገኘውን ከፍተኛ ጥፋት ለዓለም በመግለጽ በተለይም ደግሞ የጦር እስረኛ የነበሩ ሰዎች አያያዝ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑ በወቅቱ በስፋት በመዘገቡ የተነሳ መሆኑን አጎስቶ ፌራራ ገልጹዋል።

“በ1943 ዓ.ም በቫቲካን ላይ የተጣሉ ቦንቦች” በሚል አርእስት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በቫቲካን ላይ የተጣሉትን 5 ቦንቦች በተመለከተ መጽሐፍ ያሳተሙት አጎስቶ ፌራራ ከቫቲካን ዜና ጋር በትላንትናው ዕለት ማለትም በጥቅምት 26/2011 ዓ.ም ባድረጉት ቃለ ምልልስ ይህንን ጥቃት በተመለከተ እንደ ገለጹት “በእርግጥ እነዚህ በቫቲካን ላይ የተጣሉ 5 ቦንቦች በቫቲካን ከተማ ውስጥ የሚገኘውን እና በወቅቱ በመካሄድ ላይ የነበረውን ሁለተኛ የዓለም ጦርነት በመቃወም ከፍተኛ ዘገባ ስያስተላለፍ የነበረውን የቫቲካን ሬዲዮ ዋና መስርያ ቤት ለመደምሰስ የተቃጣ ጥቃት እንደ ነበረ ምንም ጥርጥር እንደ ሌላቸው” ገልጸዋል።

በወቅቱ የነበሩት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮ 12ኛ ይህንን በፋሽስቶች የተቃጣውን የቦንብ ጥቃት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ምዕመናን በተሰበሰቡበት ጥቃቱን አውግዘው እንደ ነበር ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

06 November 2018, 14:29