ፈልግ

TRATTA DI ESSERI UMANI TRATTA DI ESSERI UMANI 

ቅድስት መንበር ከ40 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በባርነት ሕይወት ውስጥ እንደሚገኙ አስታወቀች።

ሊቀ ጳጳስ ቤርናዲቶ አውዛ ምንም እንኳን ወንጀሉን ለመከላከል ቃል ከተገባበት ከፓለርሞ ፕሮቶኮል እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስምምነቶች በኋላ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም በዓለማችን ከ40 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በተለያዩ የባርነት ሕይወት ውስጥ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በዓለማችን ከ40 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በተለያየ የባርነት ሕይወት ውስጥ እንደሚገኙ ቅድስት መንበር ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ይፋ አደረጋለች። ለባርነት ሕይወት የተዳረጉትም በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የተጠውቁ መሆናቸው አስታውቋ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በጽኑ መቃወም እንደሚያስፈልግ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቤርናዲቶ አውዛ ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀ ጳጳስ ቤርናዲቶ አውዛ በማከል ቤተክርስቲያን በሰዎች ላይ የሚደርስ ሕገ ወጥ የሰው ልጅ ዝውውር ለማስቆም ትኩረት ሰጥታበት በመሥራት ላይ መሆኗን ገልጸው ወጣቶችም ይህን አሰቃቂ ድርጊት ለማስወገድ ድርፍረትን የተላበሰ ጥረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል። ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን አስመልክቶ በተባበበሩት ሕንጻ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ትናንት ተገኝተው ድምጻቸውን ያሰሙት፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቤርናዲቶ አውዛ፣ በወንጀሉ ምክንያት በሰዎች ላይ በሚደርሱ ችግሮች ብቻ ማትኮር ሳይሆን የወንጀሉ መሠረትን፣ ኤኮኖሚያዊ ይዘታቸውንም ለይቶ ማወቅ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። ሊቀ ጳጳስ ቤርናዲቶ አውዛ በማከልም ምንም እንኳን ወንጀሉን ለመከላከል ቃል ከተገባበት ከፓለርሞ ፕሮቶኮል እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስምምነቶች በኋላ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም በዓለማችን ከ40 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በተለያዩ የባርነት ሕይወት ውስጥ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

ስምምነቶች በተግባት መተርጎም ይኖርባቸዋል፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመስከረም ወር 2008 ዓ. ም. በሰዎች ላይ የሚፈጸም ህገ ወጥ ወንጀል እየተስፋፋ በሚገኝበት ባሁኑ ጊዜ በተግባር ላይ የማይዉሉ ውሳኔዎችን ማስተላለፍ ምንም ፋይዳ አይኖረውም ያሉትን ያስታወሱት ሊቀ ጳጳስ ቤርናዲቶ፣ ሕገ ወጥ ወንጀሉ በሰዎች ላይ የባርነት ሕይወትን፣ ሴትኛ አዳሪነትን፣ የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛንና የሰው አካል ክፍሎች ንግድን እያስፋፋ መምጣጡን አስረድተው አራት ደንቦችና ውሳኔዎች በተግባር መተርጎም እንዳለባቸው አስረድተው እነዚህም ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን መከላከል፣ ሰዎች የወንጀሉ ተጠቂ እንዳይሆኑ መከላከል፣ በወንጀሉ ላይ የተሰማሩትን ወደ ሕግ ዘንድ ማቅረብና ውንጀሉን ለመከላከል የቆሙት ተቋማት በመካከላቸው ሕብረት እንዲኖር ያስፈልጋል ብለዋል።

የእምነት ተቋማት ጥረት መኖር ያስፈልጋል፣

በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ሰለባ የሆኑትን ለመርዳት በ70 አገሮች ውስጥ የሚገኙ 22 የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ድርጅቶች መኖራቸውን ያስታወሱት ሊቀ ጳጳስ ቤርናዲቶ የቅድስት ማርታ ግሩፕ የተባለ የቤተክርስቲያን ተቋም ከሌሎችም የሕይማኖት ድርጅቶች ጋር፣ ከመንግሥት የፖሊስ ሠራዊት ጋር የተቀናጀ ሕብረትን በመፍጠር ወንጀሉን ለመዋጋት እያንዳንዱ ተቋም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። 

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት ይጫኑ
12 November 2018, 15:13