ፈልግ

2018.11.28 Card. Parolin incontra l'Associazione Rondine 2018.11.28 Card. Parolin incontra l'Associazione Rondine 

ካርዲናል ፓሮሊን በፖለቲካው ዓለም ሰላምን የሚያራምዱ አዳዲስ መሪዎች እንደሚያስፈልጉ ገለጹ፣

የቅድስት መንበር ዋና ተግባር የሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር ከሚሰሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር በመተባበር፣ ሁለገብ ማሕበራዊ እድገትን ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት ማገዝና መደገፍ እንደሆነ ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን አስረድተው፣ በኢጣሊያ ውስጥ ከተቋቋመ ሃያ አመታትን ያስቆጠረውን የግጭት አስወጋጅ ኮሚቴ ማሕበር፣ የቆመለትን ዓላማ እንዲያሳካ፣ ሰላማዊ ማሕበረሰብን ለመገንባት የሚያድረገው ጥረት ውጤትን እንዲያመጣ፣ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የጋራ ውይይት አስፈላጊነት በመረዳት፣ በተለይም ደግሞ የሕዝቦችን ማሕበራዊ እድገት በማስቀደምና ለዚህ ዓላማ የሚቆሙ ወጣቶችን ለማዘጋጀት የሚያደርገው ጥረት ፍሬያማ እንዲሆን ለማገዝ ቅድስት መንበር ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የፖለቲካ ስርዓት ቀዳሚ ዓላማ ሕዝቦች ለጋራ ልማት እንዲቆም ማስተባበር፣ በአገር ውስጥ ሆነ በዓለም አቀፍ ደርጃ በአገሮች መካከል ለሚፈጠሩ አዳዲስ ቅራኔዎች የጋራ መፍትሄዎችን ማግኘት እንዲቻል መንገዶችን የሚያመቻች መሆን ያስፈልጋል ብለዋል። ይህ ካልሆነ ግን ዛሬ የመከላከል እና የመተግበር ግዴታ ያለብንን የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ሊደናቀፍ ይችላል ብለዋል። ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ይህን ያስገነዘቡት ህዳር 19 ቀን 2011 ዓ. ም. ግጭቶች ከሚካሄዱባቸው አገሮች ሸሽተው በኢጣሊያ የግጭት አስወጋጅ ማሕበር ልኡካን ከቅድስት መንበር ዲፕሎማሲ አካላት ጋር በተገናኙበት ወቅት መሆኑ ታውቋል።

ለውይይት ብቃት ያለው አዲስ የፖለቲካ ባለስልጣን ያስፈልጋል፣

የቅድስት መንበር ዋና ተግባር የሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር ከሚሰሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር በመተባበር፣ ሁለገብ ማሕበራዊ እድገትን ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት ማገዝና መደገፍ እንደሆነ ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን አስረድተው፣ በኢጣሊያ ውስጥ ከተቋቋመ ሃያ አመታትን ያስቆጠረውን የግጭት አስወጋጅ ኮሚቴ ማሕበር፣ የቆመለትን ዓላማ እንዲያሳካ፣ ሰላማዊ ማሕበረሰብን ለመገንባት የሚያድረገው ጥረት ውጤትን እንዲያመጣ፣ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የጋራ ውይይት አስፈላጊነት በመረዳት፣ በተለይም ደግሞ የሕዝቦችን ማሕበራዊ እድገት በማስቀደምና ለዚህ ዓላማ የሚቆሙ ወጣቶችን ለማዘጋጀት የሚያደርገው ጥረት ፍሬያማ እንዲሆን ለማገዝ ቅድስት መንበር ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

በኢጣሊያ የግጭት አስወጋጅ ማሕበር የሰላም አራማጅ ወጣቶችን ለማፍራት ይጥራል፣

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን፣ የሰላም መሪዎች በሚል ርዕስ በየሦስት ዓመት የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ ዘመቻን ለመጀመር የሚያስችል አዲስ መርሃ ግብር ከኢጣሊያ የግጭት አስወጋጅ ማሕበር እጅ የተቀብሉ ሲሆን ማሕበሩ በዚህ አዲስ የቅስቀሳ ዘመቻው የዓለም መንግሥታት እገዛና ድጋፍ መጠየቁ ታውቋል። አዲስ ነው የተባለው መርሃ ግብር በቀዳሚነት የሚያስቀምጠው መንግሥታት በየአገሮቻቸው ካዋቀሩት የትምሕርት ሥርዓት ጋር በማዛመድ ስለ ሰላምና ስለ ሰብዓዊ መብቶች በቂ ዕውቀት የሚገኝበት የትምህርት ዘርፍ ተዘርግቶ፣ የሰላም መሪ ወጣቶችን ለማዘጋጀት የሚያስችል መርሃ ግብር እንደሆነ ታውቋል።

በፍልስጤምና በእስራኤል መካከል ሰላም እንዲመጣ ጥሪ ቀርቧል፣

በኢጣሊያ ውስጥ የተቋቋመው የግጭት አስወጋጅ ማሕበር ልኡካን በቫቲካን ውስጥ የቅድስት መንበርን ዲፕሎማሲ አካላት አግኝተው ባነጋገሯቸው  ወቅት፣ ከዚህ በፊት ማለትም በጥቅምት 1 ቀን 2011 ዓ. ም. ለኢጣሊያ ሪፓብሊክ መንግሥት ፕሬዚደንት ለሆኑት ለክቡር አቶ ሴርጆ ማታረላ፣ ግጭቶችና ጦርነቶች ባሉባቸው አገሮች መካከል ሰላምን ለማውረድ የኢጣሊያ መንግሥት የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግ የሚል ጥሪ ቀርቦ እንደነበር የሚገልጽ መልዕክት፣ ተመሳሳይ የሰላም ጥረት እንዲደረግ የሚል ጥሪ ሰኞ ህዳር 24 ቀን 2011 ዓ. ም. ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደሚደርሳቸው የሚገልጽ መልዕክት በሁለት አገሮች ተወላጆች ማለትም በፍልስጤምና በእስራኤል አገር ተወላጆች በኩል የተነበበ መሆኑ ታውቋል። በኢጣሊያ ውስጥ የተቋቋመውን የግጭት አስወጋጅ ማሕበር መስራችና ፕሬዚደንት የሆኑት አቶ ፍራንኮ ቫካሪ፣ በቅድስት መንበር የተለያዩ አገሮች አምባሳደሮችና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ የየአገሮቻቸው አምባሳደሮችም ሳይቀሩ ወጣቶቹ በንባብ ላቀረቡት የሰላም ጥሪ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ በማለት ጥሪ አቅርበዋል። ክቡር አቶ ፍራንኮ ቫካሪ በማከልም በየሦስት ዓመት የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ ዘመቻ የሚጀምረው በመጭው ታህሳስ 1 ቀን 2011 ዓ. ም. በኒውዮርክ ከተማ እንደሆነ ገልጸው የዘመቻ እንቅስቃሴ ሞራላዊና ፖለቲካዊ ሃይልና ብርታት እንደሚያገኝ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ክቡር አቶ ፍራንኮ ቫካሪ በንግግራቸው እንዳስገነዘቡት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል አገሮች በኒውዮርክ ከተማ ተሰብስብው፣ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ የተደረገበት 70 ኛ አመትን በሚያከብሩበት ወቅትም ተመሳሳይ የሰላም ጥሪ የድጋፍ ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል። በዚህ ወቅትም ከኢጣሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቀረበለት ጥያቄ መሠረት ማሕበራቸው ግጭቶችን ለማስወገድ የተከተላቸውን መንገዶችንና ልምዶችን ለመንግስታቱ ድርጅት ይፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

በዓለም የሰላም ምሳሌ የሚሆኑ መሪዎችን ማዘጋጀት፣

በኢጣሊያ የግጭት አስወጋጅ ማሕበር መስራችና ፕሬዚደንት የሆኑት ክቡር አቶ ፍራንኮ ቫካሪ በመጨረሻም፣ የሰላም ጥሪ ድጋፍ መልዕክታቸውን በንባብ ያቀረቡት የሁለቱ አገሮች ተወላጆች ማለትም የፍልስጤምና የእስራኤል አገር ተወላጆች በሁለቱ አገሮች መካከል የሚታየውን የጠላትነት አሉታዊ ምስሎች ለይቶ አውጥተዋል ብለው በኢጣሊያ ውስጥ የሚገኝ የግጭት አስወጋጅ ማህበራቸው ቀስ በቀስ ተስፋን የሚሰጡ የሰላም ጥረቶችን እንደሚያደርግ አስረድተው፣ በዓለማችን የተስፋፋውን የሕዝቦች ስቃይ ለመቀንስ የሚረዱ መንገዶችን በመጠቀም የሰላም ምሳሌ የሚሆኑ መሪዎችን ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግና ማሕበራቸውም ለዚህ ዓላማ የቆመ መሆኑን አስረድተዋል።

30 November 2018, 15:23