ፈልግ

የኒውክለር የጦር መሳሪያ ሙከራ የኒውክለር የጦር መሳሪያ ሙከራ 

ቅድስት መንበር፡ “የኒውክለር የጦር መሳሪያ መስፋፋት የምያግደው ስምምነት በፍጹም መፍረስ የለበትም”

በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ እና በራሻ መካከል በአዲስ መልክ አገርሽቶ ሁሉቱን የዓለማችን ኃያላን የሚባሉ ሀገራት የኒውክለር የጦር መሳሪያ በአዲስ መልክ ለመታጠቅ የምደረገው ሩጫ ሁለቱንም ሀገራት ፍጥጫ ውስጥ እንደ ከተታቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህ ፍጥጫ ከሁለቱ ሀገራት ባሻገር የዓለማችንን ሕዝቦች ለስጋት የዳረገ ክስተት እየሆነ መምጣቱ ይታወቃል። 

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ

ከዚህ ቀደም ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1960ዎቹ በተከሰተው የቀዝቃዛው ጦርነት ሳቢያ ሁለቱም የዓለማችን ኃያላን ሀገራት የኒውክለር የጦር መሳሪያን በከፍተኛ ሁኔታ መታጠቅ መጀመራቸው የሚታወቅ ሲሆን በወቅቱ ይህንን ጅምላ ጨራሽ የሆነ መሳሪያ ለመታጠቅ የሚደርገው እሽቅድድም ለዓለማችን ከፍተኛ ስጋት በመሆኑ የተነሳ መወገድ የሚገባው ፍጥጫ እንደ ሆነ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አቋሟን መገልጿ የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ በመከናወን ላይ በነበረው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ መካከል ላይ ይህ ጉዳይ በከፍተኛ ሁኔታ ያሳሰባቸው በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዮሐንስ 23ኛ ይህንን በአሜሪካ እና በራሻ መካከል በወቅቱ ተከስቶ የነበረውን የኒውክለር የጦር መሳሪያ ፍጥጫ ለማርገብ በማሰብ  በላቲን ቋንቋ “Pacem in Terris” በአማርኛው “ሰላም በምድር ላይ ይሁን!” በሚል አርዕስት ሐዋሪያዊ መልእክት ለንባብ ማብቃታቸው የምታወስ ሲሆን በዚሁ ሐዋሪያዊ መልእክት በእውነት፣ በፍትህ፣ በፍቅር እና በነጻነት ላይ የተመሰረተ ዓለማቀፍ ይዘት ያለው ሰላም መገንባት እንደ ሚገባ ጠንካራ የሆነ መልእክት ለመላው የክርስቲያን ማኅበርሰብ እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ሁሉ ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል በአዲስ መልክ የኒውክለር የጦር መሳሪያን በተመለከተ ቀድም ሲል ይህንን የጦር መሳሪያ በዓይነት እና በይዘት ለመቀነስ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1987 ዓ.ም ሁለቱም ሀገራት የገቡትን ስምምነት በተለይም አሜርካ በአሁኑ ወቅት ባሉት ፕሬዚዳን ዶናልድ ትራንፕ አማካይነት ውድቅ በማድረግ አሜርካ በአዲስ መልክ የኒውክለር የጦር መሳሪያን ለመታጠቅ የወሰነችው ውሳኔ ዓለማችንን ስጋት ውስጥ እየከተተ የመጣ ወቅታዊ እና አሳሳቢ ጉዳይ እንደ ሆነ በእየ ጊዜው ከምንሰማው ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህ አሜርካ በተናጥል የወሰነችው ውሳኔ ሁለቱም ሀገራት የዛሬ 31 አመት ገደማ የፈረሙትን ስምምነት የሚሽር በመሆኑ ራሻ የሚያሳስባት ጉዳይ እንደ ሆነ በይፋ ማሳወቋ ይታወሳል።

ዓለማቀፍ ዘገባዎች እንደ ሚያሳዩት በሁለቱ የዓለማችን ኃያላን ሀገራት መካከል በአዲስ መልክ የቀዝቃዛው ጦርነት መከሰት መጀመሩን እየዘገቡ መሆናቸውን በስጋት በመግለጽ ላይ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ስጋቱ እንዲጨምር የሚያደረገው ክስተት ደግሞ ይህ ፍጥጫ ከሁለቱ የዓለማችን ኃያላን ሀገራት ባሻገ በመሄድ የኒውከለር የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሌሎች ሀገራትን ሳይቀር በተለይም ቻይናን ጭምሮ ያለተገባ ውዝግብ ውስጥ ሊከታቸው እንደ ሚችል ከወዲሁ ግምት ተሰቶታል።

ቅድስት መንበር፡ የአቶሚክ የጦር መሣሪያዎችን እገዳ እና ዓለም አቀፍ ስደተኞችን የተመለከተ ስምምነት ተጋባራዊ ሊሆን ይገባል

የአቶሚክ የጦር መሳሪያዎችን አስፈላጊ በሆነ ሰዓት ለመጠቀም የሚደርገው ሽርጉድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስጨንቃት እና የሚያሳስባት ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጿ የሚታወስ ሲሆን ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የኒውክለር የጦር መሳሪያን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚደርገው ሩጫ መጨረሻው አስከፊ የሆነ ጦርነት በመሆኑ በጥብቅ ሊታሰብበት የሚገባው ጉዳይ እንደ ሆነ አቋማቸውን በተለያዩ መንገዶች በመግለጽ ላይ እንደ ሚገኙ ይታወቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተለይም ደግሞ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መባቻ ላይ (በ1945 ዓ.ም ማለት ነው) በጃፓን ሄሮሽማ እና በነጋሳኪ ላይ የተጣሉት አቶሚክ ቦንቦች በወቅቱ ያደረሱትን ከፍተኛ ጉዳት በማስታወስ ይህ አስከፊ የሆነ ጥቃት በድጋሚ በምድራችን ላይ መፈጸም እንደ ሌለበት በተደጋጋሚ መገለጻቸው የሚታወስ ሲሆን ይህ በቀቡ የአሜርካው ፕረዝዳንት ዶንል ትራንፕ  የኒውክለር የጦር መሳሪያን በዓይነት እና በይዘት የማስፋፋት እቀባን የተመለከተ ስምምነት በተናጥል ለማፍረስ መሞከራቸው ተገቢ እንዳልሆነ እና በተቃራኒው የዓለማችንን ሕዝቦች ለስጋት ያጋለጠ ጅምላ ጨራሽ የሆነ መሳሪያ በመሆኑ የተነሳ ይህንን የተናጥል ውሳኔ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የምትቃወመው ብቻ ሳይሆን የምታወግዘው ተግባር መሆኑን ከቅድስት መነበር የደርሰን ዜና ያመለክታል።

23 October 2018, 15:52