ፈልግ

2018.10.09 conferenza stampa sinodo giovani 2018 sala stampa 2018.10.09 conferenza stampa sinodo giovani 2018 sala stampa 

ካርዲ. ግራሲያስ “ወጣቶች ቤተክርስቲያን ስሕተትን ከመቁጠር ይልቅ እንድንሳሳት ትፍቀደን ይላሉ”።

የሕንድ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚደንትና የቦምቤይ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ካርዲናል ኦስዋል ግራሲያስ የበርካታ የተለያዩ አገሮች ወጣቶች ጥያቄ ተመሳሳይነት እንዳለው ተመልክተው፣ ወጣቶች የእግዚአብሔርን ቃል እንድናዳምጥ የሚያድረግና የሚያሳትፍ የአምልኮ ስርዓት እንዲኖር መፈለጋቸውን ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ከመስከረም 23 ቀን 2011 ዓ. ም. ጀምሮ 15ኛው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤ በቫቲካን ከተማ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። በሆነው ወጣቶች፣ እምነታቸውና ጥሪያቸውን ጥበብና ማስተዋል በታከለበት አኳኋን እንዲገነዘቡ በሚለው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የመወያያ ርዕስ ርዕሥ ዙሪያ በርካታ ሃሳቦች፣ አስተያየቶች እንዲሁም መግለጫዎች ከተሳታፊዎች በኩል መቅረባቸው ታውቋል። የጳጳሳቱ ሲኖዶስ ትናንትና ባካሄደው ውይይቱ ቤተክርስቲያን የወጣቶችን ስሕተት ከመቁጠር ይልቅ እንዲሳሳቱ የምትፈቅድ ትሁን በማለት ወጣቶች ጥያቄ ማቅረባቸውን ብጹዕ ካርዲናል ግራሲያስ ግልጽ አድረገዋል። ትናንት መስከረም 29 ቀን 2011 ዓ. ም. የወጣቶችን እውነታ ለማዳመጥ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ቀርበው ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄ መስል የሰጡት ሦስት ካርዲናሎችና አንድ ገዳማዊ መነኩሴ መሆናቸው ታውቋል። በሕንድ የቦምቤይ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ካርዲናል ኦስዋል ግራሲያስ፣ ወጣቶች ቤተክርስቲያን በቁም ነገር እንድታዳምጠን ብቻ ሳይሆን እንድንሳሳትም በመፍቀድ ከስህተታችን እንድንማር ታድርገን ማለታቸውን አስረድተዋል።

15ኛውን የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት የተካፈሉትና በፈረንሳይ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ የቀድሞ የወጣቶች ስብከተ ወንጌል ስርጭትና ጥሪ አግልግሎት አስተባባሪ የነበርይት ሲስተር ናታሊ ቤካርት በጋዜጣዊ መግለጫቸው እንዳስረዱት፣ ወጣቶች፣ የጾታ ልዩነትን ሳታደርግ ሁሉ አቀፍ፣ ጠንካራና የወንድማማችነትን መንፈስ የተላበሰች ቤተክርስቲያን መመልከት እንደሚፈልጉ ገልጸው የወንጌል ምስክርነት ለመስጠት የሚያስችል ወጣቶችን ማዳመጥና ጥሪያቸውን በጥበብና በማስተዋል እንዲገነዘቡ የሚያግዝ የጳጳሳት ሲኖዶስ መኖር እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ሲስተር ናታሊ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጉባኤው በይፋ ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ ባሳየው የመጀመሪያ ሳምንት የውይይት ሂደት ባሳየው ወንድማዊ ስሜት መደሰታቸውን ገልጸዋል።

የሕንድ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚደንትና የቦምቤይ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ካርዲናል ኦስዋል ግራሲያስ የበርካታ የተለያዩ አገሮች ወጣቶች ጥያቄ ተመሳሳይነት እንዳለው ተመልክተው፣ ወጣቶች የእግዚአብሔርን ቃል እንድናዳምጥ የሚያድረግና  የሚያሳትፍ የአምልኮ ስርዓት እንድኖር መፈለጋቸውን ተናግረዋል።

ወደ አዲስ ሐዋርያዊ አገልግሎት ለወጣቶች፣

ከዘጠኙ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አማካሪ ካርዲናሎች መካከል አንዱ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ግራሲያስ እንደገለጹት፣ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ከጉባኤው በኋላ ለወጣቶች የሚሆን አዲስ የሐዋርያዊ አገልግሎት መንገድ እንደሚዘረጋ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ወጣቶች ተደማጭነትን ካገኙ የበለጠ ያምኑናል፣

ወጣቶችን ማዳመጥ፣ መውደድና ለሕይወታቸው ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ያሉት የማዳጋስካር ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚደንት ብጹዕ ካርዲናል ዴዚሬ ጻራሃዛን እንዳስገነዘቡት ወጣቶች እኛን የሚከተሉት እንዲሁም እምነታቸውን የሚጥሉብን እኛ እውነተኛ የወንጌል መስካሪዎች ስንሆን ነው ብለዋል። ካርዲናል ዴዚሬ ጋዜጣዊ መግለጫቸውን በመቀጠል እምነትን ከዕለታዊ ኑሮ ነጥሎ መመልከት የለብንም ብለው፣ በማዳጋስካር የሚገኙ ክርስቲያኖች በሙሉ እምነታቸውን ከዕለታው ኑሮ ጋር ማዛመድ ቢችሉ ኖሮ ማዳጋስካር አሁን ወደምትገኝበት አስቸጋሪ ጊዜ ላይ አትደርስም ነበር ብለዋል።  የማዳጋስካርን ማሕበራዊ ችግሮችን በመገንዘብ በተለይም ወጣቱ ትውልድ አስተሳሰቡን በመለወጥ፣ ሃላፊነትን በትክክል እንዲወጣ የሚያሳስብ ጥሪን የማዳጋስካር ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ማስተላለፉን ገልጸዋል። ብጹዕ ካርዲናል ዴዚሬ በማዳጋስካር የሚታየው ከፍተኛ የሥራ እጦትና ሙሰኝነት የወጣቶችን ሕይወት እንደጎዳው ገልጸዋል። ካርዲናል ዴዚሬ በመጨረሻም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ማዳጋስካር ሐዋርያዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ መጋበዛቸውን የገለጹ ሲሆን፣ በመጭው የአውሮጳዊያኑ ዓመት 2019 ዓ. ም. እንደሚታይ በቅድስት መንበር የቫቲካን የሕትመት ክፍል ዳይረክተር አቶ ግሬግ ቡርከ ተናግረዋል።

ከወጣቶች ደስታ ሲፈልቅ፣

በጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት፣ በካናዳ የኪበክ ሊቀ ጳጳሳይ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ጀራርድ ሲፕሪያን በበኩላቸው በብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ መካከል የሚታየው የግልጽ ውይይት መንፈስ እንዳስደሰታችው ገልጸው ከወጣቶች ጋር ሆነው አዲስ የወደ ፊት አቅጣጫን ለማቀድ መነሳታቸውን አስረድተው በብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ 15ኛ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ ላይ የተገኙት ወጣቶች ቁጥር ከሰላሳ ትንሽ የሚበልጥ ቢሆንም ሃሳባቸውን ከምንጠብቀው በላይ በደስታ እየገለጹ መሆናቸውን አስረድተው የዚህን ብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ፍሬን የሚሰበስብ አንድ ወገን ብቻ ሳይሆን መላዋ ቤተክርስቲያን እንደምትሆን ገልጸዋል።

ብጹዓን ካርዲናሎች ለወጣቶች የቪዲዮ መልዕክት ያስተላልፋሉ፣

በብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ መጀመሪያ ላይ ከተለያዩ የሲኖዶሱ አባቶች በቀቡት ጥያቄዎች መሠረት፣ የጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት፣ ካርዲናሎችና ጳጳሳት የሚሳተፉበት የቪዲዮ ምልዕክት ስርጭት እንደሚቀርብ  በቅድስት መንበር የመገናኛ ክፍል ተጠሪና የሲኖዶስ ዜና ክፍል አስተባባሪ አቶ ፓውሎ ሩፊኒ ገልጸዋል።            

09 October 2018, 18:39