ፈልግ

2018.10.03 Apertura lavori Sinodo 2018.10.03 Apertura lavori Sinodo 

ወጣቶች የጊዜውን እውኔታ ቶሎ የሚገነዘቡ የቤተክርስቲያን ተዋናዮች መሆናቸው ተገለጸ።

የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣ ወጣቶች በዲጂታል ባሕል ዘልቀው በመግባት ለማሕበራዊ ሕይወታቸው የሚያገለግሉ መረጃዎችን የሚያገኙትን ያህል የሚጎዱ መረጃዎችንም እንደሚያገኙበት ገልጸው ይህን የመገናኛ መንገድን ከሚፈለገው በላይ የሚያዘወትሩ ከሆነ ወደ ብቸኝነት ሕይወት እንደሚዳርጋቸው ሲኖዶሱ አስረድቷል። ወጣቶች ወደዚህ ደረጃ ከመድረሳቸው በፊት ትክክለኛ የዲጂታል የመገናኛ መሳሪያዎች አጠቃቀምን ቤተክርስቲያን ወጣቶችን ማስተማር እንዳለባት አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ወጣቶች እምነትና ጥሪያቸውን በጥበብና በማስተዋል እንዲያውቁት በሚል የመወያያ ርዕስ ላይ ጉባኤውን የከፈተው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ትናንት ባካሄደው ውይይቱ ቤተክርስቲያን ከወጣቶች ጋር ሳታቋርጥ የምትወያይ፣ ወጣቶችን የምታዳምጥ፣ ለወጣቶች ሕይወት ትኩረት የምትሰጥ፣ ለወጣቶች የቤተክርስቲያን ተሳትፎ ዋጋንና ክብርን የምትሰጥ መሆን አለባት ብለው ይህ ከሆነ ብቻ ወጣቶች ወንጌልን ለጓደኞቻቸው መመስከር እንደሚችሉ የሲኖዶሱ አባቶች አስረድተዋል።

ወጣቶች በራሳቸው ቤተክርስቲያን መሆናቸውን የገለጸው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኒዶስ፣ እግዚአብሔር ለወጣቶች የሰጣቸው ሕይወት  በተስፋ እንዲኖሩ የሚደርግ ጥሪ በመሆኑ ይህን ጥሪ እንዲገነዘቡትና እንዲያውቁት ማገዝ ያስፈልጋል ብለው ወጣቶች በሕይወታቸው መካከል ወደ ውሳኔ ለመድረስ ችሎታና ብቃት ቢኖራቸውም ቤተክርስቲያን በደስታ ስሜት ልታግዛቸው ያስፈልጋል ብለዋል።

ወጣቶች በዲጂታል ዓለም፣

የዲጂታል ዓለም ባሕልን በማስመልከት ውይይት ያደረገው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣ ወጣቶች በዲጂታል ባሕል ዘልቀው በመግባት ለማሕበራዊ ሕይወታቸው የሚያገለግሉ መረጃዎችን የሚያገኙትን ያህል የሚጎዱ መረጃዎችንም እንደሚያገኙበት ገልጸው ይህን የመገናኛ መንገድን ከሚፈለገው በላይ የሚያዘወትሩ ከሆነ ወደ ብቸኝነት ሕይወት እንደሚዳርጋቸው ሲኖዶሱ አስረድቷል። ወጣቶች ወደዚህ ደረጃ ከመድረሳቸው በፊት ትክክለኛ የዲጂታል የመገናኛ መሳሪያዎች አጠቃቀምን ቤተክርስቲያን ወጣቶችን ማስተማር እንዳለባት አሳስበዋል። ከዚህም ጋር በማያያዝ በገጠራማው የዓለማችን ክፍሎች የሚገኙ ወጣቶች የኢንተርኔት አገልግሎት እንደማያገኙ የሲኖዶሱ አባቶች ገልጸዋል።

ስጣንን መከታ አድርጎ መባለግ፣

ቤተክርስቲያን በምዕመናኖቿ በኩል እምነትን እንድታጣ ከሚያደርጉ የተሳሳቱ አካሄዶች መካከል ወሲባዊ ጥቃቶች መኖራቸውን የተረዱት የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እነዚህ የተሳሳቱ አካሄዶች ቤተክርስቲያንን ምን ያህል እንደጎዱ በመገንዘብ ሁለተኛ እንዳይደገሙ ለማድረግ ጥብቅ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስበው፣ ጥቃቱ የተፈጸመባቸውን በመርዳት የምሕረትና የይቅርታን መንገድ ማመቻች እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

ስደትና መንስኤው፣

የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ በትናንትው ዕለት ባደረገው ውይይቱ ስደት የበርካታ ወጣቶች ሕይወት እንደጎዳ አስታውሰው፣ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ ፍትህንና ትክክለኛ ፖለቲካዊ ለውጦችን እንዲያደርጉ ከተለያዩ አገሮች መንግሥታት ጋር ውይይት ማድረግ እንደምትችል ተጠቁሟል። ይህን ውይይት ስኬታማ ለማድረግ በየአገሩ የሚገኙ የብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመሆን ስለ ስደት እና ለስደት ምክንያት ናቸው በሚሏቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠይቀዋል። ሲኖዶሱ በማከልም ለስደተኞች ሊሰጥ ስለስሚገባው መስተንግዶና ሕጋዊ ከለላን በተመለከተ ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ጋር ዘላቂ ስምምነት ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስበው በአንዳንድ አገሮች ውስጥ በሚነሱ ግጭቶች ምክንያት መፈናቀል፣ መከራና ስቃይ የሚደርስባቸዋ በርካታ ሕዝቦች መኖራቸው መዘንጋት እንደሌለበት አስታውሰዋል።

ጥራት ያለው ሰፊና ሁለገብ ትምህርት ማዳረስ፣

ወጣቶች የሚቀስሙት የትምህርት ዓይነቶች ጥራት ያላቸው ሰፊና ሁለ ግብ መሆን እንዳለባቸው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በትናንትናው ዕለት ከተወያየባቸው ርዕሶች መካከል አንዱ እንደሆነ ታውቋል። በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የሚተዳደሩ፣ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የሚገኙ የትምሕርት ተቋማት የወጣቶችን ስነ ምግባር በማነጽ ወደ ተሻለ የሕይወት ደረጃ እንዲደርሱ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ሲኖዶሱ አሳስቧል።

 

10 October 2018, 18:52