ፈልግ

የ15ኛው አጠቃላይ መደበኛ የብጹዕን ጳጳሳት ሲንዶስ ማጠቃለያ  የ15ኛው አጠቃላይ መደበኛ የብጹዕን ጳጳሳት ሲንዶስ ማጠቃለያ  

የ15ኛው አጠቃላይ መደበኛ የብጹዕን ጳጳሳት ሲንዶስ ሰነድ አጠቃላይ ይዘት

ክፍል አንድ

ከባለፈው መስከረም 23/2011 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 18/2011 ዓ.ም “ወጣቶች፣ እምነት እና በጥሪ ላይ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረው 15ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ መደበኛ የብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ  በጥቅምት 18/2011 ዓ.ም መጠናቀቁ ይታወሳል። ይህ 15ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ መደበኛ የብጹዕን ጳጳሳት ሲንዶስ ሲጠናቀቅ በሦስት ክፍሎች የተከፈለ፣ 12 ምዕራፎችን የያዘ፣ 167 አንቀጾችን እና በአጠቃላይ 60 ገጾች ያሉት ሰንድ በጥቅምት 17/2011 ዓ.ም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ተፈርሞ ይፋ የተደረገ ሲሆን ይህ 15ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ በጥቅምት 28/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በተካሄደው የማጠቃለያ መስዋዕተ ቅዳሴ መጠናቀቁ ይታወሳል።

የዚህ ዘገባ አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ይህ 15ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የብጹዕን ጳጳሳት መደበኛ ሲኖዶስ ማጠቃለያ ሰነድ በማጣቀሻነት የተጠቀመው በሉቃስ ወንጌል 24፡13-35 ላይ የተጠቀሰውን የኤማሁስ መንገደኞች ታሪክ ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን “እነሆም፥ ከእነርሱ ሁለቱ በዚያ ቀን ከኢየሩሳሌም ስድሳ ምዕራፍ ያህል ወደሚርቅ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር ይሄዱ ነበር፤ ስለዚህም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር። ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር” በምለው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተችሉዋል።

መግቢያ

“ኢየሱስም አብሮዋቸው ይሄድ ነበር”

ወደ ኤማሁስ በመጓዝ ላይ የነበሩ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ታሪክ የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ከወጣቱ ትውልድ ጋር አብሮ መጓዝ እንደ ሆነ በንድፈ ሐሳብ ደረጃ ያስቀምጣል፣ ያስተምራልም። ይህን የቅዱስ ወንጌል ክፍል አሁን በተጠናቀቀው በዚሁ በ15ኛ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ ላይ የተለማመድነው ሲሆን፣ ይህንንም ዛሬ ባለቺው ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በመተግበር ቤተ ክርስቲያን በተለይም ደግሞ ከወጣቶች ጋር ያላትን ግንኙነት አጠናክራ መቀጠል እንደ ሚገባት እና እንደ ምትፈልግም ያሳያል። ኢየሱስ የእርሱን ስቃይ፣ ሞት እና ትንሳሄ ለመረዳት አዳግቱዋቸው ኢየሩሳሌምን እና ሌሎች ደቀ መዛሙርትን ጥለው ወደ ገዛ ሀገራቸው ወደ ኤማሁስ በመጓዝ ላይ ከነበሩ ሁለት ደቀ መዛሙርት ጋር አብሮ ሲጓዝ እናያለን። ኢየሱስም አብሮዋቸው ለመሆን በማሰብ ከእነሩሱ ጋር ይጓዛል። ኢየሱስም እነዚህ ሁለት የኤማሁስ መንገደኞች “በመንገዳቸው ላይ ስለምን እያወሩ እንደ ሆነ በመጠየቅ” ፣ እነርሱም ስለምን እያወሩ እንደ ሆነ በዝርዝር ለእርሱ በሚተርኩበት ወቅት እነርሱ በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ፣ ምን ዓይነት ችግር እንደ ገጠማቸው፣ በምን ዓይነት ተግዳሮት ውስጥ እየኖሩ እንደ ሆነ ለማወቅ እርሱ በትዕግስት እያዳመጣቸው አብሮዋቸው ይጓዝ ነበር። እነሩሱ የገጠማቸውን ነገር በዝርዝር ካስረዱት በኋላ ኢየሱስ በተራው በታላቅ ኃይል እና ርኅራኄ እነዚህ ሁለት የኤማሁስ ደቀ መዛሙርት የገጠማቸውን ተግዳሮት ቅዱሳን መጽሐፍትን በማጣቀስ ትርጓሜያቸውን አንድ በአንድ ማስረዳት ይጀምራል። እነርሱም ወደ መንደራቸው በደረሱ ጊዜ መሽቶ ስለነበር እርሱ ከእነርሱ ጋር ምሽቱን እንዲያሳልፍ ያቀረቡትን ግብዣ ኢየሱስ ይቀበላል፣ አብሮዋቸውም ወደ ቤት ይገባል። እርሱ ቅዱሳን መጽሐፍትን እያጣቀሰ ስያስተምራቸው በነበረበት ወቅት ልባቸው ይቃጠል ነበር፣ አዕምሮዋቸውም በብርሃን ተሞልቶ ነበር፣ እንጀራን አንስቶ በቆረሰበት ወቅት ዓይናቸው ተከፍቶ ነበር። በዚህም ምክንያት ማንም ሰው ሳያስገድዳቸው በራሳቸው ፈቀድ ወደ ነበሩበት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፣ ከሌሎች ደቀ መዛሙርት ጋር ተመልሰው ተቀላቀሉ፣ ኢየሱስን በተገናኙበት ወቅት የነበረውን ሁኔታ ሁሉ ለቀሪዎቹ ደቀ መዛሙርት በዝርዝር አስረዱ።   

ቤተ ክርስቲያን ለወጣቱ ትውልድ ትኩረት መስጠት ይኖርባታል

ይህ 15ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ መደበኛ የብጹዕን ጳጳሳት ሲንዶስ ሲጠናቀቅ ይፋ የሆነው የማጠቃለያ ሰንድ ይህንን ወደ ኤማሁስ ሲጓዙ የነበሩትን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ታሪክ ከግምት ባስገባ መልኩ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን በቀዳሚነት “ከእነርሱ ጋር አብሮዋቸው ይጓዝ ነበር” (ሉቃ. 24፡15) የሚለው የሰነዱ የመጀመርያ ክፍል እንዲሆን ተደርጉዋል።

ይህም የሆነበት ምክንያት በዚህ 15ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ መደበኛ የብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ ተካፋይ የነበሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይህንን የኤማሁስ መንገደኞች ታሪክ ከግምት በማስገባት ልክ ኢየሱስ እንዳደርገው ቤተ ክርስቲያን ለወጣቱ ትውልድ ትኩረት በመስጠት፣ አብራ በመጓዝ ወጣቱ እምነትን በተመለከተ ያለውን ማነኛውም ዓይነት ጥያቄን በቅዱሳን መጽሐፍት ብርሃን በመተርጎም እና በማስረዳት ወጣቱ በእመነት ጎዳና ላይ በምያደርገው ጉዞ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን አብራ መጓዝ እንዳለባት አጽኖት ለመስጠት በማሰብ የመረጡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሲሆን በዚህም መስረት የዚህ 15ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ መደበኛ የብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ የማጠቃለያ ሰንድ የመጀመርያው ክፍል “ከእነርሱ ጋር አብሮ ይጓዝ ነበር” (ሉቃ. 24.15) በሚል ጭብጥ ዙርያ ላይ እንዲያጠነጥን ተደርጉዋል።

“ዓይናቸው ተከፈተ”

በተመሳሳይ መልኩም የዚህ 15ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ መደበኛ የብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ ማጠቃለያ ሰነድ ሁለተኛ ክፍል “ዓይናቸው ተከፈተ” (ሉቃ.24.31) በሚለው ዐረፍተ ነገር ዙሪያ ላይ እንዲያጠነጥን የተደረገ ሲሆን ይህም በሲኖዱሱ ወቅት የነበሩ መሰረታዊ ጥያቄዎች በሙሉ በጥንቃቄ እና በቅዱስ ወንጌል ብርሃን በመታገዝ ትክክለኛ ትርጓሜያቸውን ማግኘታቸውን ለመግለጽ ታስቦ የተጠቀሙበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው። የ15ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ መደበኛ የብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ ማጠቃለያ ሰነድ ሦስኛው ክፍል የምያጠነጥነው አሁንም በሉቃስ ወንጌል (24፡13-35) ላይ በተጠቀሰው የኤማሁስ መንገደኞች በነበሩ ሁለት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ዙሪያ ላይ እንደ ነበር ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህም መሰረት “በዚያችም ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ” (ሉቃ. 24፡33) በተጠቀሰው ቃል ዙርያ ላይ ያጠነጠነ ሲሆን ይህም መንፈሳዊ፣ ሐዋርያዊ እና ሚስዮናዊ ለውጥ ለማምጣት የሚደረገውን የግል ምርጫ እና ውሳኔ ያሳያል።

ክፍል አንድ

“አብሮዋቸው ይጓዝ ነበር”

“እነሆ፥ ከእነርሱ ሁለቱ በዚያ ቀን ከኢየሩሳሌም ስልሳ ምዕራፍ ያህል ወደሚርቅ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር ይሄዱ ነበር፤ ስለዚህም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር። ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር” (ሉቃ 24. 13-15)። በዚህ ምንባብ ውስጥ ወንጌላዊው ሁለቱ ተጓዦች በገጠማቸው ክስተት እና ተግዳሮት መረበሻቸውን በማውሳት ለችግሮቻቸው መፍትሄ እንደ ምያስፈልጋቸው ያሳያል። በዚህም አግባብ በመጓዝ ላይ በነበሩበት ወቅት ኢየሱስ የመፍትሄው አካል እንዲሆን በማሰብ ከእነርሱ ጋር አብሮ መጓዝ እንደ ጀመረም ወንጌላዊው ይገልጻል። ይህም ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ችግሮች፣ ግራ መጋባቶች፣ተስፋዎችን ስንቀው ከሚጓዙ ከእያንዳንዱ ወጣት ጋር አብሮ እንደ ምጓዝ ያሳያል። ኢየሱስ አብሮ ይጓዛል፣ያዳምጣል ሐሳቡን ያካፍላል።

የ15ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ መደበኛ የብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ ማጠቃለያ ሰነድ የመጀምርያ ክፍል በዚሁ “ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር” በሚለው ሀረግ ዙርያ እንዲሆን የተደረገበት ምክንያት በአሁኑ ወቅት ወጣቱ ትውልድ እየኖረው የሚገኘውን ነባራዊ ሁኔታ በማመላከት ጥንካሬዎቻቸውን እና ችግሮቻቸውን ያጎላል። ሁሉም ነገር የሚጀምረው በትዕግስ፣ በርኅራኄ እና በትህትና በማዳመጥ ሊሆን እንደ ሚገባው በማውሳት ይህም ከወጣቱ ትውልድ ጋር ለሚደርገው ማነኛውም ዓይነት ውይይት ሰፊ የሆነ መንገድ የሚከፍት እና እንዲሁም ቀደም ሲል “ዝግጁ ሆነው የተቀመጡ” መልሶችን ከመስጠት ይታደጋል። በእርግጥ ወጣቶች “መደመጥ፣ እውቃናን ማግኘት እና መታጀብ” ይፈልጋሉ፣ ከእዚያም ባሻገር ወጣቶች ድምጻቸው “በቤተ ክርስቲያን እና በማኅበራዊ መስኮች ውስጥ” ሳይቀር ድምጻቸው እንዲሰማ እና አስፈላጊ መሆናቸውን ለማወቅ ይፈልጋሉ። ብዙን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ዓይነት ባሕርይ የላትም የሚለውን ወቀሳ 15ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ የብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ የተቀበለው ወቀሳ ሲሆን ብዙን ጊዜ ጳጳሳት እና ቀሳውስት በተሰጣቸው ሐዋርያዊ ተልዕኮዎች ላይ ብቻ ትኩረት የምያደርጉ በመሆናቸው የተነሳ ወጣቱን የማዳመጫ ጊዜ እንደ ሌላቸው ሲኖዶሱ ገልጹዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!

 

30 October 2018, 14:05