ፈልግ

cardinale Fernando Filoni cardinale Fernando Filoni 

ብጹእ ካርዲናል ፈርናርዶ ፊሎኒ ለብጹኣን ጳጳሳት በተዘጋጀው ዓውደ ጥናት ላይ ተገኙ።

በዚህ ዓውደ ጥናት ላይ ኣዲሶቹ ጵጳሳት ከቤተክርስቲያኗ ጋር በተያያዙ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ በጥልቀት ይወያያሉ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - የኢትዮጵያ ጳጳሳዊ ኮሊጅ - ቫቲካን

ብጹእ ካርዲናል ፈርናርዶ ፊሎኒ በሓዋርያዊ ተልዕኮ ግዛት ውስጥ ለሚሰሩ ብጹኣን ጳጳሳት ስለ ፎርሜሽንና ማጋራት ወይም ስርጭት ላይ በተዘጋጀው ዓውደ ጥናት ላይ መመልከቱ ታውቋል። ይህ ወንጌልን በዓለም ሁሉ ለማዳረስ በተቋቋመው ቢሮ ኣማካኝነት በተዘጋጀው ሴሚናር ላይ በተደረገው ቃለ ምልልስ ካርዲናል ፊሎኒ እንዳብራሩት የዓውደ ጥናቱ ተቀዳሚ ግብና ዓላማ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የጵጵስና ማዕረግ የተቀበሉ ጳጳሳት በጥልቀት የጵጵስና ኣገልግሎት ምንነትን መረዳት በቤትክርስቲያን ውስጥ ስለሚከናወኑት የተለያዩ ክንውኖች በቂ ግንዛቤ ማዳበርና ከዚሁም ጋር ኣብሮ ከሮማ ኩሪያ ጋር የጠበቀ ግንኙንት መፍጠርና ስለሚያከናውናቸው ተግባራት መረዳት እንዲሁም የተለያዩ ልምዶችን መለዋወጥ መሆኑን የቫቲካን ከተማ የሬዲዮ ኣገልግሎት ባልደረባ ዲቦራ ዶኒኒን ዋቢ በማድረግ ጠቅሷል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የተሾሙት 75 አዳዲስ ጳጳሳት በተልዕኮ ግዛቶች ውስጥ በሚካሄዱት ሓዋርያዊ እንቅስቃሴ እንዴት ኣድርገው ቤተክርስቲያንን እንደሚመሩና የልምድም ልውውጥ እምደሚያደርጉ እድል የሚፈጥር ነው። ይህ ዛሬ ጥዋት ማለትም እንደ እውሮፓውያኑ ዘመን ኣቆጣጠር መስከረም 4 2018 በሮሜ በሚገኘው በደብረ ጳጳሳት ጳጳሳዊ ኮሌጅ የተከፈተው ዓውደ ጥናት ዋና ዓላማ መሆኑ ተገልጿል። ኤጲስ ቆጶሶቹ ከአራት አህጉራት ማለትም ከአፍሪካ ከእስያ ከላቲን አሜሪካ እና ከኦሽንያ የመጡ ናቸው ቅዳሜ መስከረም 15 መስከረም 2018 እንደ እውሮፓውያኑ ዘመን ኣቆጣጠር የሚጠናቀቅ ሲሆን በነዚህ የስብሰባ ቀናት ፀሎቶች እና የተለያዩ ዘገባዎች በየቋንቋ ቡድኖቹ መሠረት እንደሚከናወኑ ታውቋል። (ኣዲስ ለተሾሙት ጳጳሳት የተደረገውን ዓውደ ጥናት ኣስመልክቶ ከካርዲናል ፊሎኒ ጋር የተደረገውን ቃለ መጠይቅ ያዳምጡ)

የተለያዩ ስልጠናዎችን በተመለከተ

በዚህ ዓውደ ጥናት ላይ ኣዲሶቹ ጵጳሳት ከቤተክርስቲያኗ ጋር በተያያዙ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ በጥልቀት ይወያያሉ በዚህ ሴሚናር ላይ የወንጌል ስርጭት ቢሮ ዋና ጸሐፊ ሞንሲኞር ፕሮታሴ ሩጋምብዋ እንዲሁም ተተባባቂ ዋና ጸሐፊ ጆቫኒ ፒየትሮ የቅድስት መንበር የተልዕኮ ተግባሮች ዋና ጸሐፊ እንዲሁም የተለያዩ የቅድስት መንበር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ካርዲናሎች ከሚመሩት ቢሮ ኣኳያ እንዲሁም ባህርያት ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ይነጋገራሉ።

በተጨማሪ የተለያዩ ጳጳሳትና ኤጲስ ጵጳሳት እንደ ፖል ሪቻርድ ጋለገር የህዝባዊ ግንኙነት አስፈፃሚ, እንዲሁም ጁኣን አኛዚዮ አሪኤታ የሕግ ምክር ቤት ፀሐፊ ሌሎችም እንደሚሳቱፉበት ታውቋል። በቡድኑ ሪፖርቶች ውስጥ የሞንሲኞር ዳርዮ ኤድዋርዶ ቪጋኖ በመገናኛ ብዙሃን ወንጌላዊ ስርጭት ዘዴን መጠቀም ስለመቻል እንዲሁም የኣባ ሃንስ ዞልነር እድሜያቸው ለኣቅመ ኣዳም ያልደረሱትንና እና ለተላያዩ ሰባዊና

ኣካላዊ ኣደጋ ለተጋለጡ አዋቂዎች ጥበቃን በተመለከተ እንዲሁም የሞንሲኞር ጉዊዶ ማሪኒ ስለ በቤተክርስቲያን ሥነ-ስርዓት እና ቅድስና በተመለከተ ውይይት እንደሚደረግ ታውቋል።

ካርዲናን ፊሎኒ ኣያይዘውም ከተለያዩ ኩሪያዎች ጋር የበለጠ ለመተዋወቅ እና እድል ለመስጠት ያህል በዚህ ጠዋት ዓውደ ጥናቱ ሲከፈት የወንጌል ኣገልግሎት ሥርጭት የበላይ ጠባቂ የሆኑት ካርዲናል ፈርናንዶን ፊሎኒ የዓውደ ጥናቱን ተቀዳሚ ዓላማና ተግባር በዝርዝርና በተናጠል ኣብራርተዋል።

ካርዲናሉ በመቀጠልም በተለምዶ ይህ የወንጌል ኣገልግሎት ሥርጭት ቢሮ ይህንን ዓውደ ጥናት በየሁለት ዓመቱ ለአዲስ ጳጳሳት የሚያዘጋጅ እና ኣዳዲስ ጵጳሳቱ በተለያዩ የቤተክርስቲያኗ ኣካሄዶችና ከንውኖች የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። በዚህ ዓውደ ጥናት የሚሳተፉት ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የወንጌል ሥርጭት ግዛቶች ሐዋርያዊ ኣስተዳደር ግዛቶች የተሰበሰቡ ሲሆኑ ይህ ኣጋጣሚ ለተሰብሳቢዎቹ ስለ ሮማን ኩሪያ የበለጠ ግንዛቤ የሚያስጨብጥና እንደዚሁም ደግሞ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚያበረክቱትን ኣገልግሎት በቅርብ ለማጤን የሚያግዝ መሆኑን ኣክለውበታል። እዚህ በሮም ውስጥ ባሉ ሁሉም መሳሪያዎች እንዲሁም ልዩ ባለሙያተኞች ባሉበት የተሰብሳቢዎችን የተለያዩ ጥያቄዎችና ውይይቶች በማዳመጥ እንዲሁም ጥያቄዎችን በመጠየቅ በቤተክርስትያን አመራር ውስጥ ያለዉን ውስብስብ እውነታን በቅርብ ሆኖ ለማየትና ከዚህም ጋር ራሳቸውን የበለጠ እንዲያቀራርቡ እርስ በርሳቸውም እንዲተዋወቁ እድል ይሰጣቸዋል ብለዋል።

እነዚህ ጳጳሳት በተራራቁና በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ ይሰራሉ ስለሆነም እነዚህን በተለያዩ በወንጌል ሥርጭት ኣገልግሎት የሚሰሩትን ጳጳሳቶች ማሠልጠን የምትፈልጉበት ማዕከላዊ እና የጋራ ነጥቦቹ ምንድን ናቸው ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲያስረዱ

ይህ ዓውደ ጥናት በተለያዩ የቫቲካን ከፍተኛ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ የተለያየ የሥራ ኃላፊነት ያላቸው እና በነገሩም ላይ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ባላቸው ሰዎች ኣማካኝነት የሚካሄድ ነው እነዚህ ዘርፎችም በአካባቢው ያሉ አብያተ ክርስቲያናትንም የሚመለከቱ ናቸው ስለዚህ በርዕሰ-ጉዳዩ ላይ ከመጀመሪያው የመግቢያ ክፍል በተጨማሪ, ጳጳሳቱ ጠለቅ ያለ ውይይት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩና ሓሳብ እንዲንሸራሸር ይደረጋል። እነዚህ ጳጳሳት የመጡት ጳጳስ ሆነው ከሚያስተዳድሩት ሕዝብና ክልል በመሆኑ በየኣካባቢያቸው ያለውን እውነታና ነባራዊ እንቅስቃሴ በሚገባ ይረዱታል። በእነዚህ የመጀመሪያ ሁለት የጵጵስና ዓመታት ሁሉም የየራሳቸው ክልሎች ልምድ ስላላቸው, በሚኖራቸው ተሞክሮ እንዲሁም ልምድ ልውውጥ የተለያዩና ጠቃሚ ሓሳቦችን ሊለዋወጡ ይችላሉ ስለዚህ ሁሉም ከተለያየ ቦታ እንደመምጣታቸው ልዩነቶችና የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩም ይህ ለሁሉም በተለያዩ ሓሳቦች ላይ ግልፅ የሆነና የበለጠ ግንዛቤ ለማግኘት እድል ይሰጣል ለሁሉም የዓውደ ጥናቱ ተካፋዮች የሌሎችን ልምዶች ማወቅ ሌሎች ተመሳሳይነትና ልዩነት ያላቸውን እሴቶች መመልከትና ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ትኩረት ሰተን ልንመለከተው እንደሚገባ ኣስረድተዋል።

03 September 2018, 17:46