ፈልግ

በሶርያ እና በኢራቅ እየደረሰ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ በተመለከተ ስብሰባ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - የኢትዮጵያ ጳጳሳዊ ኮሌጅ፣ ቫቲካን

በሶርያ እና በኢራቅ እየደረሰ ባለው ሰብአዊ ቀውስና እንዲሁም ስደተኞችን በፈቃደኝነት ወደ ሃገራቸው መመለስ በሚል መሪ ቃል ባዛሬው ዕለት በቫቲካን ከተማ ውይይት ተጀምሯል። ይኸው በሰው ኣጠቃላይ ሰብኣዊ እድገት ላይ የሚሰራው ቢሮ እንዳስታወቀው ይህ ስብሰባ ከሁሉ በላይ ቅድሚያ ሰጥቶ የሚወያይበት ጉዳይ በፈቃደኝነት ወደ ሃገራቸው መመለስ ስለሚፈልጉ ተፈናቃዮች መሆኑን ኣስታውቋል። በቀጠልም ሞንሲኞር ሰጉንዶ ቴጃዶ እንዳስታወቁት ለጉዳዩ አፋጣኝ መልስ መስጠት ግንባር ቀደም ተግባር ቢሆንም የተፈናቃዮቹንም ሥነ-ልቦናዊ ይሁን ኣካላዊ ጉዳት መፈወስም እንደሚያስፈልግ መነሳቱን የቫቲካን ከተማ የሬዲዮ ኣገልግሎት ባልደረባ ቼቺሊኣ ሴፒኣን ዋቢ በማድረግ ጠቅሷል።

በዚሁ መስከረም 13 እና 14 2018 ዓ.ም. እ.ኣ.ኣ. በቫቲካንና ባኡርባኒኣና ዩኒቨርሲቲ ዮሓንስ ጳውሎስ 2ኛ ኣዳራሽ በሰብኣዊ ሁለንተና ዕድገት ቢሮ በኩል በተዘጋጀው በሶርያ እና በኢራቅ እየተከሄደ ባለው ሰብአዊ ቀውስና እንዲሁም ስደተኞችን በፈቃደኝነት ወደ ሃገራቸው መመለስ በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው ስብሰባ ላይ 50 የሚሆኑ የካቶሊክ በጎ አድራጎት ድርጅቶች የአካባቢያዊው ኤጲስ ቆጶሳት የህዝብ ተቋማት እና የሃይማኖት መሪዎች ተወካዮች እንዲሁም የሶሪያ ኢራቅ የሊባኖስና የቱርክ የር.ሊ.ጳ. ተወካዮች እንደሚሳተፉ ታውቋል።

ለተለያዩ መጠይቆች መልስ ስለመጠት

ሞንሲኞር ሰጉንዶ ቴጃዶ በቫቲካን የሰው ኣጠቃላይ ሰብኣዊ እድገት ቢሮ ተጠባባቂ ጸሓፊ እንደገልጹት እዚህ የተሰብሰብን ሁላችን በሰውም ሆነ በሃብትና በመሳሰሉት ብዙ ነገሮችን መሥራት እንችላለን ምክንያቱም ሁላችን በኣንድም ሆነ በሌላ መልኩ በኣንድ ቤተክርስቲያን ሥር ሆነን ኣገልግሎት መስጠት ላይ እንገኛለንና ነው ብለዋል። ይህ ስብሰባ እርስ በእርሳችን እንድንተዋወቅና እንድንተያይ ብሎም የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን ለማንሳትና ልምዶችን ለመለዋወጥ እጅግ በጣም ጥሩ ኣጋጣሚ ይፈጥርልናል ብለዋል። ከዛም በመቀጠል ሲናገሩ እኛ አንደዚህ መሆን ኣለበት ብለን ኣስቅድመን የምንወስነው የምናደርገው ነገር ባይኖርም ቅሉ የተለያዩ ሓሳቦችን በተለይም ደግሞ በቦታው ላይ ካሉ ቤተክርስቲያኖች ጋር በመነጋገር የሚመጡትን ሓስቦች በሙሉ ሚዛን ላይ በማስቀመጥ በቅድሚያ ሊሰሩ የሚገባቸውን ሥራዎች ለይቶ በማወቅና ቅድሚያ በመስጠት የወንድማማችነትና የአሰራርን ሁኔታ ለማዳበር እንደሚያስችል ተብራርቷል።

የስደተኞች ወደ ሃገራቸው መመለስ

በዚህ ዓመት የበለጠ ትኩረት ሰተን ይምንንቀሳቀስበት ጉዳይ ቢኖር ይህን ስደተኞችን በፈቃደኝነት ወደ ሃገራቸው ወደ ትውልድ ቄኣቸው የመመለስ ጉዳይ ነው ይላሉ ሞንሲኞር ቴጃዶ። ከዚህ ቀደም በነበሩ ዓመታት ኣብዛኛዉን ጊዜ ትኩረት እናደርግ የነበረው ከካሪታስ ጋር በመተባበር በሰብኣዊ እርዳታዎች ማለትም

በተለያዩ ችግር ባለባቸው ኣካባቢዎች ላይ የምግብ ኣቅራቦትን መሸፈን የመድሃኒትና የመገልገያ ቁሳቁሶችን ማቅረብ ነበር ምክንያቱም በዚህ ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የዕርዳታ ድርጅቶች እምብዛም ስለነበሩ ነው። በእርግጥ ስደተኞችና ተፈናቃዮችን ወደ ነበሩበት ቦታ መልሶ ለማስፈር በሚመለሱበት ቦታ ያለዉን የሰላምና የጦርነት ሁኔታ በደንብ መመልከትና ማሰብ ያስፈልጋል በተለይም በጆርዳን በሊባኖን እና በቱርክ ያሉት ስደተኞችና ተፈነቃዮች።

ሸሽተው ወተው ከተሰደዱባቸው ቦታዎች ስለመመለስ የሚለው ኣጀንዳ ብዙ ጊዜ ሲወራ ይሰማል። ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ለዚሁ ጉዳይ የቆሙ ቢሮዎች ኣሉ። እነዚህ ኤጀንሲዎች ወይም ቢሮዎች የበለጠ እንዲገነዘቡና በጉዳዩም ላይ ጠንክረው እንዲሰሩ ለማድረግ የሚያስችሉ እገዛዎች እንደሚኖሩ ተስፋ እናደርጋለን ብለው ኤጀንሲዎች ወይም ቢሮዎች ያቀዷቸውን ዕቅዶች እንዴት ኣድርገው ተፈፃሚ እንደሚያደርጉና በጉዳዩም ዙሪያ የፖለቲካ የዓለም ኣቀፍና የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን ሁኔታዎች ማጥናት እንደሚያስፈልግ ኣስምረውበታል። በመቀጠልም ለመመለስ የሚፈልጉ ብዙ ተፈናቃዮችና ስደተኞች ቢኖሩም በተለያዩ ሁኔታዎችም ዙሪያ እርዳታ እንደሚያፈልጋቸው ኣያይዘው ተናግረዋል።

የበጎ አድራጎት ጣልቃ ገብነት ላይ ሪፖርት ስለማድረግ

ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለኣንዱ ያደርጋችሁት ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው በሚል ሓሳብ ከ 2017-2018 ዓ.ም. እ.ኣ.ኣ. በኢራቅና በሶሪያ ለዋለው የሰባዊና የቁሳቁስ እገዛ ይህንን እርዳታ ለሰጡት ለተለያዩ የቤተክርስቲያንና የቤተክርስቲያን ላልሆኑ ድርጅቶች ሪፖርት ማርደጉ ኣስፈላጊ መሆኑን የካሪታስ ኢንተርናሽናል ባልደረባ ሞኢራ ሞናቼሊ ጠቅሳ በሪፖርቱ ውስጥ እርግጠኛ የሆኑ መልሶችን የተከናወኑ የፍቅር ክንውኖችን እንዲሁም የተፈወሱ መንፈሳዊና ቁሳዊ ችግሮችን ማጠንከር ያስፈልጋል ብላለች። በመቀጠልም በሪፖርቱ ላይ እንደተሰማው ከ 2014 ዓ.ም. እ.ኣ.ኣ. በተለያዩ የቤተክርስቲያን ተቋሞች ከ 1 ቢሊኦን ዶላር በላይ በ7 የችግሩ ሰለባዎች በሆኑ ኣገሮች ላይ ከ 4 ሚሊዎን በላይ ተጠቃሚዎችን እንዳሳተፈም ተጠቅሷል።

በ2017/2018 ገንዘቡ በ500 ሚሊዎን ዶላር ጨምሯል ይህም በቤተክርስቲያን የተለያዩ ተቋማት ውስጥ ይህንን እንቅስቃሴ ለማገዝ የማያቋርጥ እና ሰፊ የሆነ ቁርጠኝነትን እንዳለ የሚያሳይ ነው። ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከ 5,800 በላይ ሰራተኞች እና ከ 8,300 በላይ የበጎ ፈቃድ ሰራተኞች በየቀኑ በዚህ ቀውስ ከተጎዱት ጋር ከሚሰሩ ሃይማኖታዊ ተቋማትና ካህናት እንዳሉ ይገመታል። በዚህ ዙሪያ የቤተክርስቲያን ጣልቃ ገብነት ዘርፈ ብዙ ነው። ጣልቃ ገብነቷ በአንዳንድ ዋና ዋና ዘርፎች ማለትም በትምህርት በጤና በስነ-ልቦና በማህበራዊ ድጋፍ እና በቅርብ ዓመታት ውስጥ ስለወደፊቱ በማሰብ ከፍተኛና የተረጋጋ ቤተሰብ ለመፍጠር ለወጣቶች አዲስ የሥራ እድሎች እና ለወጣቶች ስልጠናን ለማቅረብ የሚያስችሉ የኑሮ ዘይቤዎች ላይ መሆኑ ትጠቅሷል።

የፊታችን ዓርብ የስብሰባው ተሳታፊዎች ከ ር.ሊ.ጳ. ጋር ይገናኛሉ

የፊታችን ዓርብ ማለትም መስከረም 14 ቀን 2018 ዓ.ም. እ.ኣ.ኣ. ከምሽቱ 12 ሰዓት ይኸው ቡድን ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጋር በሓዋርያዊ ጽሕፈት ቤታቸው እንደሚገናኝና ስለሶሪያና በጦርነት ስለተጎዱት የተለያዩ ኣገሮች እንደሚነጋገር ታውቋል። ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በተለያየ ጊዜ ስለ ሶሪያና በጦርነት ስለሚጎዱት ሃገሮች ጥሪያቸውን ማሰማታቸው ሞንሲኞር ቴጃዶ ኣስታውሰው በቅርብ ጊዜም ተመሳሳይ ጥሪ ለዓለም ማስተላለፋቸውን ገልጸው የነሱም ቢሮ የሰብአዊ ሁለንተና እድገትን በተመለከተ እስከሆነ ድረስ ይህ የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጭንቀትና ጥሪን ግምት ዉስጥ በማስገባት ሁልጊዜም ኣብረዋቸው እንደሚቆሙና ለመሥራትም የተቻላቸዉን ሁሉ እንድሚያደርጉ ኣስታውቀዋል።

13 September 2018, 17:41