ፈልግ

Papa francesco e Mons Paul Richard Gallagher Papa francesco e Mons Paul Richard Gallagher 

ብጹዕ አቡነ ጋላገር የሰው መብት፣ ኢኮኖሚ፣ ሰላምና ተፈጠሮ ኣንዱ ከሌላው ጋር እንደሚገናኝ ኣስታውቁ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - የኢትዮጵያ ጳጳሳዊ ኮሌጅ፣ ቫቲካን

ከተናንት በስቲያ በታወሰው የ70ኛ ዓመት የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ በቫቲካን የውጭ ጉዳይ ተወካይ በቫቲካን የአውሮፓ ቋሚ ምክር ቤት ኣስተባባሪነት በተዘጋጀው የትራስበርጉ ሲምፖዚየም ላይ መሳተፋቸው ተገለጸ። በዚሁ በተዘጋጀው ሲምፖዚየም ላይ የተቀናጀ የሰው ልማት እና ሁሉን አቀፍ መብቶች ተያያዢነት እንዳላቸው መነጋገራቸውን የቫቲካን ከተማ የሬዲዮ ኣገልግሎት ባልደረባ አድሪኣና ማሶቲን ዋቢ በማድረግ ጠቅሷል።

ይህ የ70ኛ ዓመት የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ ቅድስት መንበር ለስዎች መብት ጠንክራ እየሰራች መሆንዋን እና ይህም እንደ ትልቅ ሃብት የሚቆጠረው የሰው ልጆች መብት በቲዎሪ ብቻም ሳይሆን በተግባርም እንዲተገበር ለማሳሰብ ጥሩ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑ ኣብራርታለች። በቫቲካን የውጭ ጉዳይ ተጠሪ የሆኑት ሞንሲኞር ፖል ሪቻርድ ጋላገር በዚህ በተዘጋጀው የትራስበርጉ ሲምፖዚየም ላይ በተለይም በዓለም ኣቀፍ ደረጃ የሰውን ልጅ መብትን ለማረጋገጥ ችግር የሆኑትን በተለይም ሦስት ነገሮች ኣንጥሮ ማውጣትና ለችግሮቹም ኣጥጋቢ መልስ እንደሚያስፈልግ ኣብራርተዋል።

የመካተት የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶችን ተግዳሮቶች በኣንድነት አለማካተት

እንደ ሊቀ ጳጳሱ ኣመለካከት ችግሮቹ ይላሉ በተለያዩ ቦታዎች ያሉ የሰባዊ መብት ጥሰቶችን የተለያየና የተከፋፈለ ባሕልና ሕብረተሰብ እስካለ ድረስ ኣንድ ወጥ የሆነ ሞዴል ለሁሉም ቦታና ሕብረተሰብ ሊዘጋጅ ኣይችልም ብለዋል።

በዓለም ላይ የተመዘገቡት የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች በተለያዩ ምክንያቶች በምዕራባውያን ህዝቦች ውስጥ እየተመለከትን ነው። በመቀጠልም ኤጲስ ቆጶሱ እንዲህ ይላሉ "በተጋላጭ ሁኔታዎች ውስጥ በሰዎች ላይ የሚከሰተውን የማኅበራዊ መብቶች ተግባራዊነት ቀውስ በአለምአቀፍ ደረጃም እንኳን የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገቱ ቢታደስም ሁሉም ሕዝብ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ኣብራርተዋል።.

ያለ ዴሞክራሲ እና ያለመብት የኢኮኖሚያዊ ዕድገት ምሳሌዎች ወይም የግለሰብ ነጻነትን በማረጋገጥ ላይ የተመሰረቱ ማህበራዊ ሞዴሎች በማኅበራዊ ፍትህ የደካሞችን ሰብአዊ መብት ዓለም አቀፋዊነት አደጋ ላይ እንደሚጥል ገለጹ።

የኣንትሮፖሎጂካል ግጭት ኣደጋ

በማህበረሰባችን ውስጥ እየጨመረ የሚሄደው የባህል መቀላቀል አዲስ ክስተት አይደለም ይላሉ ሊቀ ጳጳሱ ጋላገር በ1948 በተደረገው ዓለም አቀፍ ድንጋጌ ድርድር ሂደት ውስጥ የተለያዩ ባህላዊ እሴቶችና እና ሃይማኖታዊ አመለካከቶች ለማዋሃድ በተደረገው ጥረት ከበድ ያሉ ሁኔታዎች አጋጥሟቸው ነበር። በጊዜዉም ይህ የዓለም አቀፍ የሰው ልጆች መብት ድንጋጌ የምዕራቡን ዓለም ባህላዊ ቅርስ ብቻ የጠበቀ ነው የሚሉም ኣልታጡም።

እኚሁ የቅድስት መንበር የውጭ ጉዳይ ተጠሪ እንዳስቀመጡት እኛ በኣንድ በኩል የዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት መርሆ ላይ የተመሠረተ አንድ ማህበረሰብ የማገዝ ዝንባሌ ነገር ግን በዲሞክራሲያዊና በሰብኣዊ መብት ላይ የተመሠረቱ በሚመስሉ የፖለቲካ ብሔራዊ ርዕዮተ አክራሪነት ላይ የማደግ አዝማሚያ ማንጸባረቅ በሌላ በኩል ደግሞ አውራ የነፃ ባህል ሥር-ነቀል ግለሰባዊ መብቶች በሕጉ እንዲካተቱ የማድረግ ሃሳብ ኣንድ ወጥ የሆነ ሕብረተሰባዊ ሕግ የማምጣቱ ሁኔታ ያጠያይቃል ብለዋል። ሞንሲኞር ጋላገር በተጨማሪ በ ሥነ-ሰብ ውስጥ በሚፈጠረውን ግጭት ምክንያት የሚፈጠረውን አደጋ አስመልክቶ ሉላዊነት እና ሰብዓዊ ተንቀሳቃሽነትን ይበልጥ ግልጽ አድርገዋል።

በብዙ የዓለም ክፍሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች

ለዓለም አቀፍ የመብት እገዳ ሦስተኛው ችግር የዓለምአቀፍ ሥርአት አለመረጋጋት እና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብን የሚያዉኩ ብጥብጥ እና ስልታዊ ጥቃቶች የዓለም አቀፉን ሕብረተሰብ ትኩረት ይሻል። ይህም በወጣው ህግ መሠረት ኣንድ ሥርዐትን የመመስረት ኣቅሙን የሚፈተሽ ነው ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ከሌሎች መንግሥታት ጋር ያለውን ግንኙነት ሲያስረዱ ከሁሉ በፊት የሰውን አጠቃላይ ዕድገት መገንባት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

መልሱ አጠቃላይ ሰብአዊ ዕድገት ማምጣት ነው

ቅድሚያ ትኩረት የተሰጣቸው ፈተናዎች እና የማኅበራዊ ልማት ሞዴል በተመለከተ ሊቀ ጳጳሱ መሠረታዊ የፖሊሲ እና ሲቪል መብቶች እንዲሁም የፖለቲካ እና የሰብአዊ መብቶች በተደጋጋሚ የሚያረጋግጡበት ዓለም አቀፋዊ ድንጋጌዎችን የሚያመለክት ነው። ከኢኮኖሚያዊ ከማህበራዊና ከባህላዊ እይታ አንፃር ሁለቱም ኣንዱ ከሌላው ሊነጠሉ እንደማይችሉ መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው።

እንደ ሞንሲኞር ጋላገር ኣገላለፅ ይህ የሰው ልጅ እድገት የሚለውን መርህ የማረጋገጥ ጉዳይ ነው ብለዋል። ይህንን በተመለከተ ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ 6ኛ ሲናገሩ የኣንድ ሰው ዕድገት የሁሉም ሰው ዕድገት ነው ካሉ በኃላ ኣያይዘው የእያንዳንዱን ሰው መሠረታዊ ነፃነት የማራመድ አላማ ትክክለኛውን ኅብረተሰብ ከመገንባት ጋር ምንም ልዩነት አይኖረውም ብለዋል።

ሃይማኖታዊ ነፃነትና የመንግሥት ገለልተኛነት

ሞንሲኞር ጋላገር ስለ ባሕል ልዩነት ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ በእርግጥ ለምሳሌ የሃይማኖት ነፃነትን ሕግ ብንወስድ ይህ ኣንዱ የሌላዉን ሃይማኖት ማክበሩ ኣንዱ ለሌላው ሃይማኖት ያለውን ክብርና እኩልነት ያሳያል ብለዋል። ነፃነት የሰባዊ መብትን ለመገንባት ከፍተኛ ሚና አለው። እንደ ሞንሲኞር ጋላገር ኣገላለፅ በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ የሚደረገው የመንግሥት ሚዛናዊ ጣልቃ ገብነት መልካም ገለልተኝነትን የተከተለ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ወንድማማችነት ለሰብኣዊ መብት አስፈላጊ ሁኔታ ነው

የሰብአዊ መብት መረጋገጡ ለሰው ልጅ ደህንነትና ለሠላም ግንባታ በቂ አይደለም። ጋላገር በመላው ዓለም እየተፈጸሙ ያሉትን በርካታ ሰባዊ መብት ጥሰቶች በመጥቀስ እንዲሁም በዚህ ድንጋጌ የመጀመሪያ ቁጥር ላይ የተፃፈዉን አመላክተዋል ወንድማማችነት በሰዎች መካከል የሚለውን ሃሳብ በሰው ልጆች መካከል ኣስቀምጠዋል ይህ ወሳኝ ነጥብ መሆኑን ሊቀ ጳጳሱ አስረደተዋል።

የሰብአዊ መብት ግንባታ በሙሉ የወንድማማችነት መብት ነው። የእኔ መብትና የሌሎች መብቶች እርስ በርስ የተሳሰሩ እንደሆኑ መረዳት ያስፈልጋል። ይህ ዛሬም በአውሮፓ የሚታይ እውነታ ነው በስደተኞች ላይ የሚደርሰው ስቃይ ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዳንዶቹን ያስተማርናል ብለዋል።

ሁሉም ነገር ከሥነ-ምህዳር ጋር ትያያዢነት ኣለው

ልማት ሰላም ትብብር የአካባቢ ጥበቃ የሰብአዊ መብቶች ሁሉም ነገሮች የተገናኙ ናቸው ይህ ትምህርት ነው ይላሉ ሞንሲኞር ጋላገር ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ላውዳቶ ሲ ወይም ውዳሴና ክብር ለኣንተ ይሁን ተብሎ በተተረጎመው ሰነዳቸው በተደጋጋሚ ሁሉም ነገር ግንኙነት እንዳለው ኣስታውሰዋል። ሕይወትን ማክበር ፍትሃዊ ኢኮኖሚ እና የመብቶች መረጋገጥ እአዲሁም የጤናና የዲሞክራሲ ግንባታ የፍጥረት ጥበቃ ሁኔታ የፍትህ ማስፋፋትና የሰላም ጥበቃ ሁሉም የተገናኙ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የአሁኑን ዓለም አቀፍ ቀውስ ለማሸነፍ ስለ አጠቃላይ ሥነ-ምህዳር Integral Ecology እንደተናገሩ ተጠቅሷል።

በመጨረሻም ሞንሲኞር ጋላገር ስለ ሰው ልጆች መብት መጠበቅ ሲያብራሩ ልክ እንደ መሠረታዊ ነፃነት እንደ መሠረታዊ ፍትህና እንደ መሠረታዊ የዓለም ሰላም ሊወሰድ ይገባል ብለዋል።

በታኅሣሥ ወር በቫቲካን ዓለም አቀፍ ጉባኤ ይካሄዳል

እ.ኣ.ኣ. ሰኞ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም. የተካሄደው ኮንፈረንስ ዓለም አቀፋዊው የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች 70ኛ ዓመት በሚከበርበት ቀን የተዘጋጀ ሲሆን በዚሁ በያዝነው ዓመት ውስጥ በታኅሣሥ ወር ቫቲካን በዚሁ ዙሪያ በሚዘጋጀው ዓለም አቀፍ ጉባዔ እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።

12 September 2018, 17:49