ፈልግ

አቡነ ኔሜት ታዳጊ ወጣቶች ከር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጋር በነበራቸው ቆያት መበረታታታቸውን ገለጹ

አቡነ ኔሜት ታዳጊ ወጣቶች ከር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጋር በነበራቸው ቆያት መበረታታታቸውን ገለጹ

በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ከ19 ሀገራት የተውጣጡ ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑ በስርዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ከ13-23 የእድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች ማኅበር አባላት  12ኛውን መንፈሳዊ ንግደት ለማድረግ በሐምሌ 24/2010 ዓ.ም ወደ ሮም ከተማ መምጣታቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን እነዚህ ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑ በስርዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ታዳጊ ወጣቶች ማኅበር አባለት በቆይታቸው ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መገናኘታቸውም የሚታወስ ሲሆን ታዳጊ ወጣቶች ለአራት ቀናት ያህል በሮም ከተማ ያደርጉትን ቆይታ አጠናቀው በትላንትናው እለት ወደ እየመጡበት ሀገር ተመልሰዋል።

የዚህ ዜና አጠናቃሪ መብራቱ ኋይሌጊዮርጊስ-ቫቲካን

ይህንን 12ኛውን መንፈሳዊ ንግደት በተመለከተ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ቆይታ ያደረጉት በስርዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ዓለማቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ማኅበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት አቡነ  ኔሜት እንድ አገለጹት በስርዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ዓለም አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ማኅበር አባለት በሐምሌ 24/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እጅግ በጣም መደሰታችውን እና መበረታታታቸውን፣ ታዳጊ ወጣቶቹ በቆይታቸው ትልቅ የእመንት ጸጋን እንደ ተቀበሉ መናጋራቸውንም ጨምረው ገለጸዋል።

“ከራሳችን እና ከቤተሰባችን በመነሳት በዓለም ውስጥ ሰላምን ማስፈን እንደ ሚገባ” ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የሰጡት ማበረታቻ በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ታዳጊ ወጣቶች ማኅበር አባላት በጣም ከተደሰቱባቸው መልእክቶች መካከል ዋነኛው እንደ ሆነ የገለጹት አቡነ ላዲስላቪ ኔሜት ይህ በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ታዳጊ ወጣቶች ዓለማቀፍ ማኅበር በዚህ በ12ኛው  ዓለማቀፍ መንፈሳዊ ንግደት ያደርጉ ከ70 በላይ ወጣቶችን ቀልብ የገዛ አሳብ መሆኑን ገለጸው ይህ 12ኛ ዓለማቀፍ መንፍሳዊ ንግደት “ሰላምን ፈልጋት ተከተላትም”  ከሚለው መሪ ቃል ጋር የተጣጣመ በመሆኑ መደሰታቸውን ጨምረው ገለጸዋል።

በመንፈሳዊ ንግደቱ ወቅት የተገኙ ወጤቶች

በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ከ19 ሀገራት የተውጣጡ ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑ በስርዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ከ13-23 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች ዓለማቀፍ ማኅበር አባላት በሮም ባደርጉት መንፈሳዊ ንግደት የተጎናጸፉት አዎንታዊ ውጤቶች በተመለከተ ታዳጊ ውጣቶችን በማጀብ ወደ ሮም የመጡት የተለያዩ ሀገራት ጳጳሳት በዛሬው እለት ማለትም በሐምሌ 28/2010 ዓ.ም ረፋዱ ላይ በቅድስት መንበር የሕትመት እና የዜና አገልግሎት መስጫ ጽሕፈት ቤት ተገኘትው በሰጡት መገለጫ ብጹዕን ጳጳሳቱ እንደ ገለጹት በቅድሚያ በታዳጊ ወጣቶች ዘንድ የአንድነት እና የኅበርት ስሜት እንዲፈጠር ያስቻለ መንፍሳዊ ንግደት መሆኑ ተቀዳሚ ውጤት ነው ብለዋል።

በመንፈሳዊ ንግደቱ ከተገኙት ውጤቶች መካከል በዋነኛነት የሚገለጸው እነዚህ ከ70ሺ በላይ የሆኑ ወጣቶች ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን የነበራቸው ቆይታ እንደ ነበረ የተናገሩት አቡነ ላዲስላቪ ኔሜት በተለይም ቅዱስነታቸው ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ ከወጣቶቹ ጋር በነበራቸው ቆይታ በሙሉ ልባቸው ከወጣቶቹ ጋር እንደ ነበረ መመልከቱ በራሱ ትልቅ እና አመርቂ የሆነ ውጤት መሆኑን ጨምረው ገለጸዋል።

Photogallery

በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ከ13-23 የእድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች ማኅበር አባላት
04 August 2018, 15:20