ፈልግ

የቅድስት መንበር እና የቻይና ባለ ስልጣናት ውይይት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ። የቅድስት መንበር እና የቻይና ባለ ስልጣናት ውይይት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ። 

የቅድስት መንበር እና የቻይና ባለ ስልጣናት ውይይት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ

የመላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና በተለይም የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቋም፣ ከኮሚኒስት ርዕዮተ ዓለም አራማጅ ከሆኑ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች፣ ተቀባይነት በሌላቸው ጽንሰ-ሐሳቦችና በሁለቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል የሚደረጉ ጥረቶች በውይይት አማካይነት መልካም ውጤትን እንዲያመጡ ማድረግ እንደሚቻል ተገለጸ።

የቅድስት መንበር እና የቻይና ባለ ስልጣናት ውይይት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ።

የመላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና በተለይም የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቋም፣ ከኮሚኒስት ርዕዮተ ዓለም አራማጅ ከሆኑ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች፣ ተቀባይነት በሌላቸው ጽንሰ-ሐሳቦችና በሁለቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል የሚደረጉ ጥረቶች በውይይት አማካይነት መልካም ውጤትን እንዲያመጡ ማድረግ እንደሚቻል ተገለጸ።

በመላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የቅርብ ጊዜ ታሪክ፣ በተለይም በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ወቅት በቻይና መንግስትና በቅድስት መንበር መካከል በሚገኙ ተቋማት መካከል ግንኙነቶች መዘርጋታቸው ይታወቃል። ወደ መጀመሪያ ገደማ ይህ ነው የሚባል ዉጤት ባይታይበትም ዝግ ውይይቶች ሲደረጉ ቆይቷል። ቢሆንም ቅድስት መንበር ተስፋ ባለመቁረጥ፣ የተጀመረው ውይይት እንዳይቋረጥ በማለት፣ አስፈላጊውን ትኩረት በመስጠትና ለቻይና መንግሥትም ያላትን ትልቅ አክብሮት በመግለጽ፣ በቻይና የምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ በቅድስት መንበር በኩል በምታከናውናቸው ሁለ ገብ አገልግሎቶች ላይ፣ ባለፉት ዓመታትና ዛሬ በዘመናችንም እየተፈጸሙ ያሉትን በደሎች በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ስታሳውቅ ቆይታለች።

ይህም በጽንሰ-ሐሳብ ደረጃ በሁለቱ ወገኖች መካከል ሊኖር የሚገባውን የውይይት መድረክ አስፈላጊነትን በማጉላት የቻይና መንግሥት ለካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ያላትን አመለካከት በበጎ እንዲሆን አድርጎታል። ቀስ በቀስም የካቶሊክ እምነት በቻይና መንግሥት መካከል ሊያስከትል ይችላል እየተባለ የሚታሰበውን አሉታዊ ተጽዕኖን እና በምዕናን ላይ የሚደርሰውን ስቃይ በመቀነስ፣ ምንም እንኳን በመላው የቻይና ግዛት ውስጥ ተግባራዊነቱ በጉልህ ባይታይም የመቀራረብንና የመተማመንን መንፈስ አሳድጓል ማለት ይቻላል።

የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ፣ በ1993 ዓ ም የውይይት አስፈላጊነትን አስመልክተው ለቻይና መንግሥት ባለስልጣናት ባደረጉት ንግግራቸው፣ መላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለሰው ልጅ ጥቅም ስትል ከቻይና መንግሥት ጋር የውይይት መድረኮችን ለማስፋት የምታደርገው ጥረት ከማንም የተሰወረ እንዳልሆነ ገልጸው እንደነበር ይታወቃል። ቀጥሎም በ1999 ዓ ም የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት 16ኛም፣ መላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በቻይና ያላት ተልዕኮ የመንግሥት ተቋማትን እና አስተዳደርን መቀየር ሳይሆን ለሕዝቡ የኢየሱስ ክርስቶስን የወንጌል ምስራች ማብሰር ነው ብለው እንደነበር ይታወሳል።

ይህን በማድረግ ቤተክርስቲያን የወንጌልን የምስራች የመናገር መብቷንና ነጻነቷን ትጠቀማለች። በዚህም ወደ ፖለቲካ አቋም ከማዘንበል ራሷን ነጻ ታደርጋለች። ማሕበራዊ መረጋጋትን ማምጣት የመንግሥት የፖለቲካ ግዴታ መሆኑ ቢታወቅም በተጨማሪም ቀዳሚ የሆነ ሰብዓዊ እና ሞራላዊ ግደታ መሆኑን ቤተ ክርስቲያንም ጠንቅቃ በማወቅ ግልጽ የሆኑ ምክንያቶችን፣ ባለሙያ ግለሰቦችን በማዘጋጀት፣ እንደየ አስፈላጊነቱ ገንቢ የሆኑ አስተያየቶችን በማቅረብ ድምጿን ታሰማለች። 

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት 16ኛ፣ የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት እንዳደረጉ ሁሉ፣ ቅድስት መንበር ከቻይና ባለስልጣናት ጋር ግልጽ ውይይቶችን ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነች አሳውቀው ነበር። ይህን ዓላማ በማጠናከርም ዘላቂና ጠንካራ የግንኙነት እና የመተጋገዝ መንገድ ተዘርግቶ ማየት እንደሚፈልጉ ገልጸው ነበር። በመካከላቸ ያለው ወዳጅነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣት፣ ደሳትንም ሆነ ሃዘንን  አብሮ በመጋራት፣ እርስ በርስ መተጋገዝ እንደሚያስፈልግ መናገራቸው ይታወሳል። በሌላ ወገን መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ ቢኖር፣ እምነትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ለሕዝቡ የሚያመጣዉን ጥቅም ወደ ጎን ማድረግን አስወግደን ይልቅስ ለሐዋርያዊ አገልግሎት እንቅፋት የሚሆኑትን በማስወገ መፍትሄዎችንም በጋራ መፈለግ እንደሚያስፈልግና ግጭቶችን ለማስወገድ ከሕዝባዊ ባለስልጣናት ጋር ዘላቂ ግንኙነት እንደሚያስፈልግ ማሳሰባቸው ይታወቃል። 

ይህን ፈለግ በመከተል የተያዘው ጥረትና የውይይት ሂደት እንዲቀጥል ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጉዳዩ ለሚመለከተው የቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት አሳስበዋል። ቅዱስነታቸው አክለውም ከቻይና መንግሥት ጋር የሚደረገው ውይይት ጥንቃቄን የተላበሰ፣ ደከመን ሰለቸን ሳንል፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሚመጣው ጥበብ እና እምነት መታገዝ ይኖርበታል ብለዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስም ታላቁን የቻይና ሕዝብን ለመጎብኘት እና ከሃገሪቱ መራሄ መንግሥት ጋር ለመገናኘት ታላቅ ምኞት እንዳደረባቸው ታውቋል።                      

03 July 2018, 09:19