ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ከስደተኞች ጋር በላምፐዱሳ በተገናኙበት ወቅት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ከስደተኞች ጋር በላምፐዱሳ በተገናኙበት ወቅት 

ቅድስት መንበር፣ የስደተኞች ሰብዓዊ መብት ይጠበቅ ስትል አሳሰበች።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ቤርንዲቶ ኣውዛ፣ በኒዮርክ በተደረገው ጉባኤ እንደገለጹት፣ ለሰው ልጅ የሚደረግ ከለላ መርህ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ አሳሰቡ።

ቅድስት መንበር፣ የስደተኞች ሰብዓዊ መብት ይጠበቅ ስትል አሳሰበች።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ቤርንዲቶ ኣውዛ፣ በኒዮርክ በተደረገው ጉባኤ እንደገለጹት፣ ለሰው ልጅ የሚደረግ ከለላ መርህ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ አሳሰቡ። በኢጣሊያ የጎዞ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ማርዮ ግረክ በቃለ ምልልሳቸው ወቅት በተናገሩት ተጨማሪ ገለጻቸው፣ አውሮጳም ለስደተኞች በምትሰጠው ከለላ የክርስትና መሠረቷል እንደምትገነዘብ ተስፋ አለኝ ብለዋል።

የዚህ ዜና አጠናቃሪ፡ ዮሐንስ መኮንን-ቫቲካን

ቅድስት መንበር፣ ለስደተኞች የሚደረገውን ከለላ እና የመብት ማስከበር ሂደት ሥርዓት ባለው መንገድ፣ ሕጋዊ እና ዘላቂ እንዲሆን ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ጥሩ ውጤት እያሳየ መምጣቱ እንዳስደሰታት ገልጻለች። በተጨማሪም መንግሥታት ስደትን አስመልክቶ በፖለቲካ አቋማቸው ትክክለኛ መንገድን እንዲከተሉ የሚያግዙ ዘዴዎችን መጠቀም እንዳለባቸው አሳስባ ከዚህ በተጨማሪም፣ ዓለም አቀፍ ግዴታዎችን በማክበር፣ የስደተኞችን ሰብዓዊ መብቶችን በማክበር የሚገባቸውን ከለላ እንዲሰጡ አደራ ብላለች። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ቤርንዲቶ ኣውዛ፣ ግሎባል ኮምፓክት በሚል መጠሪያ ስም የሚታወቅና በቅርቡ የስደተኞችን ጉዳይ አስመልክቶ በኒዮርክ ከተማ ለስድስተኛ ጊዜ በተደረገው ጉባኤ ላይ እንደተገለጸው፣ የስደተኞችን ሰብዓዊ መብት፣ ሕጋዊ ዝውውርን፣ ሊደረግላቸው ስለሚገባው ከለላ እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን የሚያጠቃልል ዓለም አቀፍ ሕግ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኩል ጸድቆ እንደሚወጣ ተናግረዋል።

ብጹዕ አቡነ ቤርናዲቶ አውዛ በኒዮርክ ላይ የተደረገውን የግሎባል ኮምፓክት ጉባኤን አወድሰው፣ በመንግሥታት መካከል ሕብረትን በመፍጠር፣ በስደተኞች ጉዳይ ላይ በጋራ በመምከር መፍትሄን ለማፈላለግ፣ ከዚህ በፊት የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት ውጤታማ ሥራን ለመሥራት የሚያስችል ሕግ መረቀቁ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል። ብጹዕ አቡነ ቤርናዲቶ፣ የሚሰደዱ ቤተ ሰቦችን አስመልክተው እንደተናገሩት፣ የሚጸድቀው አዲሱ ሕግ፣ በቤተ ሰብ መካከል መከፋፈል እንዲፈጠር የመንግሥታትና የሕጻናትም ፍላጎት እንዳልሆነ ያገናዘበ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ቤርናዲቶ ኣውዛ የቅድስት መንበርን አቋም በመመርኮዝ ባቀረቡት አስተያየት እንደገለጹት፣ በመንግሥታቱን መርህ ውስጥ በቂ ድምጽን ማግኘት የማይችሉ የአንዳንድ ድርጅቶች ሃሳብ አሁን በሚወጣው አዲሱ ሕጉ ቢካተቱ የቅድስት መንበርን አቋም ስምምነትን በማዛነፍ ለሌላ ውይይት ይዳርጋል ብለዋል።

ብጹዕ አቡነ ቤርናዲቶ፣ ስደተኞችን የሚቀበሉ አገራት ለስደተኞች የሚያቀርቡትን አገልግሎቶች ለምሳሌ የሕክምና አገልግሎት፣ የትምህርት ዕድል እና ሕጋዊ ከለላን እንዲያደርጉ የሚያስገድደውን ሕግ ማስቀረቱ እንዳሳሰባቸው ገልጸው፣ ስደተኞችን ተቀብለው የሚያስተናግዱ አገራት፣ በስደተኞች መካከል ልዩነት ሳያደርጉ እነዚህን አገልግሎቶችን ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ገልጸዋል። ስደተኞችን ተቀብለው የሚያስተናግዱት አገራት፣ የሚመሩበትን ሕግ በማክበር ሕጋዊ እና ሕጋዊ ያልሆኑ ስደተኞችን በመለየት የዓለም አቀፍ ሕጎችን በማክበር አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

ለስደተኞች የሕግ ከለላ እንዲኖር የሚለው ሐረግ ከሚረቀቀው ሕግ መሰረዙ የቅድስት መንበር ልዑካንን ያሳሳበ ቢሆንም ብጹዕ አቡነ ቤርናዲቶ እንደገለጹት ለስደተኞች ሊደረግ የሚገባው የሕግ ከለላ፣ በዓለም አቀፍ የስደተኞች መብት ውስጥ የተካተተ በመሆኑ ተግባራዊ ሆነው መታየት አለበት ብለዋል።

የቅድስት መንበርን አቋም ያረጋገጠው የቫቲካን ልዑካን እንዳስታወቀው ሰዎች በአገሮቻቸው በሰላም ወጥተው ገብተው እና በልጽገው መኖር መብታቸው ቢሆንም ይህ ካልተመቻቸላቸው ግን ወደ ፈለጉት አገር ሄደው የመኖር መብታቸውም የተጠበቀ መሆን አለብት ብለዋል።

በኢጣሊያ የጎዞ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ማርዮ ግረክ፣ ያለፈው እሁድ፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓል ተከብሮ በዋለበት ዕለት ለምዕመናን ያቀረቡትን ቃለ ምዕዳን በማስታወስ ባሰሙት ንግግር፣ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተቀበለው መከራ ዛሬ በዘመናችንም እየተከሰተ እንዳለ አስታውሰው፣ ሰዎች በፍርሃት፣ ተስፋ በመቁረጥ፣ በኢፍትሃዊነት፣ በአመጽ እና በድህነት በሚሰቃዩበት ጊዜ ሁሉ አብሮአቸው በመሆን እንዲሁም ከባሕር ላይ አደጋ ራሳቸውን ለማዳን ከሚጥሩ ስደተኞችም ጋር እንደሆነ አስረድተዋል።

በኢጣሊያ የጎዞ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ማርዮ ግረክ ለቫቲካን የዜና ማሰራጫ እንደገለጹት፣ አውሮጳ  አንድነትን፣ ፍትህን፣ እኩልነትን ኣና ሰብዓዊ ክብርን እንድታከብር የሚያደርጋትን ክርስቲያናዊ እሴቶቿን ወደ ጎን ማለቷን ጠቅሰው፣ ይህ ልበ ደንዳናነት ዛሬ የምናየውን አሳዛኝ ክስተት እንድንኖር አስገድዶናል ካሉ በኋላ አውሮጳ ወደ ክርስትና መሠረቷ መመለስ ያሻታል ብለዋል። በስደተኞች አንደበት በኩል ለሚሰማው የእግዚ አብሄር ጩኸት አውሮጳ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት የለባትም።  ብጹዕ አቡነ ማርዮ ግረክ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን መልዕክት በማስታወስ፣ አውሮጳ ብታረጅም የራሷን ሰብዓዊና ክርስቲያናዊ መሠረቷን ፈልጋ ማግኘት አለባት ብለዋል።

10 July 2018, 09:18