ፈልግ

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ሐዋርያዊ መልዕክት 50ኛ ዓመት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ሐዋርያዊ መልዕክት 50ኛ ዓመት 

የሰው ልጅ ሕይወት የሚለው የር. ሊ. ጳ. ጳውሎስ 6ኛ ሐዋርያዊ መልዕክት 50ኛ ዓመት

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ “የሰው ልጅ ሕይወት” የሚለውን ሐዋርያዊ መልዕክት ያስተላለፉት፣ የጋብቻን ሕይወት ለማጎልበት ድጋፍ እንዲሆን በማሰብ ነበር።

ዮሐንስ መኰንን - ከቫቲካን

“የሰው ልጅ ሕይወት” የሚለው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ሐዋርያዊ መልዕክት ለንባብ ከበቃ እነሆ በዛሬው ዕለት 50 ዓመቱን አስቆጥሯል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ይህ ሐዋርያዊ መልዕክት ይፋ ከመሆኑ ከአንድ ሳምንት አስቀድመው ባቀረቡት የረቡዕ ዕለት ጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተንትኖ፣ ክርስቲያን ባለ ትዳሮች፣ “የሰው ልጅ ሕይወት” የሚለውን ሐዋርያዊ መልዕክት፣ ለጋብቻ ሕይወታቸው ጥሪ መጎልበት ድጋፍ እንዲሆናቸው በማለት እንዲያነቡት ጥሪ አቅርበው ነበር።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ በበጋው የዕረፍት ማሳለፊያ ሥፍራ ከሆነው ከካስቴል ጋንዶልፎ ጳጳሳዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመሆን የጠቅላላ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምሮአቸውን አቅርበው ነበር። በዕለቱ ያስተላለፉትን መልዕክት ሲጀምሩ “የዛሬው መልዕክቴ እጅግ አስፈላጊ እና አንገብጋቢ በሆነው “የሰው ልጅ ሕይወት” በሚል ሐዋርያዊ መልዕክቴ ላይ የተመሠረተ ነው በማለት መጀመራቸው ይታወሳል። ይህ አጋጣሚ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ሕዝቡን በቀጥታ ማግኘት እንዲችሉ መልካም አጋጣሚን ፈጥሮላቸው ነበር። በዕለቱ “የሰው ልጅ ሕይወት” በማለት ያቀረቡት መልዕክት፣ በሐዋርያዊ አገልግሎት ዓመታት አንስተው ከተወያዩባቸው ሰነዶች  መካከል የበለጠ ትኩረትን የሳበ እንደነበር ይታወሳል።

ይህ ሰነድ፣ የሰዎችን የተሳሳተ ሞራላዊ ሕጎችን የሚቃረን፣ ይህም ማለት የሰው ልጅ እንዳይዋለድ፣ ሕይወትም እንዳይበራከት የሚያደርገውን ሕግ የሚቃወም ብቻ ሳይሆን፣ ትክክለኛውን ስነ ምግባርን በመከተል፣ ባለ ትዳሮች በፍቅር ያከናወኑትን የጋብቻ ጥሪያቸውን መሠረት በማድረግ እንዲወልዱ የሚያዝ ነው። ሰነዱ ቤተ ክርስቲያን ከውጭም ሆነ ከውስጥ ሊደርስባት የሚችለውን ነቀፋ ይሁን በጎ አስተያየት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ በጥንቃቄ ተመልክተውት ነበር። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በዕለቱ ከጳጳሳዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሆነው  ያስተላለፉትን መልዕክት ስናዳምጥ፣ “የሰው ልጅ ሕይወት” የሚለው ሐዋርያዊ መልዕክት ይፋ መሆን፣ የጋብቻን ሥነ-ምግባር የሚደግፍ በመሆኑ አስፈላጊነቱ ግልጽ ነው የሚል ነበር። ስለ ሰው ልጅ ሕይወት በስፋት የሚናገር ሐዋርያዊ መልዕክት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛን ትኩረት ብቻ ሳይሆን የሰው ልጆችን ልብ በሙሉ የሳበው ለምንድር ነው። የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ሐዋርያዊ መልዕክት በእርግጥም የመወያያ ርዕስ ሆኖ መቅረቡ ብቻ ሳይሆን ትንተና እና ግልጽነት እንዲኖረው ያስፈልጋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛን መልዕክት ስውር፣ ሌሎችን የሚያስከፋ የባለ ስልጣን አስተሳሰብ ሳይሆን፣ ለቤተ ሰብ ካላቸው አባታዊ ፍቅር የመነጨ፣ በተለይም የየዕለት ሕይወታቸውን ከእምነት በሚያገኙት የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ በመመራት ለሚኖሩት ቤተ ሰቦች እንዲሆን በማሰብ ያስተላለፉት መልዕክት ነበር።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ በዕለቱ በስፍራው ለተሰበሰቡት ምዕመናን ባሰሙት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምሮ፣ ስለ ሰው ልጅ ሕይወት በተናገሩ ጊዜ፣ ምዕመናን በርዕሠ ጉዳዩ ጊዜን ሰጥተው እንዲያስቡበት እና ከአራት ዓመታት ወዲህ ሲነገር የቆየው ርዕሠ ጉዳይ የበለጠ ሕይወት እንዲያገኝ ለማሳሰብ ነበር። በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ “ሰው ልጅ ሕይወት” በሚለው መልዕክት ቀዳሚ ትኩረት፣ ትልቅ ሃላፊነት በመውሰድ፣ ማንበብ፣ ማጥናት፣ መወያያት እን መጸለይ ነበር።

ሌላ ተጨማሪ ትኩረት እና ሃሳብ የነበረው፣ ሐዋርያዊ መልዕክታቸው በሚታይበት ጊዜ ወይም ጥናት በሚደረግበት ጊዜ ሁሉ ትሕትናን የተላበሰ እንዲሆን ማድረግ፣ በጋብቻ ሕይወት ለመኖር ለተጠሩት በሙሉ ሊደረግላቸው የሚያስፈልገውን ሐዋርያዊ እንክብካቤን እን አገልግሎትን በፍሬያማነት ማዳረስ ነበር። ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ሐዋርያዊ መልዕክት የተሰጠው ሦስተኛ ትኩረት ተስፋን ማድረግ ነበር። ይህን ስንል ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ በመልዕክታቸው፣ በክርስቲያናዊ ፍቅር በመነሳሳት የጋብቻ ሕይወታቸውን አብረው ለመኖር የተነሱት ባለትዳሮች፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እርሱ የመሠረታትን ቤተ ክርስቲያን እንደወደዳት ሁሉ፣ በጋብቻ አንድ አካል የሆኑት ባለ ትዳሮችም ለእውነተኛ  ፍቅር መጥራታቸውን እንዲያውቁ የሚያሳስብ ነው። በተጨማሪም ይህ በጎ ዓላማ በዘመናችን ባለ ትዳሮች ዘልቆ በመግባት፣ እንደ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ሐዋርያዊ መልዕክት መንፈሳዊ ይዘትን በመላበስ፣ ለእያንዳንዱ ቤተ ሰብ ቅድስና እና ምስክርነት እንዲሆን የታሰበ ነው። 

25 July 2018, 09:09