ፈልግ

በመካከለኛው የፍሪካ ሪፖብሊክ ዋና ከተማ በባንጉዊ ካቴድራል መስዋዕተ ቅዳሴ በተደረገበት ወቅት በመካከለኛው የፍሪካ ሪፖብሊክ ዋና ከተማ በባንጉዊ ካቴድራል መስዋዕተ ቅዳሴ በተደረገበት ወቅት  

ቅዱስ ወንጌል ከግጭት እና ከድህነት የበለጠ ብርቱ እንደ ሆነ ተገለጸ

CUAMM በመካካለኛው አፍሪካ ሪፖብሊክ መጠነ ሰፊ የሆነ የጤና ክብካቤ ድጋፍ በማድረግ ላይ የሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነ የግብረ ሰናይ ድርጅት

ቅዱስ ወንጌል ከግጭት እና ከድህነት የበለጠ ብርቱ እንደ ሆነ ተገለጸ

CUAMM በሚል ምጻረ ቃል የሚታወቀው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በአፍሪካ አህጉር የሚደረጉትን የጤና ክብካቤ እንቅስቃሴዎችን የሚደግፍ የጣሊያን መንግሥታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት እንደ ሆነ ይታወቃል። ይህ መንግሥታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት በአሁኑ ወቅት በእርስ በእርስ ጦርነት እየተጎሳቆለች በምትገኘው በመካካለኛው አፍሪካ ሪፖብሊክ መጠነ ሰፊ የሆነ የጤና ክብካቤ ድጋፍ በማድረግ ላይ የሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነ የግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን የእዚህ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አባ ዳንቴ ካራሮ በቅርቡ በመካከለኛው አፍሪቃ ሪፖብሊክ ቆያታ አድርገው ወደ ጣሊያን ከተመለሱ በኋላ ከሬዲዮ ቫቲካን ጋር ቆያት ባድረጉበት ወቅት እንደ ገለጹት ቅዱስ ወንጌል ከግጭት እና ከድህነት የበለጠ ብርቱ እንደ ሆነ ለመረዳት ችያለሁ ብለዋል።

የCUAMM  ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አባ ዳንቴ ካራሮ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደ ገለጹት በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ በአሁኑ ወቅት የሚታየው የጤና ሁኔታ በእርስ በእርስ ጦርነቱ የተነሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሁኔታው እየተባባሰ መሄዱን ገልጸው ለምሳሌም የወዲፊቱ የሀገሪቷ የጀርባ አጥንት ናቸው የሚባሉ ሕጻናት የሚታከሙበት 4 ሆስፒታል ብቻ እንደ ሚገኑ፣ እነዚህም 4 የሕጻናት ሆስፒታሎች በእርስ በእርስ ጦርነቱ የተነሳ በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት እንደ ማይሰጡ ገለጸው ይህ ሁኔታው አሳሳቢ የሆነ ደረጃ ላይ እንደ ሚገኝ ያሳያል ብለዋል።

በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ 16 የሚሆኑ የጦር አበጋዞች በተለያዩ ግንባሮች ጦርነት እያካሄዱ እንደ ሚገኙ የጠቀሱት CUAMM  ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አባ ዳንቴ ካራሮ በሀገሪቷ ያለው የድኽነት ሁኔታ በጣም አሰቃቂ በመሆኑ የተነሳ ይህም በሀገሪቷ ለሚታየው አሰቃቂ ግጭት ዋነኛው መንስሄ ሊሆን ችሉዋል ብለዋል።

በመካከለኛው የፍሪካ ሪፖብሊክ የሚኖሩ ሕዝቦች መሰረታዊ የሆነ ፍላጎታቸውን የሚያሟላላቸው የመንግሥት አካል እንደ ሚያስፈልጋቸው ጨምረው የገለጹት CUAMM ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አባ ዳንቴ ካራሮ ሀገሪቷ በከፍተኛ ሁኔታ በአሰቃቂ የድኽነት ማቅ ውስጥ በምትገኝበት በአሁኑ ወቅት በተቃራኒው ደግሞ የሀገሪቷ አንጡራ የሆኑ ሀብቶች ለምስሌም ወርቅ፣ ዩራኒዬም እና ዳይመንድ ሳይቀር በሕገ-ወጥ መነገድ እየተበዘበዘ እንደ ሆነ ጨምረው ገለጸዋል።

በሀገሪቷ የሚገኘው መንግሥት በአሁኑ ወቅት አንጻራዊ በሆነ መልኩ በዋና ከተማዋ በባንጉዊ ከዓለማቀፉ ማኅበርሰብ ከተውጣጡ የሰላም አስከባሪዎች ጋር በጋራ በመሆን አንጻራዊ በሆነ መልኩ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ መቻሉን ጠቅሰው ከዋና ከተማዋ ውጪ ግን 16 የተለያዩ አንጃዎች ያሻቸውን እየፈጸሙ ሀገሪቷን ከድጡ ወደ ማጡ እንድትሄድ በማድረግ የሀገሪቷን ሕዝቦች ለከፍተኛ ድኽነት እና ሰቆቃ መዳረጋቸውን ጨምረው ገለጸዋል።

በመካከለኛው አፍሪካ ሪፖብሊክ በአሁኑ ወቅት የሚታየው የእርስ በእርስ ግጭት እንዲፋፋም ያድርገው በሀሪቷ የሚገኘውን የተፈጥሮ ሐብት የሚገኙባቸውን ሥፍራዎች ለመቆጣጠር በሚደረግ ሩጫ እንደ ሆነ የገለጹት የCUAMM ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አባ ዳንቴ ካራሮ ሕዝቡን ለሚያሳቅቅ መከራ መዳረጋቸውን ጨምረው ገለጸዋል።

በአሁኑ ወቅት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን 196 አልጋዎች ያሉት የሕጻናት ሆስፒታል ገንብታ ለሀገሪቱ ሕዝብ አገልግሎት ማብቃቷን የገለጹት የCUAMM ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አባ ዳንቴ ካራሮ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት የተለያየ ዓይነት የሕነጻ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችሉ ተቋማትን ቤተክርስትያኗ በመገንባት ላይ እንደ ሚተገኝ ጨምረው ገለጸው በተለይም ደግሞ የሕክምና አገልግሎቱን የተቀላጠፈ ለማድረግ በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች የሚሰለጥኑበት ማዕከል በመገንባት ላይ እንደ ሆነ ጨምረው ገለጸዋል።

በቅርቡ በሀሪቷ በምትገኘው የካቶሊክ ቤተክርስትያን ካህናት ላይ ጥቃት መፈጸሙን የገለጹት የCUAMM ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አባ ዳንቴ ካራሮ ካህናቱ በሀሪቷ በአሁኑ ወቅት የሚታየውን ብጥብጥ በማውገዛቸው የተነሳ በምዕመኑ ላይ ሳይቀር ከፍተኝ የሆነ ስቃይ እየደረሰ መሆኑን ጨምረው ገለጸዋል።

25 July 2018, 08:57