ፈልግ

የባሕር ንጽሕና አጠባበቅ የባሕር ንጽሕና አጠባበቅ 

የባሕር ውስጥ ፍጥረትን ከጥፋት ለመከላከል እርምጃ ተወሰደ።

የባሕር ቀን ታስቦ በዋለበት ቅዳሜ ሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ. ም. የባሕር ውስጥ ፍጥረትን ከጥፋት መከላከል እንደሚያስፈልግ የዘርፉ ዳይረክተር የሆኑት ክቡር አባ ብሩኖ ቺቸሪ አስገንዝበዋል። ክቡር አባ ብሩኖ ለባሕር ውስጥ ፍጥረታት የሚደረግ ጥበቃ እና እንክብካቤ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይፋ ካደረጉት፣ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” የሚለውን ሐዋርያዊ መልዕክት የሚያከብር ነው ብለዋል።

የባሕር ውስጥ ፍጥረትን ከጥፋት ለመከላከል እርምጃ ተወሰደ።

የባሕር ቀን ታስቦ በዋለበት ቅዳሜ ሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ. ም. የባሕር ውስጥ ፍጥረትን ከጥፋት መከላከል እንደሚያስፈልግ የዘርፉ ዳይረክተር የሆኑት ክቡር አባ ብሩኖ ቺቸሪ አስገንዝበዋል። ክቡር አባ ብሩኖ ለባሕር ውስጥ ፍጥረታት የሚደረግ ጥበቃ እና እንክብካቤ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይፋ ካደረጉት፣ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” ከተሰኘው ሐዋርያዊ መልዕክት ጋር ይገናኛል ብለዋል።

የዚህ ዜና አዘጋጅ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ክቡር አባ ብሩኖ በገለጻቸው እንዳስታወቁት እሁድ ተከብሮ የዋለው የባሕር ቀን፣ ለባሕር ሃይል አባላት፣ ለባሕር ላይ ዓሣ አጥማጆች እና ለቤተሰቦቻቸው፣ ለባሕር ላይ ተጓዦች ሐዋሪያዊ አገልግሎትን ለሚያበረክቱ ቆሞሶስች ጸሎት እንዲደረግላቸው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ማሳሰባቸውን ገልጸዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በባሕር ላይ በተለያዩ ሥራዎች በተለይም ባሕርን በማጽዳት ሥራ         ላይ ተሰማርተው የሚገኙትን ማስታወሳቸው ይታወቃል።

ብጹዕ ካርዲናል ታርክሰን በበኩላቸው በባሕር በተለያዩ ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙትን ሰራተኞችን በማስታወስ ለነዚህ ሰራተኞች ለሚቀርብ የዕለት ምግብ እግዚአብሔርን አመስግነው፣ ባሕርን በመንከባከብና አስፈላጊዉን ጥበቃ በማድረግ ሰራተኞች ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዋል። በቅድስት መንበር የሰዎችን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚንከባከብ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል አፒያ ታርክሰን፣ ዕለቱ ተከብሮ በዋለበት ዕለት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባሕርን እና በባሕር ላይ የሚገኙትን ፍጥረታት ደህንነት እና የባሕርን ብክለት የሚቆጣጠር ዓለም አቀፍ ድርጅትን ቅድስት መንበር በእጅጉ እንደምታግዝ እና እንደምትደግፍ አስታውቀዋል።

ባሕርን ከብክለት ጠብቆ፣ ንጽሕናውን ለመንከባከብ መልካም መንገድ የሚጠቁም ዓለም አቀፍ ጉባኤ በሐምሌ ወር በቫቲካን ተክሂዶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ይህም የተከናወነው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” በሚል ርዕስ ይፋ ያደረጉት መልዕክት ሦስተኛ ዓመትን ባስቆጠረበት ወቅት እንደሆነ ታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመልዕክታቸው ስለ ባሕርና በባሕር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች አስታውሰው የተናገሩበት ዋና ምክንያትም ባሁኑ ጊዜ የባሕር ሙላት እየጨመረ መምጣቱን በመረዳት፣ ይህ እንዲህ ከቀጠለ በባሕር ዙሪያ የሚኖሩ፣በቁጥር አንድ አራተኛ የሚሆን የዓለም ሕዝብ በከባድ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ በመገንዘባቸው ምክንያት እንደሆነ ታውቋል። ቅዱስነታቸ እንደገለጹት በባሕር ውስጥ የሚደፉ መርዛማ የሆኑ የፋብሪካ ውጤቶች ባሕርን በመበከል ለምግብነት የሚውሉ ፍጥረታት ላይ ችግር እንደሚያስከት አስረድተዋል።

የባሕር ላይ ሐዋርያዊ አገልግሎት በተመለከተ፣ ዕለቱ ተከብሮ በዋለበት ዕለት የተለያዩ ግንዛቤ ሰጭ የሆኑ መልዕክቶችንና መረጃዎችን በማሰራጨት እንደተከናወነ የሚታወቅ ሲሆን በቀጣይ ዓመታትም በባሕር ላይ ለሚኖሩ ሰዎች፣ ሐዋሪያዊ አገልግሎት ለማዳረስ ተሰማርተው የሚገኙ ካህናትን እና በበጎ ፈቃደኝነት ሥራ የተሰማሩትንም በሙሉ ለመርዳት የሚደረግ ሐዋርያዊ ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል። ክቡር አባ ብሩኖ ቺቸሪ ለቫቲካን የዜና ማሰራጫ አገልግሎት እንደገለጹት፣ ባሕር ለፍጥረታት በሙሉ የጋራችን በመሆኑ፣ በተለይ በቁጥር በርካታ የሆኑ ሰዎች በዓሣ ማጥመድ ሥራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ገልጸው፣ በምንም መልኩ የባሕር ንጽሕና ተጠብቆ እንዲቆይ ያስፈልጋል ብለዋል።  ክቡር አባ ብሩኖ ቺቸሪ በማከልም የአካባቢ ጥበቃን በተለይም የባሕር እንክብካቤን በባሕር ላይ ከሚሰሩ የሥራ ዓይነቶች ጋር ማቀናጀት ያስፈልጋል ብለዋል።

ባሕር በመርከቦች፣ ከመርከቦች በሚወጣው ጭስ፣ ከመርከብ ውስጥ በሚፈሰው ነዳጅ እና ቅባት ነክ ነገሮች ምክንያት ሊቆሽሽ ይችላል። ዘመናዊ መርከቦች አነስተኛ ጭስ እንዲወጡ ተደርገው መሰራታቸው በባሕር ላይ ሊደርስ የሚችለውን ብክለት እንደቀነሰ አባ ብሩኖ ገልጸው፣ በባሕር ላይ ሆነው ጸሐይ ስትወጣ እና ስትጠልቅ መመልከት፣ የተለያዩ የዓሣ ዓይነቶች በባሕር ውስጥ ሲሄዱ ማየት የእግዚአብሔርን ታላቅነት ሰዎች እንዲያውቁ ያግዛል ብለው የባሕርን ንጽሕና ጥብቆ ውበቱን በመመልከት ሰዎች የእግዚአብሔርን ጥበብ በመመልከት ወደ እርሱ እንዲቀርቡ ያግዛቸዋል ብለዋል።

የባሕር ውሃ እንዲበከል ዋናው ምክንያት ወደ ባሕር በሚወረወሩ የፕላስቲክ ውጤቶች ነው ያሉት አባ ብሩኖ በተቻለን መጠን በፕላስቲክ ዕቃ ከመጠቀም ይልቅ በሸክላ ወይም በብርጭቆ ነክ ዕቃ መገልገል ይመረጣል ብለዋል።                     

09 July 2018, 15:49