ፈልግ

ር.ቃ.ጳ. ፍራንቸስኮ 14 በቫቲካን በቅዱ ጴጥሮስ ባዚሊካ በሰየሙበት ወቅት ር.ቃ.ጳ. ፍራንቸስኮ 14 በቫቲካን በቅዱ ጴጥሮስ ባዚሊካ በሰየሙበት ወቅት  

ር.ቃ.ጳ. ፍራንቸስኮ 14 አዳዲስ ካርዲናሎችን መሾማቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሰኔ 21/2010 ዓ.ም ከ11 የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ 14 ካርዲናሎችን በቫቲካን በሚገኘው በቅድሱ ጴጥሮስ ባዚሊካ በተካሄድው ስነ-ስረዓት ላይ የካርዲናልነት ማዕረግ መስጠታቸው ተገለጸ።

ር.ቃ.ጳ. ፍራንቸስኮ 14 አዳዲስ ካርዲናሎችን መሾማቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሰኔ 21/2010 ዓ.ም ከ11 የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ 14 ካርዲናሎችን በቫቲካን በሚገኘው በቅድሱ ጴጥሮስ ባዚሊካ በተካሄድው ስነ-ስረዓት ላይ የካርዲናልነት ማዕረግ መስጠታቸው ተገለጸ።

መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ

እነዚህ አዳዲስ ካርዲናሎች ከ11 የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ እንደ ሆነ ለመገንዘብ የተቻለ ሲሆን በእዚህ መሰረት ከቦሊቪያ፣ ከኢራቅ፣ ከጣሊያን፣ ከጃፓን፣ ከፓኪስታን፣ ከፖላንድ፣ ከፖርቹጋል፣ ከፔሩ፣ ከማዳጋስካር፣ ከሜክሲኮ እና ከእስፔን መሆናቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የካሪዲናሎች የመማክርት ጉባሄ ማለት ምን ማለት ነው?

የካርዲናሎች የመማክርት ጉባሄ ብጹዕን ካርዲናሎች ብቻቸውን ወይም ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን አስፈላጊ እና ዋና ዋና በሚባሉ በቤተ ክርስቲያንቷ ጉዳዮች ላይ ተሰብስበው የሚመካከሩበት የመማክርት ጉባሄ ሲሆን በተለይም ደግሞ የብጽዕና እና የቅድስና ማዕረግ በሚሰጣቸው ሰዎች ዙሪያ ተገናኝተው የሚመካከሩበት እንዲሁም ካርዲናሎችን ለመሰየም ተገናኝተው የሚወያዩበት እና ውሳኔ የሚያስተላልፉበት የመማክርት ጉባሄ ነው።

በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዋና ዋና እና አስፈላጊ በሚባሉ የቤተ ክርስቲያኗ ጉዳዮች ላይ ለመምከር የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ አማካሪዎች እና የሥራ ተባባሪ የሆኑት ካርዲናሎችን ሰብስበው የሚያነጋግሩበት አሰራር እንደ ነበረ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም ረገድ ዓለማቀፋዊ የሆነችው ቤተ ክርስቲያን በሚገባ ሥርዓቷን እና ወጓን ጠብቃ እንድትጓዝ ለማድረግ ምክክር በማድረግ አስፈላጊውን የአመራር ውሳኔ የሚያደርጉበት የምክክር ጉባሄ አዘውትረው ያከናውኑ እንደ ነበረ ይታወሳል።

ብጽዕ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ማነኛውንም ዓይነት ዓለማቀፍ ሐዋሪያዊ ጉብኚት አድግርገው ወደ ቫቲካን በሚመለሱበት ወቅት ሁሉ የመማክርት ጉባሄ አባላት የሆኑትን ካርዲናሎችን ሰብስበው እንደ ሚያነጋግሩ እና ስለ ገጠመኞቻቸውም እንደ ሚነጋገሩ የሚታወቅ ሲሆን በሐዋሪያዊ ጉብኝታቸው ወቅት የገጠማቸውን ገጠመኞች እና የታዘቡዋቸውን አሉታዊ እና አዎንታዊ የሆኑ ገጠመኞችን ከካርዲናሎቹ ጋር በመሰባሰብ ይወያዩባቸው እንደ ነበረ ከታሪክ መዕደር ለመረዳት ይቻላል።

በሰኔ 21/2010 ዓ.ም የካርዲናሎች የመማክርት ጉባሄ አባላት በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮስ ከዐስራ አንድ ሀገራት የተውጣጡ 14 አዳዲስ ካርዲናሎች የካርዲናልነትን ማዕረግ ተቀብለው ወደ ዓለማቀፋዊቷ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የካርዲናሎችን መዝገብ ውስጥ መካተታቸው የተገለጸ ሲሆን እነዚህ የካርዲናልነትን ማዕረግ የሚቀበሉ አዳዲስ ጳጳሳት ጥቁር ልብሰ ተክህኖ ለብሰው ቅይ መቀነት አገልድመው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ሌሎች የካርዲናሎች የመማክርት ጉባሄ አባላት እና ምዕመናን በተገኙበት አዳዲስ እጩ ካርዲናሎች የሐዋሪያት ጸሎተ ሐይማኖት ከደገሙ በኃላ እጩ ካርዲናሎች አንድ በአንድ ወደ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመቅረብ ተንበርክከው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአዳዲስ ካርዲናሎች ራስ ላይ ቀይ ቆብ ያጠልቃሉ፣ ከእዚያም ለእያንዳንዱ ካርዲናል ጣት ላይ ቀለበት ያጠላቃሉ።

ከእዚያም በመቀጠል በሮም ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ቁምስናዎች መካከል ተመርጠው ለእያንዳዱ አዲስ የካርዲናልነት ማዕረግ ለተቀበሉ ካርዲናሎች በስማቸው እንዲሰየሙ ይደረጋል።

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሕገ ቀኖና ውስጥ የካርዲናሎችን የመማክርት ጉባሄ በተመለከተ ሁለት ዓይነት የካርዲናል የመማክርት ጉባሄ እንዳለ የተጠቀሰ ሲሆን አንደኛው እና የመጀመሪያው መደበኛ ባልሆነ መልኩ አንድ አንድ አጣዳፊ ወይም በጣም አስፈላጊ የሆኑ ክስተቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚከሰቱበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመላው ዓለም የሚገኙትን ካርዲናሎች መደበኛ ባልሆነ እና ልዩ በሆነ መልኩ እንዲሰባስቡ የሚያደርጉበት እና ለየት ያሉ ሁኔታዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚከሰቱበት ወቅት ለክስተቶቹ ተገቢውን ምላሽ የሚሰጡበት ሂደት የመጀመሪያው ነው። በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ የሚገኘው የካርዲናሎች የመማክርት ጉባሄ በመደበኛ መልኩ የሚደርገው ዓይነት ሲሆን ይህም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አንዳንድ አስፈላጊ የሆኑ ሁኔታዎች በሚገጥሙዋቸው ወቅት፣ መደበኛ ነገር ግን አስፈላጊ የሆኑ ክስተቶች በሚፈጠሩበት ወቅት መላሽ ለመስጠት የካርዲናሎችን የመማክርት ጉባሄ መደበኛ በሆነ መልኩ ጠርተው የሚያማክሩበት ሂደት ደግሞ ሁለተኛው የመማክርት ጉባሄ አጠራር ሂደት ነው።

28 June 2018, 14:04