ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከአስፈላጊ የአለም ኢኮኖሚ አካላት ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከአስፈላጊ የአለም ኢኮኖሚ አካላት ዋና ስራ አስፈፃሚዎች  (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ለንግድ ተቋማት መሪዎች የበጎ አድራጎት ተግባር ብቻ በቂ አይደለም ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ የንግድ ተቋማት መሪነት ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች በማንፀባረቅ የዘላቂ ገበያዎች ተነሳሽነት አባላት ከሆኑ 25 ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ጋር ተገናኝተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዳሜ ሰኔ 8/2016 ዓ.ም ማለዳ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዘላቂ ገበያ ኢኒሼቲቭ አባላት ከሆኑ 25 ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ጋር በቫቲካን ተገናኝተዋል።

በተጨማሪም የስዊስ ገበያ መረጃ ጠቋሚ ተቋም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጄኒፈር ጆርዳን-ሳይፊ ተገኝተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለእንግዶቻቸው “በሺዎች እና በሺዎች በሚቆጠሩ ሰራተኞች ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር” እና “በመንግሥታት ሀብት ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር” ሥራቸው ወሳኝ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል ።

በዚህ ምክንያት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከእነሱ ጋር ስለ ሶስት ጉዳዮች ማለትም ስለ አካባቢ፣ ድሆች እና ወጣቶች በአጭሩ ለማሰላሰል ፈልጎ ነበር።

ጎብኚዎቹ በበኩላቸው በቅርቡ ለG7 የአለም አቀፍ እ.አ.አ 2030 ዓ.ም ማህበራዊ እና አካባቢን ግቦች  በተመለከተ ያቀረቡትን መደበኛ ምክሮች ዝርዝር አቅርበውላቸዋል።

አካባቢው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንግዶቻቸው የምንኖርበትን አካባቢ ወይም ምድራችንን "ማዕከል" ያደርጉ ንግግሮች ላይ ትኩረታቸውን እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የአየር ንብረት ቀውስን ከግምት ውስጥ በማስገባት “ከእንግዲህ በጣም በዝግታ የሚከናወኑትን የክልሎችን የአገሮች ህጎች ማክበር ብቻ በቂ አይደለም” ሲሉ አፅንዖት ሰጥቷል።

እንደ እውነቱ ከሆነ የወደፊቱን በመተንበይ እና በእዚህ ትንበያ ላይ መሰረት ያደረግ ደፋር እና የወደፊት ምርጫዎች ላይ ውሳኔ ማቅረብ ያስፈላጋል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “በአሁኑ ጊዜ የሥራ ፈጣሪው ፈጠራ በመጀመሪያ የጋራ ቤታችንን በመንከባከብ ረገድ ላይ ያተኮረ ፈጠራ መሆን አለበት” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለስብሰባው ተካፋዮች መልእክት ስያስተላልፉ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለስብሰባው ተካፋዮች መልእክት ስያስተላልፉ

ድሆች

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “በጣም ድሆችን እና የተጣሉትን መርሳት” መልካም እንዳልሆነ ማሰብ አስፈላጊ ነው ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “በአንድ የተወሰነ ‘ሜሪቶክራሲ’” (በችሎታ ላይ የተመሰረተ ሥርአት) ላይ መንጠልጠል መልካም እንዳልሆነ አስጠንቅቀዋል፣ እሱም፣  “የማይገባቸው ተብለው የተፈረጁ ድሆችን ማግለል ህጋዊ ለማድረግ መሥረት እንደ ሆነ” ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

እንዲሁም "ትንሽ በጎ አድራጎት" በቂ እንደሆነ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል የሚለውን ሀሳብ ማዳበር አስፈላጊ እንዳልሆነ የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ችግሩ ድሆችን በንግድ ሥራ ውስጥ ማካተት ነው፣ ለሁሉም የሚጠቅም ሀብት ለማድረግ ነው… የተጣሉ ሰዎች የለውጥ ዋና ተዋናይ የሚሆኑበት ዓለም ማለም ይኖርብናል ብለዋል።

ወጣቱ

በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንግዶቻቸው ብዙውን ጊዜ "በሀብት፣ በእድሎች እና የወደፊት ድሆች" ለሆኑ ወጣቶች ትግል ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል። “ሁሉንም ሥራ መማር የምንችለው ያንን ሥራ ስንሰራ ብቻ ነው” በማለት የሚፈለገውን ልምድና ክህሎት በማጣት እንዳይንገላቱ ወጣቶችን እንዲቀጥሩ አበረታቷቸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለወጣቶች “አንድ ትውልድ ተስፋ እንዳይቆርጥ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ፍንጭ በመስጠት ለጋስ ሁኑ” ሲሉ አሳስበዋል።

ማጠቃለያ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አምላክ እንግዶቻቸው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ እና “ደፋር ምርጫዎችን እንዲያደርጉ” እንዲረዳቸው በመጸለይ ንግግራቸውን አጠናቅቀዋል።

“ለምታደርጉት ነገር አመሰግናችኋለሁ” ሲሉ ተናግሯል፥ “አቅኚዎች ናችሁ - ተስፋ አትቁረጡ፣ ነገር ግን አቅኚዎች ሁኑ” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 

 

16 June 2024, 11:53