ፈልግ

ር.ሊ.ጳ  ፍራንችስኮስ ሕሙማንን ለሚከባከቡ የቅዱስ ልብ እኅቶች እና ከቅዱስ ካሚል ማሕበር ደናግላን  ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ሕሙማንን ለሚከባከቡ የቅዱስ ልብ እኅቶች እና ከቅዱስ ካሚል ማሕበር ደናግላን ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሕሙማንን ለሚከባከቡ ገዳማዊያት ለሕሙማን ፍቅር ለመስጠት ደፋር ሁኑ አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሕሙማንን ለሚከባከቡ የቅዱስ ልብ እኅቶች እና ከቅዱስ ካሚል ማሕበር ደናግላን ጋር በቫቲካን የተገናኙ ሲሆን የሚረዷቸውን ሕሙማን እና ድሆችን ለመውደድ ድፍረት ይኑራችሁ ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐሙስ ዕለት ግንቦት 15/2016 ዓ.ም ፣ ሕሙማንን በመንከባከብ ላይ የሚገኙትን የኢየሱስ ቅዱስ ልብ እህቶች ማሕበር አባላትን እና የቅዱስ ካሚል ማህበር አባላት እህቶች ንግግር አድርገዋል።የሁለቱም ማሕበር አባላት የታመሙትንና ድሆችን በመርዳት ላይ ያተኮሩ ናቸው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ንግግራቸውን ሲከፍቱ የእነዚ መንፈሳዊ ማሕበራት አባላት የማሕበራቸውን መስራቾች አርአያ እንዲከተሉ አበረታቷቸዋል፣ ይህም ድፍረታቸውን እና በ19ኛው መቶ ዘመን መገባደጃ ላይ ማሕበራቸውን እንዲመሰርቱ ያደረጋቸውን “የተቀደሰ የፍቅር እብደት” ጠቁመዋል። "ፍቅር ከሌለን እኛም አልቀናል" ሲሉ ተናግሯል።

ሁላችንም ፈውስ እንፈልጋለን

ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን የጀመሩት የእግዚአብሔር አገላጋይ በነበረው በቅዱስ ዮሐንስ ተመስጦ እ.አ.አ በ1881 ዓ.ም በስፔን ሕሙማንን ለመርዳት በቅዱስ ልብ ሆስፒታል አቅራቢዎችን የመሠረቱትን የማሪያ አንጉስቲያስ ጊሜኔዝ፣ የተከበሩት ማሪያ ጆሴፋ ሬሲዮ እና ቅድስት በነዴቶ መኒ አስደናቂ ታሪክ በማስታወስ ጀመሩ ሲሉ በንግግራቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው የአእምሮ ሕመምተኞች በመርዳት አብዮታዊ የሆነ ሐሳብ አፈለቁ ያሉ ሲሆን  "ይህ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ እንቅስቃሴ በጣም ቆንጆ ነው" ብለዋል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጉባኤው “የአምላክን ምሕረት በእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ እንዲያገኝ” ለሌሎች ስቃይና ድህነት ዓይነቶች ዕርዳታ አድርጓል። ሁሉም የሚሳተፉበት እና ለሌሎች መልካም አስተዋጽኦ የሚያበረክት ተግባር ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ይህ ውብ ነው፣ ምክንያቱም በዚህ መንገድ እያንዳንዱ ሰው እንደ ፍላጎቱ እና እንደ ተሸከማቸው ቁስሎች አንድ ላይ ይድናል። እንዲያውም ሁላችንም ፈውስ እንደሚያስፈልገን መዘንጋት የለብንም እርስ በርሳችን መተሳሰብ ለኛ ጠቃሚ ነው፣ ሰውነትን ብቻ ሳይሆን ልብንም ይፈውሰናል” ብለዋል።

መከራ የሚያሸንፈው በፍቅር ብቻ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል ከቅድስት ጁሴፒና ቫኒኒ እና ብጹዕ ሉዊጂ ቴዛ ጋር የቅዱስ ካሚል እህቶች ማሕበር መስራቾች ጨዋነት ተመስጦ ሕሙማንን ለመርዳት በጣሊያን የቅዱስ ካሚል እህቶች ማሕበር ከጥቂት ዓመታት በኋላ የመሠረቱትን መሥራቾችን አስታውሰዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እራሷ በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ስትሰቃይ የነበረችው ይህች ኢጣሊያናዊት ቅድስት በግላዊ የመከራ ልምዷ ተመስጣ እንደነበረች ደጋግማ እንደምትናገር ገልጸው “በፍቅር ብቻ ይሸነፋል” ብለዋል።

ያለ ፍርሃት ማገልገል

ሁለቱ መንፈሳዊ ማሕበሮች የየራሳቸውን አጠቃላይ ስብሰባ ሲያካሂዱ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መነኮሳቱ በማሕበራቸው መሥራቾች “በተመሳሳይ ድፍረት” እንዲበረታቱ አሳስበዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሕመምተኞችና ድሆች አገልግሎት ለሚያከናውኑት ቀጣይነት ያለው ሥራ አመስግነው የማሕበሩ አባል የሆኑት እህቶችን “ፈገግታቸውንና የልብ ደስታን እንዳያጡ” በመጋበዝ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

24 May 2024, 14:37