ፈልግ

በፓፓዋ ኒው ጊኒ የተከሰተው ርዕሰ መሬት ከ670 በላይ ሰዎችን መግደሉ ታወቀ በፓፓዋ ኒው ጊኒ የተከሰተው ርዕሰ መሬት ከ670 በላይ ሰዎችን መግደሉ ታወቀ  (ANSA)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በአደጋ ከወደመችው ፓፑዋ ኒው ጊኒ ሕዝቦች ያላቸውን ቅርብት በድጋሚ ገልጸዋል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመስከረም ወር ሊጎበኟቸው ከተዘጋጁት አገሮች መካከል በምትገኘው ስፍር ቁጥር የሌላቸውን የሰው ህይወት እና የተቀበሩ መንደሮችን ተከትሎ በፓፑዋ ኒው ጊኒ ለተሰቃዩ እና ለተፈናቀሉት ሁሉ የማጽናኛ ቃል አቅርበዋል ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የሟቾች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን ረቡዕ ግንቦት 21/2016 ዓ.ም  ማለዳ ላይ ባደረጉት ንግግር የገለጹ ሲሆን በፓፑዋ ኒው ጊኒ በደረሰው ከባድ የመሬት መንሸራተት ለተጎዱት ሁሉ ያላቸውን ቅርበት ገልጸዋል።

በፓፑዋ ኒው ጊኒ በሚገኙ አንዳንድ መንደሮች በደረሰው ከፍተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ሰዎች የማደርገውን ጸሎት ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።

"እግዚአብሔር ቢፈቅድ በሚቀጥለው መስከረም የማገኛቸውን ቤተሰቦቻቸውን፣ ቤታቸውን ላጡት እና የፓፑዋን ሕዝብ ጌታ መጽናናትን ይስጣቸው” ብለዋል።

በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በኤንጋ ግዛት በሜይፕ-ሙሊታካ አካባቢ የሚገኝ የተራራ ክፍል ባለፈው አርብ መጀመሪያ ሰአታት ላይ ተደርምሷል።

ከ 2,000 በላይ ሰዎች እንደሞቱ ይገመታል፣ በአካባቢው የሚኖሩ እስከ 70,000 የሚደርሱ ሰዎች በአደጋው ​​ተጎድተዋል።

የሟቾች ቁጥር አዲስ ከፍታ ላይ ደርሷል

ይህም ጳጳሱ በሰኞ ዕለት ካወቱት የሐዘን መግለጫ መልእክት በኋላ ለተሰቃዩ ሰዎች ያቀረቡትን የቅርብ ጊዜ ጥሪ የሚጨምር ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የእርዳታ ጥረታቸውን በሚቀጥሉበት ጊዜ ለሲቪል ባለስልጣናት እና ለአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ማበረታቻቸውን አቅርበዋል እናም ለሁሉም "የማፅናኛ እና የጥንካሬ መለኮታዊ በረከቶችን" ለምነዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመስከረም ወር ኢንዶኔዥያ፣ ሲንጋፖር እና ቲሞር ሌስቴ ጋር በመሆን ሀገሪቱን ሊጎበኙ እቅድ ይዘው ነበር።  

 

29 May 2024, 13:46