ፈልግ

የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ፣ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን የሐዘን መግለጫ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ፣ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን የሐዘን መግለጫ  (ANSA)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኢራን ፕሬዝዳንት ራይሲ ሞት የሐዘን መግለጫ መልእክት ልከዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ፣ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዶላሊያን እ.አ.አ በግንቦት 19/2024 ዓ.ም በሄሊኮፕተር አደጋ ለሞቱት ሁሉ ሀዘናቸውን የሚገልጽ የቴሌግራም መልዕክት ልከዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጻፉት የቴሌግራም መልእክት ላይ የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ይፋ እንዳደርገው “የሟቾቹን ነፍስ ለልዑል እግዚአብሔር ምህረት አደራ በመስጠት በደረሰባቸው ሀዘን ላይ በተለይም ለቤተሰቦቻቸው ጸሎት በማድረግ ፣ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ከአገራቸው ጋር ያላቸውን መንፈሳዊ ቅርበት” ገልጿል ሲል አስታውቋል።

የቴሌግራም መልእክቱ የተላከው የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ መሪ ለአምስት ቀናት የሃዘን ቀናትን ላወጁት ታላቁ አያቶላ ሰይድ አሊ ሆሴይኒ ካሜኒ ነው።

ፕሬዝዳንት ራይሲ እና አጃቢዎቻቸው ከፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ጋር ተገናኝተው በነበሩበት ጎረቤት አዘርባጃን ጎብኝተው ሲመለሱ በነበሩበት ተራራማ አካባቢ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

20 May 2024, 15:56