ፈልግ

እስራኤል በደቡባዊ የጋዛ ሰርጥ በፈጸመችው የቦንብ ድብደባ የሚሰቃዩ ሕዝቦች  እስራኤል በደቡባዊ የጋዛ ሰርጥ በፈጸመችው የቦንብ ድብደባ የሚሰቃዩ ሕዝቦች  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ላይ ውይይት እንዲደረግ ይጸልያሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በፍልስጤም ፣ በእስራኤል እና በዩክሬን ሰላም እንዲሰፍን ልባዊ ልመና አቅርበዋል ፣ ግጭቶችን ለመፍታት ውይይት እንዲደረግ እና የተጎዱትን ሰዎች ስቃይ በማስታወስ ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በድጋሚ ጸሎታቸውን ወደ ዓለም ሰላም አዙረዋል። በጎሮጎርሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በአራተኛው የፋሲካ እለት ሰንበት ላይ “የሰላም ንግሥት ሆይ ደስ ይበለሽ፣ እንደተናግረው ከሙታን ተነስቷልና...” የተሰኘውን የማርያም ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ቅዱስነታቸው ከደገሙ በኋላ ለመላው ዓለም ባስተላለፉት መልእክት  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በድጋሚ በመካከለኛው ምስራቅ ውይይት፣ ድርድር እና የዲፕሎማሲ ንግግሮች ሊሰፉ እንደሚችሉ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። “በማስረጃው አመክንዮ” እንዳትሸነፍ ሲሉም አሳስቧል።

"በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ሁኔታ በጭንቀት እና በሀዘን መመልከቴን እቀጥላለሁ። ጦርነትን ላለመቀበል፣  ነገር ግን ለውይይት እና ለዲፕሎማሲ ቅድሚያ እንዲሰጥ ደግሜ ጥሪ አቀርባለሁ፣ ይህም ብዙ ሊሳካ ይችላል። በየቀኑ ለፍልስጤም ሰላም እጸልያለሁ። እናም እስራኤላውያን እና ፍልስጤም እነዚህ ሁለቱ ህዝቦች በቅርቡ ስቃያቸውን እንዲያቆሙ ተስፋ በማድረግ ነው።

ዩክሬን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደተለመደው በዩክሬን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት አስታውሰዋል። ግጭት የበዛባትን ምድር “በጣም እየተሰቃየች ያለችውን” ዓለም እንዳትጨልም ጋብዟል።

22 April 2024, 17:02