ፈልግ

ቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ቅዱስ ፒዮስ 10ኛ  

ር.ሊ.ጳ ሰ ፍራንችስኮስ ቅዱስ ፒዮስ 10ኛ በስቃይ ላይ ሰዎች ቅርብ የሆነ ጳጳስ ነበሩ ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአባ ሉሲዮ ቦኖራ የተጻፈ እና በጳጳስ ቅዱስ ፒዮስ 10ኛ የሕይወት ታሪክ ላይ ባጠነጠነው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የኖሩ፣ በትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ጥልቅ የሆነ የቤተ ክርስቲያኗን አስተምህሮ አጽኖት ሰጥተው ለመዕመናን ተደራሽ እንዲሆን ያደረጉ፣ የአንደኛው የዓለም ጦርነት በተነሣበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ሲያደርጉ የነበሩ፣ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ፒዮስ 10ኛ የሕይወት ታሪክ ዙሪያ ላይ ለሚያጠነጥነው መጽሐፍ የመግቢያ መቅድም መጻፋቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"ፒየስ 10ኛ ከቅዱስ ቁርባን ውጭ እና የተገለጡ እውነቶች ካልተዋሃዱ የግል እምነት እንደሚዳከም እና እንደሚሞት መላው ቤተ ክርስቲያን እንዲረዳ ያደረጉ ጳጳስ ነበር" ሲሉ መጽሐፉ መግቢያ ላይ ባሰፈሩት የመቅድም ጹሑፍ ላይ ያስፈሩት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያን ውዳሴ ከቀድሞው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ፒዮስ 10ኛ (1903-1914) “የፒየስ 10ኛ መታሰቢያ። ዘመናዊ ግርማ” በሚል ርዕስ አዲስ ለቀረበው መጽሐፍ የመግቢያ መቅድም ጽፈዋል።

ቅዱስ ጳጳስ አንደኛው የዓለም ጦርነት ሲፈነዳ አልቅሰው ነበር

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ይፋ በሆነው መጽሐፍ ላይ ባሰፈሩት የመግቢያ መቅድም ላይ በተለቀቀው የመቅድመ ጽሑፋቸው ላይ የቦነስ አይረስ ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ወቅት በአመት አንዴ ከካታኪስቶች ጋር ይገናኙ እንደ ነበረ የገለጹ ሲሆን ለእዚህ ተግባራቸው ከፈተኛ መነሳሻ የሆኑት የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጵሳት ፒዮስ 10ኛ እንደ ነበሩ ቅዱስነታቸው በመቅድም ጽሑፋቸው ገልጸዋል።

“ልጆችንና ጎልማሶችን የእምነትን እውነት ለማስተማር ከወሰኑት ሰዎች ጋር ጊዜ ማሳለፍ ያስደስተኛል” ሲሉ የጻፉ ሲሆን  “ፒየስ 10ኛ ደግሞ የካቴኬሲስቶች ሊቀ ጳጳስ በመባል ይታወቁ ነበር” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አክለውም ፒየስ 10ኛ “የዋህ ሆኖም ጠንካራ ጳጳስ፣ ትሑት እና ግልጽ ጳጳስ” ነበሩ ብለዋል።

ሟቹ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት “[የመጀመሪያው] የዓለም ጦርነት ሲጀምር አለቀሱ” እና “ኃያላኑን መሳሪያ እንዲያወርዱ” ተማጽነው ነበር በማለት በመግቢያ የመቅድም ጽሑፋቸው ላይ ያስፈሩት ቅዱስነታቸው  “በዚህ በዘመናዊው ዓለም አሳዛኝ ወቅት ከእርሳቸው ጋር ምን ያህል ቅርበት አሁንም እንዳለኝ ይሰማኛል” ብለዋል።

በመከራ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች የነበራቸው ቅርበት

በተጨማሪም “ከታናናሾች፣ ድሆች፣ ችግረኞች፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ተጠቂዎች፣ ችግረኞችና በተፈጥሮ አደጋዎች ለሚሰቃዩ” ሰዎች ቅዱስ ፒዮስ 10ኛ የነበራቸውን ቅርበት ይገልጹ እንደ ነበረ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ገልጸዋል።

18 April 2024, 22:15