ፈልግ

በጋና አክራ በሚካሄድ ላይ በሚገኘው የአራተኛው ዓለም አቀፍ የክርስቲያን ሸንጎ በጋና አክራ በሚካሄድ ላይ በሚገኘው የአራተኛው ዓለም አቀፍ የክርስቲያን ሸንጎ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ለክርስቲያናዊ አንድነት ግንባታ የሚረዳውን እምነት እና ህብረት ያበረታታሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮ በጋና አክራ በሚካሄድ ላይ በሚገኘው የአራተኛው ዓለም አቀፍ የክርስቲያን ሸንጎ ስብሰባ ላይ ለተሳታፊዎች ባደረጉት ንግግር ሁሉም ሰው እምነቱን እንዲያጠናክር እና የወንድማማችነት ፍቅር እንዲያንሰራራ በማበረታታት ክርስቲያኖች የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች በውይይት ለመፍታት የተጠሩ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን ዓለም አቀፍ የክርስቲያን ማህበረሰብ የሚያጋጥመውን ማንኛውንም ፈተና እና ተግዳሮት በንግግር መፍታት ይኖርበታል ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከሚያዚያ 7 እስከ ሚያዚያ 12/2016 ዓ.ም በጋና አክራ እየተካሄደ ለሚገኘው አራተኛው ዓለም አቀፍ የክርስቲያን ሸንጎ ስብሰባ ተሳታፊዎች ሰላምታ ልከዋል። ዓለም አቀፋዊው ስብሰባ ከተለያዩ አለም የተውጣጡ ክርስቲያኖችን ለአንድ ልዩ የጸሎት፣ የአምልኮ፣ የውይይት እና የተልእኮ ጊዜ ያሰባስባል።

“ዓለም ሊያውቀው ይችላል” የሚለው ጭብጥ በዛሬው ዓለም የኢየሱስ ክርስቶስን ፍቅርና እውነት ለሕዝቦች በተሻለ መንገድ ለማወጅ እንዴት ክርስቶስን መመስከር እንዳለብን ይዳስሳል፣ ዓላማውም “አንድ ላይ ሆነን ለእግዚአብሔር ክብር ለውጥን እናምጣ" የሚል ዓላማ ያነገበ እንደ ሆነም ተገልጿል።

ቆንጆ የእምነት ስብስብ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለተሰበሰቡት ሁሉ “ከልብ የመነጨ ሰላምታ” ያቀረቡ ሲሆን “የዘመኑ ክርስትና ያማረ ሞዛይክ” የሚያንፀባርቅ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች እንደመሆናችን መጠን አንድን ማንነት የሚጋራውን ዓለም አቀፋዊ ስብጥር አወድሰዋል።

በቫቲካን የክርስቲያን ሕብረት ለምፍጠር የሚሰራው እና የክርስቲያኖች እንድነትን ለመፍጠር የሚተጋው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና ጸኃፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፍላቪዮ ፓቼ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱን ቃል በማንበብ በስብሰባው ላይ ተካፋይ ሆነው የእራሳቸው ንግግር አክለው አቅርበዋል።

ክርስቲያኖች ወደ አንድነት እና ፍቅር ተጠርቷል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ዓለም እንዲያውቅ” (ዮሐንስ 17፡23ለ) የሚለውን ጭብጥ በመንካት ክርስቲያኖች “ስለ ዓለም እንዲመሰክሩ በግል እና በቤተ ክርስቲያን ሕይወታቸው የቅድስት የሥላሴን አንድነትና ፍቅር እንዲይዙ ተጠርተዋል” ብለዋል። በመከፋፈል እና በፉክክር ጠባሳ" የተፈጠረውን ክፍፍል ክርስቲያኖች በውይይት ሊያስወግዱ የገባል ብለዋል።

ከተልእኮ ጋር የተሳሰረ ሕብረት

አንድነት “የእግዚአብሔርን መንግሥት ራዕይ ለመቀበል ቁልፍ ነው” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አጽንኦት ሰጥተው በመልእክታቸው የገለጹ ሲሆን ይህ ደግሞ “በኢኩመኒዝም (ሕብረት) እና በክርስቲያናዊ ተልእኮ መካከል ያለውን ውስጣዊ ትስስር” ይጠይቃል ብለዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዓለም አቀፉ የክርስቲያን ሸንጎ በ25 ዓመታት ታሪኩ ውስጥ የተለያዩ የክርስትና እምነት ታሪካዊ መግለጫዎች አባላት "በክርስቶስ በመገናኘት በመከባበርና በወንድማማችነት የሚያድጉበትን" ቦታዎችን በመስጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።

በማጠቃለያው ስብሰባው ሁሉም ሰው እምነቱን እንዲያጠናክር፣ የወንድማማችነት ፍቅር እንዲያሳድግ፣በአንድነት ሲፀልዩ፣ ሲወያዩ እና በአለም አቀፍ የክርስቲያን ማህበረሰብ ፈተናዎች ላይ ልምድ እንዲለዋወጡ መጸለይ እንደሚገባ የገለጹ ሲሆን “ለሁላችሁም የኃያሉን አምላክ በረከቶች በእናንተ ላይ እንዲፈስ እማጸናለሁ፣ እናም ስብሰባው በሁሉም ክርስቲያኖች መካከል ያለውን የሚታየውን አንድነት እንዲያጎለብት እጸልያለሁ” ማለታቸው ተገልጿል።

ሊቀ ጳጳስ ፓቼ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን መልእክት ካነበቡ በኋላ፣ ከእዚያ በመቀጠል ተሳታፊዎችን በማነጋገር የራሳቸውን አስተዋጽዖ አበርክተዋል። የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱን ቃል በማስተጋባት በስብሰባው ላይ የተወከሉትን “ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት፣ ወንጌላውያን፣ ጴንጤቆስጤ፣ ገለልተኛ አብያተ ክርስቲያናት እና ማኅበረ ቅዱሳን ጨምሮ የበለጸገ የክርስትና አንድነት ለመፍጠር የሚደርገውን ጥረት” አወድሰዋል።

ዓለም አቀፍ የክርስቲያን ሸንጎ “ሕያው እምነትን” በመጋራት እና በክርስቲያን መሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ማሳደግ ትኩረት መስጠቱ “ዋጋ ያለው የሕብረት መሣሪያ” ሆኗል ብለዋል ሊቀ ጳጳስ ፓቼ፣ የአስተምህሮ ልዩነቶችን ለመፍታት፣ የእምነት ልምዶችን ለመለዋወጥ፣ መግባባትን ከማጠናከር እና ከማጎልበት በተጨማሪ ወንድማማችነት “ዋጋ ያለው የክርስቲያን ሕብረት መሣሪያ” ሆኗል ብለዋል።

ሊቀ ጳጳስ ፓቼ በተጨማሪም ክርስቲያናዊ ምስክርነት በአንድነት “የወንጌልን የማስታረቅ ኃይል” እንዴት እንደሚያሳይ እና ይህ አንድነት “ከሰዎች ልዩነት በላይ ያለውን የክርስትና እምነት ኃይል ያሳያል፣ በወንድማማች ፍቅር፣ እርስ በርስ በመከባበርና በወንድማማችነት የተመሰረተ ሕያው ማኅበረሰብ እንዲፈጠር ያደርጋል” ብለዋል።

በማጠቃለያው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ የሲኖዶስ ሂደት ውስጥ እንዴት እንደተሰማራች አስታውሰዋል፣ “ለሲኖዶሳዊ ቤተ ክርስቲያን፡ ሕብርት፣ ተሳትፎ፣ ተልእኮ” በሚል መሪ ቃል ባለፈው ጥቅምት ወር በተካሄደው የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ በርካታ ወንድማማች ልዑካንን ያሳተፈ የተለያዩ ክርስቲያናዊ ወጎችን ያካተተ ነው። በመጪው ጥቅምት ለሚደረገው ማጠቃለያ ትልቅ ቁጥር ተጋብዘዋል። በሲኖዶስ ስላደረጉት ተሳትፎ እያመሰገኑ፣ ሲኖዶስ “በእምነት አንድነት መንፈስ በጋራ ለመጓዝ ፍላጎት እንዳለው ግልጽና ተአማኒነት ያለው ምልክት እንዳስተላለፈ”፣ ክርስቲያኖችን አንድ የሚያደርገው ከምን የበለጠና ጥልቅ ነው በማለት አረጋግጠዋል።

እዚህ ጋና ውስጥ የሚገኘው ይህ ስብሰባ “በሲኖዶሳዊው መንፈስ የታነፀ ነው” በማለት አክለውም የተናገሩት ሊቀ ጳጳስ ፓቼ “በጸሎት እና በጋራ በመስራት ሀብታችንን፣ ችሎታችንን እና ግንዛቤያችንን በማዋሃድ የጋራ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና ወንጌልን በጋራ ለማራመድ እንችላለን” ብለዋል።

 

19 April 2024, 16:40