ፈልግ

በብራዚል የማሕበራዊ ሳምንት ቀን መከበሩ ተገለጸ በብራዚል የማሕበራዊ ሳምንት ቀን መከበሩ ተገለጸ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በብራዚል ለተከበረው ማሕበራዊ ሳምንት ‘የኢየሱስን በድሆች ፊት ላይ እንይ’ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የብራዚል ጳጳሳት ጉባኤ ባዘጋጀው እና ረቡዕ መጋቢት 11/2016 ዓ.ም በብራዚሊ የጀመረው 6ኛው የብራዚል ማህበራዊ ሳምንት ተሳታፊዎች የማበረታቻ መልእክት ያለኩ ሲሆን "ሁለንተናዊ ወንድማማችነት እና ማህበራዊ ወዳጅነት የሚኖርበትን የበለጠ ፍትሃዊ ማህበረሰብ" ለመገንባት ሁሉም ጠንክረው ይሰሩ ዘንድ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"በማህበራዊ ኢፍትሃዊነት ምክንያት በድህነት ውስጥ ለመኖር በሚገደዱ ሰዎች ላይ በግዴለሽነት መንፈስ እንዳንኖር የሚመክረንን የኢየሱስ ፊት ለማየት እንሞክር ምክንያቱም እርሱ ራሱ እንደተናገረው  “እውነት እውነት እላችኋለሁ የኔ ደቀ መዝሙር በመሆኑ ከነዚህ ታናናሾች ለአንዱ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ እንኳን የሚሰጥ ሰው ዋጋውን አያጣም” (የማቴዎስ ወንጌል 10.42)  በማለቱ የተነሳ የተቸገሩትን ማገዝ በራሱ ጌታን እንደማገዝ ይቆጠራል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በብራዚል ከመጋቢት 11-13/2016 ዓ.ም. በብራዚል እየተካሄደ ለሚገኘው የስድስተኛው የብራዚል ማህበራዊ ሳምንት ተሳታፊዎች በላኩት መልእክት ያቀረቡት ግዣ ነው።

ዝግጅቱ የብራዚል ጳጳሳት ብሔራዊ ጉባኤ የሐዋርያዊ አገልግሎት የተዘጋጀ ሲሆን “የምንፈልገው ብራዚል፣ የሕዝቦች መልካም ኑሮ” በሚል መሪ ቃል ተዘጋጅቷል።

ወደ "ቤተክርስቲያን በተግባር" የሚወስድ መንገድ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባስተላለፉት መልእክት የእዚህን ማሕበር አነሳስ አድንቀው “ለስብሰባው መልካም እድገትና ፍሬያማነት” ጸሎታቸውን አረጋግጠዋል።

ለመሬት፣ ለቤት እና ለስራ የሚያደርጉት ትግል።

በተጨማሪም፣ ተነሳሽነት፣ አዲስ፣ የበለጠ በአብሮነት ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ እና የዴሞክራሲ እሴቶችን ማደስ፣ በሀገሪቱ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ እውነተኛ ህዝባዊ ተሳትፎ ያለበትን ማህበረሰብ ለመገንባት የሚያግዝ ነው ብለዋል።

መሬት፣ ቤት፣ ስራ

ከዚህ አንጻር፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከወጣት ብራዚላውያን ጋር፣ "የክላራ እና የፍራንችስኮስ ኢኮኖሚ" እንዲሁም ላቀረቡት ጥሪ እ.አ.አ በ2014 ዓ.ም የዓለም ታዋቂ ንቅናቄዎች ስብሰባ ተሳታፊዎች ምላሽ እንዲሰጡ ስላደረጉ ምስጋና አቅርበዋል፣ ወደ "በጣም ተጨባጭ ፍላጎት" የሚያመራ እንቅስቃሴ በመሆኑ ሁል ጊዜም ለድሆች መታገል ይኖርብናል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት ተጨባጭ ፍላጎት "እያንዳንዱ አባት እና እናቶች ለልጆቻቸው የሚመኙት ነገር ነው፣ ፍላጎት ሁሉም ሰው ሊደርስበት የሚገባ ነገር ግን ዛሬ ሊፈጸም የሚገባው ነው" ሲሉ በምሬት ተናግሯል "በሚያሳዝን ሁኔታ ፍትህ በጣም ርቆናል። በብዙ ሰዎች ሕይወት ውስጥ መሬት፣ ቤት እና ሥራ እውን መሆን፡- እስካሁን አልቻሉም ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሕይዎት ጉዳዮች ላይ የቤተክርስቲያኗ እና የህዝብ ተወካዮች ስብስብ የሆነው ከብራዚል ማህበራዊ ሳምንት ጋር የተያያዘው ተነሳሽነት በይበልጥ ፍትሃዊ የሆነ ማህበረሰብ እንዲኖር ብዙ ፍሬዎችን እንደሚያፈራ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። የትኛውም ተጨባጭ አዎንታዊ ተግባር "ሁለንተናዊ ወንድማማችነት እና ማህበራዊ ጓደኝነት ልምድ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

22 March 2024, 15:23