ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በሕይወታችን ላይ ዘላቂ ምልክት ለመተው የቅዱስ ሳምንት አስፈላጊነትን ያስታውሳሉ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለስፔን ሜሪዳ ማኅበረ ቅዱሳን ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት፣ ቅዱስ ሳምንት ለጸሎት የምንሰጥበት “የጸጋ ጊዜ” እንደሆነ እና በጣም ለተቸገሩ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የምናስታውስበት ወቅት እንደሆነ ገልጸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ሜሪዳ ጥንታዊ የሮማውያን ሐውልቶች የሚገኙባት የስፔን በጣም ዝነኛ ከሆኑ ከተሞች አንዷ ነች፣ ስለዚህም “የስፓኒሽ ሮም” ተብላለች። ከክርስቶስ ልደት በፊት 25 አመተ አለም በአውግስጦስ ወታደሮች እንደ ቅኝ ግዛት የተመሰረተው ታሪካዊ ማዕከሉ የትራጃን ቅስት ግንብ፣ የሮማን ድልድይ፣ የዲያና ቤተ መቅደስ እና የሮማውያን አምፊቲያትር እና ሌሎች ቦታዎችን አቅፎ የያዘ ስፍራ ነው። በቅዱስ ሳምንትም ሃይማኖታዊ ውደት እና የመስቀል መንገድ ጸሎት የሚካሄዱት በእነዚህ ቦታዎች ዙሪያ ነው።

ከሜሪዳ ጋር መንፈሳዊ ቅርበት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሃይማኖታዊ ክንውኖችን ለሚያራምዱ በርካታ የአካባቢ ማኅበረሰቦች ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት፣ ከሁለት ሺህ ዓመታት በላይ በጥንት ዘመን የነበሩ የሰው ልጆችን ታሪክ የቀየረባቸውን ዘመናት ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ጥቂት ከተሞች እንዳሉ ጠቁመዋል።

በሜሪዳ ላሉ ሁሉ መንፈሳዊ ቅርበት እንዳላቸው ያረጋገጡት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የመስቀል መንገድ ጸሎት በሮም ኮሎሲየም ሲመሩ በልዩ ሁኔታ እንደሚያስታውሷቸው ገልፀው በሜሪዳ የሮማ አምፊቲያትር ከዓለም ዙሪያ ካሉ ምዕመናን ጋር በጸሎት መንፈስ በመጣመር እንደ ሚከናወን ቅዱስነታቸው ገልሰዋል።

የቅዱስ ሳምንት የማይጠፋ ምልክት

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሜሪዳ ባዳጆዝ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ልዩ ዓመት፣ የኡላሊያን ኢዮቤልዩ ዓመት፣ ሜሪዳ በስፔን የክርስትና መገኛ እንድትሆን እና የታሪክ ጉዞዎች መዳረሻ እንድትሆን ላደረገችው ወጣት ሰማዕት ቅድስት ኡላሊያን የምትዘከርበትን ልዩ ዓመት እያከበሩ እንዳለ አስታውሰዋል።

የቅዱስ ሳምንት አከባበርን ለሚያዘጋጁት ማኅበረ ቅዱሳን ባደረጉት ንግግር የቅዱስ ሳምንት ተሞክሮ በተሳተፉት ላይ “የማይጠፋና የማይሻር አሻራ ያሳረፈ” መሆኑን በማሳሰብ የኢየሱስ ሕማማት እንደገና መታየቱ “ትዕይንት እንዳልሆነ አስታውሱ” በማለት አሳስበዋል። ነገር ግን የመዳናችን አዋጅ" እና "በዚህም ምክንያት የራሱን አሻራ ጥሎ ማለፍ አለበት" ብለዋል።

የእግዚአብሔር እና የባልንጄራ ፍቅር

በተለይም የደጉ ሳምራዊ ለቆሰሉ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን የሚንከባከበውን ምሳሌ በመከተል ለጸሎት፣ የእግዚአብሔርን ቃል በማዳመጥ ጊዜ ማሳለፍ በቅዱስ ሳምንት ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የዘንድሮውን የአብይ ጾም መልእክት በመጥቀስ “እግዚአብሔርን መውደድና ባልንጀራን መውደድ አንድ ፍቅር ናቸው...በእግዚአብሔር ፊት ወንድማማቾችና እህቶች እርስ በርሳችን ተግባብተናል” ብለዋል።

ልባችንን ለሌሎች በመክፈት።

ቅዱሱ ሳምንት "የልባችንን ደጆች እንድንከፍት ጌታ የሚሰጠን የጸጋ ጊዜ ነው" በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው ኢየሱስን እና ሌሎችን ለማግኘት ወደ ውጭ መውጣታችን እንዲሁም የእኛን ብርሃን እና ደስታ ለማምጣት እምነት የምናዳብርበት ወቅት ነው፣ “እጃችንን፣ እግሮቻችንን፣ ልባችንን እንደ ምናቀርብ እያወቅን የሚመራንና መንገዱን የሚያሳየን እግዚአብሔር መሆኑን እያወቅን ሁሉም በፍቅርና በእግዚአብሔር ርኅራኄ፣ በአክብሮትና በትዕግስት እንዲወጣ አበረታቷል።

ለቤተሰብ እና ለተቸገሩ ሰዎች ጸሎት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለጥንቷ የስፔን ከተማ ያስተላለፉትን የወንድማማችነት መልእክታቸውን ሲያጠቃልሉ “የሚወዷቸው ታማሚ ያላቸው” ቤተሰቦች፣ ብቻቸውን ላሉት፣ ኢኮኖሚያዊ ችግር ላጋጠማቸው እና በመጨረሻም ራሳቸውን መስጠት ለሚችሉ ወጣቶች ልዩ ቡራኬያቸውን የሰጡ ሲሆን  አሁን እና ወደፊት ለሜሪዳ ሕዝቦች ያላቸውን የወንድማማችነት አጋርነት ቅዱስነታቸው በድጋሚ ገልጸዋል።

 

18 March 2024, 13:17