ፈልግ

እስራኤል በደቡባዊ የጋዛ ሰርጥ በፈጸመችው የቦንብ ድብደባ የፈረሱ መኖሪያ ቤቶች እስራኤል በደቡባዊ የጋዛ ሰርጥ በፈጸመችው የቦንብ ድብደባ የፈረሱ መኖሪያ ቤቶች   (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችስኮስ፡- ‘በጦርነት አሰቃቂ ሁኔታ ለሚሰቃዩ ሰዎች ጸልዩ’ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ክርስቲያኖች በጦርነት አስከፊ ሁኔታ ለሚሰቃዩ ሰዎች ሁሉ እንዲጸልዩ እና በዓለማችን ሰላም እንዲመጣ የበኩላቸውን አስተዋጾ እንዲያደርጉ ምዕመናን ጋብዘዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“ወንድሞችና እህቶች፣ በዩክሬንና በቅድስት ምድር እንዲሁም በሌሎች የዓለም ክፍሎች በአስደንጋጭ ጦርነት ለሚሰቃዩ ሰዎች እንድትጸልዩ ግብዣዬን በድጋሚ አቀርባለሁ” ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን የተናገሩት ደግሞ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ረቡዕ የካቲት 27/2016 ዓ.ም በተደረገው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ማብቅያ ላይ እንደነበረም ተዘግቧል።

"ስለ ሰላም እንጸልይ!" እናም "የሰላምን ስጦታ ጌታን እንለምነው" ማለታቸው ተግልጿል።

ለሰላም ባቀረቡ ተደጋጋሚ ጥሪ ላይ ቅዱስ አባታችን በተለይ ዩክሬንን እና ቅድስት ሀገርን ጠቅሰዋል።

የዩክሬን መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት በሩሲያ ሃይሎች ያልተቋረጠ የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃቶች ማክሰኞ የካቲት 26/2016 ዓ.ም ምሽት የኪየቭ እና የኦዴሳ ክልሎችን ጨምሮ በተለያዩ የዩክሬን ከተሞች ላይ ጥቃት አድርሰዋል።

በጋዛ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን የፍልስጤም ተጎጂዎች ቁጥር ከ30,700 በላይ የሆነው የእስራኤል ጦር የመሬት ጥቃት ከጀመረ በኋላ ነው።

እነዚህ አኃዞች እ.አ.አ ከጥቅምት 7 ጀምሮ ወደ 72,150 የሚደርሱ ጉዳቶችን ከዘገበው የጋዛ ሰርጥ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተገኘ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 86 ሰዎች ሲሞቱ 113 ሰዎች ቆስለዋል።

የዐብይ ጾም ጉዞ

በወቅቱ በሥፍራው ለነበሩ መዕመናን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ ተናገሩት ከሆነ ክርስቲያኖችም ለፋሲካ በአብይ ጾም በምናደርገው ጉዞ በታማኝነት እንዲቀጥሉ ጋብዘዋል።

“በዚህ የዐብይ ጾም ቀናት ህይወታችሁን ከሚጋርዱበት ነገር ሁሉ ራሳችሁን ነፃ ለማውጣት በድፍረት በትጋት ቀጥሉ፤ በፍጹም ልባችሁ ወደ ዘላለማዊ ፍቅር ወደ ወደደን ወደ እግዚአብሔር እንድትመለሱ” ሲሉ ጥሪ ካቀረቡ በኋላ ቅዱስነታቸው ምልእክታቸውን አጠናቀዋል።

06 March 2024, 16:05