ፈልግ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ቃል ቃል ከገቡ በኋላ በሄይቲ ዋና ከተማ ፀጥ መስፈን ጀምሯል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ቃል ቃል ከገቡ በኋላ በሄይቲ ዋና ከተማ ፀጥ መስፈን ጀምሯል 

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በሄይቲ ታግተው በተለቀቁ ሰዎች እፎይታ እንደ ተሰማቸው ገለጹ!

በእሁድ መጋቢት 8/2016 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት በሄይቲ ታግተው ከነበሩት ስድስት ሰዎች መካከል አራቱ በመፈታታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። አሁንም በእስር ላይ የሚገኙት እንዲፈቱ ቅዱስነታቸው የተማጸኑ ሲሆን፣ በጦርነት ለተጎዱት ዩክሬን፣ ፍልስጤም እና እስራኤል፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶሪያ ጸሎቶችን አቅርቧል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁዱ የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰበው ሕዝብ ንግግር ባደረጉበት ወቅት፣ ከአንድ ሳምንት ገደማ በፊት በሄይቲ ታግተው ከነበሩት ስድስት ገዳማዊያን መካከል አራቱ እና አድን መምህር ከእስር መፈታታቸው እፎይታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል። ሁለቱ በእስር ላይ ይገኛሉ፣ እናም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተቻለ ፍጥነት እንዲፈቱ እንዲሁም አሁንም "በአመጽ በተሞላው በተወዳጅ ሀገር" ውስጥ ለታሰሩት ሁሉ የይግባኝ ጥሪ አቅርበዋል ። የቅዱስ ልብ ወንድሞች ማኅበር አባላት የሆኑት ስድስቱ ገዳማዊያን  እ.አ.አ  ባለፈው የካቲት 23/2024 ዓ.ም ነበር ታግተው የተወሰዱት።

ለጋራ ጥቅም ተባበሩ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሄይቲ የሚገኙ ሁሉም የፖለቲካ እና የማህበራዊ መሪዎች ጠባብ ፍላጎቶችን በመተው "የጋራ ጥቅምን ለማስከበር በአብሮነት መንፈስ እንዲሰማሩ እና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ እርዳታ ሀገር ውስጥ ሰላማዊ ሽግግርን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል። በዜጎች መካከል የነበረውን ጸጥታ ወደነበረበት ቦታ መመለስ የሚችሉ ጠንካራ ተቋማት የታጠቁ አመጸኞችን ትጥቅ እንዲያስፈቱ ቅዱስነታቸው አክለው ትሪ አቅርበዋል።

በጦርነት ለተጎዱ ህዝቦች ጸልዩ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጦርነት ለተጎዱት የዩክሬን፣ ፍልስጤም እና እስራኤል እና ደቡብ ሱዳን ህዝቦች ሁሉም ሰው መጸለይን እንዲቀጥል ጠይቀዋል። የሶሪያን ሕዝብ በማስታወስ፣ በዚያ ያለው ሕዝብ “ለረዥም ጊዜ በጦርነት ምክንያት ብዙ መከራ ሲደርስባቸው” ችግራቸውን እንዳንረሳው ጠይቀዋል።

 

18 March 2024, 13:13