ፈልግ

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀም እ.አ.አ በመጋቢት 8/2024 ዓ.ም ተከብሮ መዋሉ ተገለጸ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀም እ.አ.አ በመጋቢት 8/2024 ዓ.ም ተከብሮ መዋሉ ተገለጸ  (ANSA)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሁሉም ሴቶች መብት እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል

በየዓመቱ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን እ.አ.አ በመጋቢት 08/2024 ዓ.ም አርብ ቀን ተከብሮ ማለፉን በማስታወስ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለሁሉም ሴቶች በተለይም ሰብዓዊ ክብራቸው ላልተከበረላቸው ሰዎች ያላቸውን ቅርበት ገልጸዋል። በዚህ ዙሪያ በሁሉም ተቋማት አሁንም ብዙ የሚቀሩ ስራዎች አሉ ብለዋል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁዱ መጋቢት 1/2016 የመልአከ እግዚአብሕእር ጸሎት ከተጠናቀቀ በኋላ በቫቲካን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ንግግር ባደረጉበት ወቅት ከሁለት ቀናት በፊት ዓመታዊውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተከብሮ ማለፉን አስታውሰዋል። በዓለም ዙሪያ ላሉ ሴቶች በተለይም ክብራቸው ላልተከበረላቸው ሁሉ ያላቸውን ቅርበት መግለጻቸው ይታወሳል።  

ገና ብዙ የሚቀረው ነገር አለ

የሴቶችን የእኩልነት ክብር ለማስጠበቅ በተጨባጭ እውቅና እንዲሰጠው በእያንዳንዳችን አሁንም ብዙ የሚቀረው ነገር እንዳለ የገለጹት ቅዱስነታቸው ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተቋማት የሴቶችን ፣የህይወት ተሸካሚዎችን ፣አስፈላጊ የኑሮ ሁኔታዎችን በማቅረብ የህይወት ስጦታን ተቀብለው ልጆቻቸውን የተከበሩ እንዲሆኑ በማድረግ የእያንዳንዱን ሰው ክብር የመጠበቅ እና የማሳደግ መሰረታዊ ግዴታ እንዳለባቸው አስታውሰዋል።

11 March 2024, 11:52