ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የተከበራችሁ ካህናት፣ ሐዘን ይቀድሳችሁ ማለታቸው ተገለጸ!

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማሕበረሰቦች ዘንድ ሐሙስ መጋቢት 19/2016 ዓ.ም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት ከሐዋርያቱ ጋር የመጨረሻ እራት የበላበት፣ የሐዋርያቱን እግር ያጠበበት፣ ምስጢረ ቅዱስ ቁርባን እና ምስጢረ ክህነትን የመሰረተበት እለት ተክብሮ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን ይህ በዓል በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በተከበረበት ወቅት በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት የተከበራችሁ ካህናት የክርስቶስ ሐዘን ይቀድሳችሁ ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ ባደረጉት ስብከት ካህናትን በጀግንነት ለሚያከናውኑት ምስክርነት አመስግነዋል፣ ነገር ግን ድክመቶችን፣ ስሕተቶችን እና የደነደነ ልብን ወደ ክርስቶስ በመቅረብ እና በአዲስ መልክ ለመጀመር ዕድሉን እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል።

"ውድ ካህናት ስለ ክፍት እና ታዛዥ ልቦቻችሁ አመሰግናለው። ስለድካማችሁ እና ስለ እንባዎቻችሁ ሁሉ እናመሰግናለን። ዛሬ በዓለማችን ላይ ላሉ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የእግዚአብሔርን የምሕረት ተአምር ስለምታደርሱ እናመሰግናለን። ጌታ መፅናናትን ይስጣችሁ። ያበርታችሁ፣ ይሸልማችሁ” ማለታቸው ተገልጿል።

የጸሎተ ሐሙስ መስዋዕተ ቅዳሴ በቫቲካን
የጸሎተ ሐሙስ መስዋዕተ ቅዳሴ በቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን ማበረታቻ የሰጡት በጸሎተ ሐሙስ ቀን ማለዳ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በተካሄደው የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ሰረዓት ላይ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በስብከታቸው ወቅት፣ የቤተ ክርስቲያናችን የመጀመሪያው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ የነበረው ቅዱስ ጴጥሮስ ክርስቶስን እንዴት ስቶ ሦስት ጊዜ እንደካደው በማሰላሰል ነበር። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጸጸት ጊዜ የጴጥሮስ አይኖች በእንባ ተጥለቀለቁ "ከቆሰለው ልብ ተነስቶ ከውሸት ሀሳቡ ራሱን ነፃ አውጥቷል" በማለት አስታውሰዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “እነዚያ መራራ እንባዎች የቅዱስ ጴጥሮስን ልብ እና ሕይወቱን ቀይረዋል” ብለዋል።

የጸሎተ ሐሙስ መስዋዕተ ቅዳሴ በቫቲካን
የጸሎተ ሐሙስ መስዋዕተ ቅዳሴ በቫቲካን

“ውድ ወንድሞች ካህናት፣ የጴጥሮስ ልብ ፈውስ፣ የሐዋርያው ፈውስ፣ የመጋቢው ፈውስ፣” በማለት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የተናገሩ ሲሆን “በኀዘን ተወጥሮና ንስሐ በገባ ጊዜ ራሱን በኢየሱስ ይቅርታ እንዲደረግለት በፈቀደ ጊዜ ነው" በማለት ፈውሱ በእንባና በመራር ልቅሶ ውስጥ መፈጸሙን ገልጿል፤ ይህም እንደገና ፍቅርን እንዲጎናጸፍ እንዳደርገው ተናግሯል።

በዚህ የጸሎት ሐሙስ ቀን፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት፣ በተወሰነ ደረጃ የተዘነጋ፣ አሁንም አስፈላጊ የሆነውን የመንፈሳዊ ሕይወት ገጽታን ከካህናት ባልደረቦቻቸው ጋር ለማካፈል እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። "እኔ ልጠቀምበት የምፈልገው ቃል እንኳን በመጠኑም ቢሆን ያረጀ፣ ነገር ግን በደንብ ለማሰላሰል ብቁ ነው። ያ ቃል መጨናነቅ የሚለው ነው" ብለዋል ቅዱስነታቸው።

የጸሎተ ሐሙስ መስዋዕተ ቅዳሴ በቫቲካን
የጸሎተ ሐሙስ መስዋዕተ ቅዳሴ በቫቲካን

ሐዘን ፣ “የልብ መሰበር”

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደተናገሩት፣ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዳደረገው የንስሐ እንባ የሚያመጣውን የሚያሠቃይ “የልብ መሰበር” ይጨምራል ያሉ ሲሆን ተስፋ እንድንቆርጥ ወይም ብቁ ባለመሆናችን እንድንጠመድ የሚያደርገው የጥፋተኝነት ስሜት ሳይሆን ልብን የሚያነጻና የሚፈውስ ጠቃሚ “የልብ መሰበር” እንደሆነ ገልጿል።

ኃጢያታችንን ከተገነዘብን በኋላ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት “በውስጣችን የሚፈልቀውን የሕይወት ውኃ ምንጭ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ልባችን ሊከፈት ይችላል፣ እናም እንባ ወደ ዓይኖቻችን እንዲፈስ የሚያደርገው እርሱ ነው” ብለዋል። “ጭንብል እንዳይገለጥ” ፈቃደኛ የሆኑ እና የእግዚአብሔር እይታ ልባቸውን እንዲወጋ የሚፈቅዱ፣ የእነዚያን እንባዎች ስጦታ፣ ከጥምቀት በኋላ ያለውን ቅዱስ ውሃ ይቀበላሉ” ብሏል።

ሆኖም ስለ ራሳችን ማልቀስ ምን ማለት እንደሆነ በግልጽ መረዳት እንደሚያስፈልገን ገልጿል።

"ብዙ ጊዜ ለማድረግ እንደምንፈተን ለራሳችን መራራ በሆነ መልኩ ማልቀስ ማለት አይደለም" ስለ ራሳችን ማልቀስ፣ “በኃጢአታችን እግዚአብሔርን ስላሳዘንን በጽኑ ንስሐ መግባት ማለት ነው፤ ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ዕዳ ውስጥ እንደምንኖር አውቀን ከቅድስናና ከታማኝነት መንገድ ርቀን ነፍሱን ከሰጠን ከአምላክ ፍቅር እንደ ወጣን አምነን መቀበል ማለት ነው" ብለዋል።

የጸሎተ ሐሙስ መስዋዕተ ቅዳሴ በቫቲካን
የጸሎተ ሐሙስ መስዋዕተ ቅዳሴ በቫቲካን

ውለታ ቢስ እና ባለመጽናታችን ይቅርታ መጠየቅ

ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህን መለማመድ ማለት "ወደ ውስጥ መመልከት እና ውለታቢስ መሆናችን እና ያለማቋረጥ ንስሐ መግባት" እና "ሁለት ዓይነት ኑሮ የምንኖር መሆናችንን፣ ታማኝ አለመሆናችንን እና ግብዝነታችንን በሀዘን መቀበል ማለት ነው" ብለዋል።

ዓይኖቻችንን በድጋሚ ወደ የተሰቀለው ጌታ በማዞር እና እራሳችንን በፍቅሩ እንድንነካ በማድረግ ሁል ጊዜ ይቅር የሚል እና የሚያነሳውን፣ “እርሱን ተስፋ የሚያደርጉትን ኢየሱስ ከቶ አያሳዝንም” ብሏል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጉንጮቻችን ላይ የሚፈሱት እንባዎች "ልባችንን ለማንጻት ይወርዳሉ" ሲሉ አሳስበዋል።

“ይህ የጭንቀት ምንጭ ሳይሆን የነፍስ ፈውስ ነው፤ ምክንያቱም በኃጢአት ቁስል ላይ መድኅኒት የሆነ ቅባት ሆኖ ስለሚያገለግል፣ “የተሰበረውን” የሚለውጥ የሰማያዊውን ሐኪም እንክብካቤ እንድንቀበል ስለሚያዘጋጀን የተሰበረ ልብ” አንዴ በእንባ ከረሰረሰ ለለውጥ ያዘጋጃል ማለታቸው ተገልጿል።

እንደ ልጆች መሆን

የመንፈሳዊ ሕይወት ሊቃውንት ቅዱስ አባታችን እንደ አስታወሱት ከሆነ የውስጥ መታደስ ሁሉ በእኛ የሰው ሰቆቃ እና በእግዚአብሔር ምሕረት መካከል ባለው ግንኙነት የተወለደ እና በመንፈስ ድህነት የሚዳብር መሆኑን በማስታወስ፣ የመደመርን አስፈላጊነት አጥብቀው ይጠይቃሉ። መንፈስ ያበለጽገን ዘንድ ልንጠይቅ ይገባል ብለዋል።

“ወንድሞች ካህናት” በማለት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ “ወደ ራሳችን በመመልከት ለሕሊናና ለጸሎታችን መረበሽ እና እንባ ምን ድርሻ እንዳላቸው እራሳችንን እንጠይቅ” በተለይም ዓመታት እያለፉ ሲሄዱ እንባችን እየጨመረ እንደሄደ ራሳችንን እንጠይቅ ብለዋል።

በእድሜ እየገፋን በሄድን ቁጥር የምናለቅስበት ሁኔታ እየቀነሰ እንደሚሄድ በቁጭት ተናግረው በምትኩ “እንደ ልጅ እንድንሆን ተጠየቅን” በማለት ተናግሯል።

“ማልቀስ ቢያቅተን ወደ ኋላ እንመለሳለን በውስጣችንም እናረጃለን” በማለት ሲያስጠነቅቁ “ጸሎታቸው ቀለል ያለና ጥልቅ የሆነ፣ በእግዚአብሔር ፊት በአምልኮና በመደነቅ ላይ የተመሠረተ ከሆነ ታድጋላችሁ፣ ትጎለምሳላችሁ” ብለዋል። በዚህም ሁኔታ "ከራሳቸው ጋር በጣም የተቆራኙ እና ከክርስቶስ ጋር የተቆራኙ ይሆናሉ" ብሏል።

ከክርስቶስ ጋር መቆራኘት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል ስለ አብሮነት እንደ ሌላው የሐዘን ገጽታ አድርገው በመግለጽ "በብፁዓን መንፈስ ነፃ የወጣ ታጋሽ ልብ በተፈጥሮው ለሌሎች መተሳሰብን ለመለማመድ የተጋለጠ ነው። በወንድሞቻችን እና በእህቶቻችን ስህተት ንዴት እና አሳፋሪ ተግባር ልባችን እንዲሰማው ከማድረግ ይልቅ ለኃጢአታቸው ማልቀስ ይኖርብናል” ማለታቸው ተገልጿል።

ጌታ አሉ ቅዱስነታቸው ምዕመናንን ሲያስታውሱ “ከሁሉም በላይ ለእርሱ የተቀደሱትን ወንዶችንና ሴቶችን፣ በቤተ ክርስቲያንና በዓለም ኃጢአት የሚያለቅሱትን፣ እና ስለ ሁሉም አማላጆች እንዲሆኑ ይፈልጋል” ማለታቸው ተገልጿል።

በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ጀግኖች ምስክሮች

"በቤተክርስቲያን ውስጥ ስንት ጀግና ምስክሮች እንደዚህ አሳይተውናል" በማለት ተደንቀው የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "በምስራቅ እና በምዕራብ ያሉ የበረሃ መነኮሳትን እናስባለን ፣ ስለ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘ ናሬክ የማያቋርጥ ምልጃ ፣ በለቅሶ እና በእንባ ፣ የፍራንችስኮስ ለፍቅር መስዋዕትነት የመሳሰሉትን እና በዚህ መልክ የኖሩትን ብዙ ካህናት እናስባለን ። ለሌሎች መዳን የንስሐ ሕይወት” ኑረው አለፈዋል ሲሉ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው “ይህ ቅኔ አይደለም፣ ክህነት እንጂ!” ሲል አስታውሷል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለካህናቱ እንዴት ጌታ "ከእኛ እረኞች" ምን እንደሚፈልግ የተናገሩ ሲሆን ጭካኔን ሳይሆን ፍቅርን "ለጥፉታችን ደግሞ እንባ" ነው የሚፈልገው ብለዋል።  

ምዕመናን ልባቸው የሐዘን ስሜት ከተሰማው በፅናት እና በምሕረት እንጂ በውግዘት አትመልሱ ብሏል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ “እኛን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር አደራ ለመስጠት እና በእርሱ ውስጥ የሚጠብቀንን መረጋጋት ለማግኘት ከጭካኔ እና ከጥላቻ ፣ ከራስ ወዳድነት ፣ ከግትርነት እና ከብስጭት ነፃ ልንወጣ እንዴት ያስፈልገናል ማዕበሉ በዙሪያችን እየነደደ ነው!" ሲሉ ጥያቄ አንስተዋል።

"ስለሌሎች እንጸልይ፣ እንማለድ እና እንባዎቻችንን እናፍስ" በማለት አሳስቧል፣ "በዚህ መንገድ ጌታ ተአምራቱን እንዲሰራ እንፈቅዳለን እናም አንፍራ ፣ በእርግጥ ያስደንቀናል!" ብለዋል።

በጸሎት የሚፈለግ ጸጋ

ቁርጠኝነት የእኛ ሥራ ሳይሆን፣ እንደዚሁ በጸሎት መፈለግ ያለበት ጸጋ መሆኑን ገልጿል።

የእግዚአብሔር ስጦታና የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ወደ ተባለው ወደ ንስሐ ስንሸጋገር፣ ቅዱስ አባታችን የንስሐ መንፈስን ለማዳበር ሁለት ምክሮችን አቅርበዋል።

"ህይወታችንን እና ጥሪያችንን ከቅልጥፍና እና ፈጣን ውጤት አንፃር ማየትን እና አሁን ባለው ፍላጎቶች እና ተስፋዎች መያዙን እናቁም ይልቁንም ነገሮችን ካለፈው እና ከመጪው ታላቅ አድማስ አንፃር እንመልከተታቸው፣ የእግዚአብሔርን ታማኝነት በማስታወስ፣ ይቅር ባይነቱን በማስታወስ እና በፍቅሩ ጸንተን በመኖር እና የወደፊቱን ጊዜ፣ “የተጠራንበትን ዘላለማዊ ግብ የሕይወታችን ዋና ዓላማ በመመልከት ያለፈውን እንዲያስቡ” አሳስቧቸዋል። "የአስተሳሰብ አድማሳችንን ማስፋት ልባችንን ለማስፋት፣ ከጌታ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ እና መተሳሰብን ለመለማመድ ይረዳል ብሏል።

ሁለተኛ መንገድ ደግሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደገለጹት ከሆነ ካህናትን “ግዴታ እና ተግባራዊ ሳይሆን በነጻ የተመረጠ፣ የተረጋጋና የሚረዝም” ጸሎትን የማዳበር አስፈላጊነትን እንደገና እንዲገነዘቡ አሳስበዋል።

"ወደ ስግደት እና ወደ ልብ ጸሎት እንመለስ" ሲል ተናግሯል።

"የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ ኃጢአተኛ ነኝ ማረኝ"

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል 'የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ ኃጢአተኛውን እኔን ማረኝ' ማለት በተደጋጋሚ እንዲለምዱ ካህናቱን ጋብዟቸዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ "የራሳችንን ኃጢአተኝነት እያሰብን እንኳን የእግዚአብሔርን ታላቅነት እናስተውል፣ ለዓይናችንም የፈውስ ኃይል ልባችንን እንክፈት" በማለት የሃይማኖት አባቶች "ጸሎታችን እንዲጀመር የቅድስት እናት ቤተክርስቲያንን ጥበብ እንደገና እንዲያውቁ ያስችላቸዋል" ሲሉ አሳስበዋል። አምላኬ ሆይ እርዳኝ ብሎ በሚያለቅስበት ምስኪን ቃል እርሱን ልንማጸን ይገባል ብለዋል።

ወደ ቅዱስ ጴጥሮስና እንባው ሲመለሱ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ “ከመቃብሩ በላይ የምናየው መሠዊያ እኛ ካህናት በየቀኑ የምንለውን ጊዜ ሁሉ እንድናስብ ያደርገናል፡- ሁላችሁም ይህን ውሰዱ ከእርሱም ብሉ። ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ነውና" - እጅግ የወደደን እጃችን ላይ ይገኛልና እርሱን ልንባርክ ይገባናል ብለዋል።  

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “እንግዲያውስ መልካም እናደርጋለን” በማለት በጸጥታ የምንላቸውን ጸሎቶች ለመድገም፦ ‘በትሕትና በተሰበረ ልብ ጌታ ሆይ በአንተ ዘንድ ተቀባይነትን ያግኝልን’ እና ‘ጌታ ሆይ፣ ከኃጢአቴ እጠበኝ’፣  ከኃጢአቴም አንጻኝ ብለነው ልንማጸን ይገባናል ብለዋል።

የጸሎተ ሐሙስ መስዋዕተ ቅዳሴ በቫቲካን
የጸሎተ ሐሙስ መስዋዕተ ቅዳሴ በቫቲካን

ውድ ካህናት እጅግ አመሰግናልችኋለሁ

አንድ ሰው ልቡ ከተሰበረ፣ ቅዱስ አባታችን እንዳሉት ከሆነ  በእርግጥ ኢየሱስ ማሰር እና መፈወስ ይችላል ያሉት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ "የተከበራችሁ ካህናት አመሰግናለው" ሲሉ ተናግሯል "ስለ ክፍት እና ታዛዥ ልባችሁ ... ድካማችሁ እና እንባዎቻችሁ ሁሉ" እና "በአሁኑ ዓለም ላሉ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የእግዚአብሔርን የምህረት ተአምር ስለምታደርጉ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ " ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጌታ ታማኞቹን ካህናቱን እንዲያጽናና፣ እንዲያበረታ እና እንዲክሳቸው በጸሎት ከጠየቁ በኋላ ስብከታቸውን አጠቃለዋል።

 

 

28 March 2024, 16:56