ፈልግ

ቫቲካን ከሌሎች አገራት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት የሚመለከተው ጽህፈት ቤት ዋና ፀሐፊ ሊቀ ጳጳስ ፖል ጋላገር ቫቲካን ከሌሎች አገራት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት የሚመለከተው ጽህፈት ቤት ዋና ፀሐፊ ሊቀ ጳጳስ ፖል ጋላገር 

ሊቀ ጳጳስ ጋላገር ለ4 ቀን ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት ወደ ሞንቴኔግሮ ማቅናታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፖል ሪቻርድ ጋላገር ቫቲካን ከሌሎች አገራት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት የሚመለከተው ጽህፈት ቤት ዋና ፀሐፊ ለአራት ቀናት የቦልካን ሀገር ሞንቴኔግሮ እየጎበኙ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ከመንግሥት ባለስልጣናት እና ከአካባቢው የካቶሊክ ማህበረሰብ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ከሐሙስ መጋቢት 11 እስከ እሑድ መጋቢት 15/2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆየው ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር፣ ቅድስት መንበር ከሌሎች አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት የምያደርገው ጽሕፈት ቤት ፀሐፊ ሞንቴኔግሮን እየጎበኙ ይገኛሉ፣ በባልካን አገር በሚኖራቸው ቆይታ ከፕሬዚዳንቱ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር ይገናኛሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ጉብኝቱ የተገለጸው ኤክስ ወይም በቀድሞ አጠራሩ ቲውተር በመባል በሚታወቀው በ @TerzaLoggia የቅድስት መንበር ጽህፈት ቤት ኦፊሴላዊ ዘገባ ላይ ነው። የሊቀ ጳጳሱ ጉብኝት የቀረበው ሐሙስ ዕለት በተገናኟቸው የሞንቴኔግሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ኢቫኖቪች ግብዣ የቀረበ ነው።

አርብ መጋቢት 13/2016 ዓ.ም ሊካሄድ የታቀደው ግንኙነት ከሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ጃኮቭ ሚላቶቪች ጋር ሲሆን በመቀጠል ከፓርላማው ፕሬዝዳንት አንድሪያ ማንዲች እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሚሎይኮ ስፓጂች ጋር ይገናኛሉ።

በእለቱ ሊቀ ጳጳስ ጋላገር በቅድስት መንበር እና በሞንቴኔግሮ መካከል ያለውን መሠረታዊ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ መክፈቻ ላይ ይገኛሉ።

የጉብኝቱ ዋና ነጥብ ቅዳሜ መጋቢት 14/2016 ዓ.ም በቅዱስ ትሪፎን ካቴድራል መስዋዕተ ቅዳሴ በሚያሳርጉበት ወቅት ከኮቶር ሀገረ ስብከት ካቶሊካዊ ማህበረሰብ ጋር መገናኘት ነው።

እሑድ የጉዞው የመጨረሻ ቀን ሊቀ ጳጳስ ጋላገር ከባር ሊቀ ጳጳስ ካቶሊካዊ ማኅበረሰብ ጋር ተገናኝተው በቅዱስ ጴጥሮስ ኅብረት ካቴድራሉ ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴ ለማሳረግ ተዘጋጅተዋል።

 

22 March 2024, 15:29