ፈልግ

ፍልስጤማዊ ዶክተር በእስራኤል በእስር ላይ በነበሩበት ወቅት የደረሰባቸውን በደል ተናገሩ ፍልስጤማዊ ዶክተር በእስራኤል በእስር ላይ በነበሩበት ወቅት የደረሰባቸውን በደል ተናገሩ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የዓለም ሕሙማን ቀን ስለ ምያንማር፣ ፍልስጤም፣ እስራኤል እና ዩክሬን ጸለዩ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዓለም ላይ ሕክምና ማግኘት ለማይችሉ እና በተለይም በጦርነት ለሚማቅቁ እንደ ምያንማር፣ ፍልስጤም፣ እስራኤል እና ዩክሬን ላሉ ሁሉ ጸሎት ማቅረባቸው ተገለጸ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮ እሁድ ጥር 3/2016 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡ ምዕመናን ጋር መላኩ ገብርኤል ማርያምን ያበሰረበትን የመልአከ ሰላም ጸሎት በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልዕክት ቅዱስነታቸው እንደገለጹት የዓለም የሕሙማን ቀን መከበሩን አስታውሰው “በዚህ ዓመት በሕመም ውስጥ ያሉ ግንኙነቶችን አስፈላጊነት ላይ ትኩረት መስጠት ይገባል” ብለዋል ።

በዚህ ረገድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ በምንታመምበት ጊዜ የሚያስፈልገን የመጀመሪያው ነገር “የምንወዳቸው ሰዎች ቅርበት” እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችና የእግዚአብሔር ግንኙነት መሆኑን ጠቁመዋል።

“ሁላችንም የተጠራነው ከሚሰቃዩት ጋር እንድንቀራረብ ነው” በማለት የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “እናም የመላው ቤተ ክርስቲያን ግንኙነት” ለታመሙ ወይም አቅመ ደካሞች ያላቸውን ቅርበት ገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል ይህ ቀን ስለሚከበር ዝም ማለት እንደማይቻል አጽንኦት ሰጥተው ነበር፣ “በአሁኑ ጊዜ የመተሳሰብ መብት እና የመኖር መብት የተነፈጉ ብዙ ሰዎች መኖራቸውን በተመለከተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው “በከፍተኛ ድህነት ውስጥ የሚኖሩትን እያሰብኩ ነው፤ ግን ስለ ጦርነቱ ግዛቶችም እያሰብኩ ነው፡ እዚያም መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች በየእለቱ ይጣሳሉ! የማንታገሰው ነገር ነው" ብለዋል። በመቀጠልም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለዩክሬን፣ ፍልስጤም እና እስራኤል ጸልየዋል፣ ለማያንማር ያደርጉትን ጸሎት ከማደስ በፊት ቅዱስ አባታችን በየካቲት 01/2016 ዓ.ም የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካደረጉ በኋላ የጸለዩላቸው የሮሂንጊያ ሙስሊሞች ለከፋ ጥቃትና በማንነታቸው ስደት እየደረሰባቸው ነው ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

12 February 2024, 15:40