ፈልግ

2024.02.28 Udienza Generale

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ለምርመራ ወደ ሆስፒታል መሄዳቸው ተገለጸ!

ሳምንታዊውን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ተከትሎ ባለፉት ቀናት ቀለል ባለ የጉንፋን በሽታ እየተሰቃዩ ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ለአንዳንድ የሕክምና ምርመራ በሮም ከተማ ወደ ሚገኘው ጂሜሊ በመባል ወደ ሚታወቀው ሆስፒታል በመሄድ አስፈላጊውን የጤና ምርመራ ካደረጉ በኋላ ወደ ቫቲካን መመለሳቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮማ ከተማ ወደ ሚገኘው የጂሜሊ ሆስፒታል የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካደረጉ በኋላ በቀጥታ ወደ እዚያው በማቅናት አንዳንድ ምርመራዎችን ማድረጋቸውን የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት የካቲት 20/2016 ዕለት ይፋ ባደርገው መግለጫ አስታውቋል። ቅዱስነታቸው አጠቃላይ የጤና ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ ወደ ቫቲካን መመለሳቸው ተገልጿል።

29 February 2024, 16:45